ወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ ትግል፡ በታላቅ ድል ያሸበረቀና ማይቀለበስ የትውልድ ተቀዳሚ አጀንዳ – ልሳነ ግፉዓን

የወልቃይት የጠገዴና የጠለምት ማህበረሰብ ከፋሽስቱና ከተስፋፊው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ድርጅትና ሆዳም ባንዳዎች በኩል የደረሰበትን ወረራና የዘር ማጽዳት ከፍተኛ ወንጀል በመመከት ዘሩን፣ ዕርስቱንና፣ ብሎም ታላቋን ኢትዮጵያ በቀደምት ጠላቶቿ ከተደገሰላት የጥፋት ጥቃት ለመታደግና ተላላኪው የህወሃት ቡድን ይህን እኩይ የጥፋት አጀንዳ በመሸከም ታላቁን የተከዜ ወንዝ ተሻግሮ በወረራና የታላቋን ትግራይ ምስረታና ተስፋፊነት እውን አደርጋለሁ በሚል ከ1972 ዓም ጀምሮ የጎንደርን ታሪካዊና ለም መሬቶች በሃይል ከረገጠበት እለት ጀምሮ ለአለፉት 36 አመታት በተለያየ መልኩ ያላቋረጠ ትግል ሲያካሂድ፣ የህይወት መስዋዕትነት ሲከፍልና፣ ብሶቱንና ሰቆቃውን ለመላው የኢትዮጵያና የዓለም ህዝብ ሁሉ ሲያሰማ ቆይቷል።
እነሆ ይህን ፍትሃዊ ትግልና መራር ጩሃት አብሮ ሲታገልና በንቃት ሲከታተል የቆየው መላው ጎንደር፣ የጎጃም፣ እንዲሁም የአማራና የኢትዮጵያ ህዝብ እብሪተኛውና አፋኙ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ድርጅት ይህን ከትውልድ ወደ ትውልድ በመሸጋገር ላይ ያለ ሰላማዊና ህጋዊ የሰብአዊነትና የማንነት ጥያቄ አንግበው በቆራጥነትና በፍፁም ጨዋነት ለኢትዮጵያ ህዝብና በሃገሪቱ ውስጥ አሉ ለሚባሉ የፍትህ አካላት ሁሉ ጥያቄውን በቁርጠኝነትና በጀግንነት ያቀረቡ «የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ» ኮሚቴ አባላትን እንደለመደው በሌሊት ለማፈንና ለመግደል ሃምሌ 5 2008 ዓም ጎንደር ከተማን የወረረው የትግራይ አፋኝ ሃይል አቶ አታላይ  ዛፌን ፣ አቶ ጌታቸው አደመን፣ አቶ አለነ ሻማንና አቶ መብራቱ ጌታሁን አለሙ እንደ ሌባ በሌሊት ካፈነ በኋላ ሌላኛውን የኮሚቴ አባል የሆነውንና «በሌሊት ለሚመጣ ሃይል እጀን አልሰጥም» ያለውን የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ቤት ሰብሮ ለመግባትና ለማፈን በከፈቱት የእብሪት ጥቃት ምክንያት ጀግናው የህዝብ ልጅ ኮሎኔል ደመቀ ራሱን ለመከላከል በወሰደው ቆራጥ እርምጃ ምክንያት የኮሚቴ አባላቱን ከማንኛውም ጠቃት በንቃትና በስስት ሲጠብቅ የነበረው አይበገሬውና ቆራጡ የጎንደር ህዝብ ከሁሉም አቅጣጫ በፍጥነት በመድረስ ባደረገው ተጋድሎ የኮሎኔሉን ህይወት ማትረፍ የተቻለ ሲሆን ትግሉም ወደ ታለመለትና ሲጠበቅ ወደ ነበረው እርከን በአመርቂ ሁኔታ እንዲያድግ አስችሎታል፡፡
ይልቁንም ይህ የወልቃይት የጠገዴና የጠለምትን ማህበረሰብ ከ36 ዓመታት በላይ መራር የህይወትና የንብረት መስዋእትነት ሲያስገብር የኖረው ፍትሃዊ ጥያቄና ህዝባዊ ትግል እነሆ ዛሬ በመላው ጎንደርና ጎጃም በፍጥነት እንዲቀጣጠልና በተለይም የአማራ ወገናችን የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር የጫነበትን የግፍ አገዛዝ በቃኝ እንዲልና ይህን የፋሽስት ስርዓት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ ቆርጦ እንዲነሳ፣ ይልቁንም ይህን ታላቅ ህዝብ ጥያቄ በማነገብና ተቀዳሚ አጀንዳ በማድረግ በቆራጥነት እየታገለ ይገኛል።
ስለዚህም በዚህ ታሪካዊና ፍትሃዊ የህዝብ ትግል ውስጥ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በመሳተፍ ክቡር የሆነውን የህይወት መስዋእትነት እየከፈለ በትግል ላይ ላለው ወገናችን ሁሉ ልሳነ ግፉዓን ልባዊ አክብሮቱንና ምስጋናውን ያቀርባል፡፡ ለሰማዕታቱም ቤተሰቦችና ወዳጆች በሙሉ መፅናናትን ይመኛል፡፡
ህዝባዊ ትግሉ የሚገኝበት ተጨባጭ ሁኔታ
በኢትዮጵያ ሁሉም ማእዘናት የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ የህወሃት መራሹን መንግስት ህልውና ከመሰረቱ ያናጋውና የማይቀረውን ታሪካዊ ሞቱን ያረጋገጠ መሆኑን ብናውቅም የትግራዩ ነፃ አውጭ ድርጅት ይህን ሃያል የህዝብ ትግል ዳግም ለመቀልብስና የህዝባችንን አንገት ለማስደፋት ላይና ታች እየኳተነ እንደሆነ በሚያደርገው መንፈራገጥ፣ የባለስልጣናት ሹመትና ሽረት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች ጋጋታ ወዘተ በአግራሞት እየተከታተልን ነው።
ለምሳሌ የወልቃይትን ህዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄን በህጋዊ መንገድ ለማቅረብ የተመረጡትን ሰላማዊና ህጋዊ የህዝብ ወኪሎች በሙሉ እየለቀሙ በተመረጡ የትግራይና ሌሎች የማሳቃያ ቤቶች በማጎርና መራር ስቃይን ከፈፀሙባቸው በኃላ የተለመደውን የሃሰት ፍርድ በታወቀውና የኢትዮጵያን ውድ ልጆች በህግ ሽፋን ቀርጥፎ በበላው የህወሃት የካንጋሮ ፍርድ ቤት ለማስፈረድ አዲስ ህወሃታዊ ድራማ እየተሰራባቸው መሆኑን አረጋግጠናል። ይህም ድራማ ሰሞኑን እነ አቶ አታላይ ዛፌን፣ ጌታቸው አደመን፤ አለነ ሻማን፣ መብራቱ ጌታሁን፣ ባንቲሁን ነጋ ወዘተ… ያካተተ እንደሚሆን ታውቋል። ድራማውን የደመቀ ለማድረግ በጎንደር ከተማ የአንገረብ እስር ቤት ውስጥ የሚገኘውን ጀግና ወንድማችን ኮሎነል ደመቀን ዘውዱን ከእስር ቤቱ አፍነው ህወሃት ወደ አዘጋጀው ልዩ የማሰቃያ ቦታ ለመውሰድ ከፍተኛ ሙከራ እያደረጉ ይገኛል።
በሌላ በኩል ደግሞ በህወሃት አዝማችነት በጎንደር ህዝብ ላይ በታወጀው የጥፋት አዋጅና በተላላኪው ብአዴን ጠቋሚነትና መንገድ መሪነት በህዝባችን ላይ ለዘመተው አፋኝና ገዳይ ቡድን እጅ አንሰጥም ያሉትንና እራሳቸውን ለመከላከል ከመኖሪያቸው የሸሹትን ወገኖች ተከታትሎ በፍፁም ጭካኔ በመግደልና ክቡር ስጋቸው ላይ ፀያፍ ተግባራትን የመፈፀም ስራ ውስጥ ተጠምዶ ይገኛል፡፡ ለምሳሌ ወጣት ዘውዱና ወጣት ሙላው የሚባሉ የወልቃይት ተወላጆች ከሚሰሩበት እርሻ ቦታ አፋኝ ቡድን በመላክ ወጣቶቹን ለማፈን ሲሞክሩ ወጣቶቹ እንደ ጀግኖች አባቶቻቸው እጅ አንሰጥም በማለት ሊያፍኑ ከመጡት የህወሃት አፋኝ ቡድን ጋር በተደረገው የተኩስ ልውውጥ አራቱን ገድለው በክብር ተሰውተዋል። በተመሳሳይ ሁኔታ ብረት አንስተው በመታገል በዳንሻ (ጠገዴ) ከተማ የተሰው ሁለት ታጋዮችን ክቡር አስከሬን ህዝብ በብዛት በተሰበሰበበት የገበያ ቦታ በመኪና በመጎተት የታጋዩን ሃይል ወላጆችና ህፃናት ልጆች ለማሸበርና ለማሸማቀቅ ፋሽስታዊ ተግባራትን በህዝባችን ላይ እየፈፀሙ ይገኛሉ፡፡
እንዲሁም ፋሽስቱ ህወሃት የጎጃምና የጎንደር ታጋይ አማራዎችን በተለያዩ መንገዶች እየነጣጠሉ በመምታት፣ የገበሬውን ቤትና ምርት በማቃጠል ሰላማዊ ህዝብን በከፍተኛ ርሃብና እርዛት ጭምር ለመቅጣት በማሴር ታሪክ ይቅር በማይለው እኩይ ተግባር ውስጥ ተሰማርቶ ይገኛል። ለምሳሌ በወገራ አውራጃ ውስጥ በእንቃሽ በቆላ ወገራ ከ500 ቤቶችና ለአጨዳ የደረሱ የእርሻ ማሳዎች በህወሃት ሮኬቶች የተቃጥሉ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ዛሬም ድረስ ታዳጊ ወጣቶችን በገፍ በማፈስና እንደ ብር ሸለቆ አይነት ማጎሪያዎች ውስጥ በማስገባት ሁለንተናዊ ስቃይና መከራ እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
በአንፃሩ ደግሞ ታጋዩ ህዝባችን ከምንግዜውም በላይ የህወሃትን ፋሽስትነትና የአማራ ዘሩን ፈፅሞ ሊያጠፋ እንደመጣ በመረዳት ሃይሉን የማጠናከርና ትግሉን በድል ለመወጣት ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ የሚገኝበት ደረጃ ላይ ይገኛል። ይልቁንም ይህ እኩይ ስርዓት እንደ ቀደሙት አምባገነን ስርዓቶች ሁሉ የህዝብ ወገን በመምሰል የሚያጭበረብርበት ጭምበል በመገፈፉና ተስፋ በመቁረጡ ምክንያት በህዝብ ላይ የሚያደርሰውን የጀምላ ፍጅትና እስር በመቀልበስ እንደ ቀደሙት ፋሽስቶች ሁሉ አይቀጡ ቅጣት ለመቅጣትና ታሪክ አድርጎ ለማስቀረት ህዝባችን በቁርጠኝነትና በአንድነት እንደተነሳ አረጋግጠናል።
ወድ ወገኖቻችን   
ምንም እንኳን የመቀበሪያ ጉድጓዱ የተማሰውና የመገነዣ ልጡ የራሰው ህወሃት የወልቃይትን ህዝብ ጥያቄ በሃይል ለማፈን እየተጓዘበት ያለው የተስፋ መቁረጥ መንገድ የብዙ ወገኖቻችንን ውድና ክቡር ህይወት እየቀጠፈ ቢገኝም እንኳ የህዝብን ጠያቄ በሃይል አፍኖና አስተዳድረዋለሁ የሚለውን ህዝብ በጀምላ ጨፍጭፎና በገፍ አስሮ በስልጣን ላይ ለመቀጠል የሞከረ ስርዓት በኢትዮጵያችንም ሆነ በአለማችን ታሪክ እንዳየነው ተገዶና ተዋርዶ መወገድ ነውና ተረኛው ህወሃትም በህዝብ ሃይል የውርድት ፅዋውን ተግቶ ከኢትዮጵያችን በቅርቡ እንደሚወገድ ልናረጋግጥ እንወዳለን፡፡ ይልቁንም የመላው ኢትዮጵያ በተለይም የወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ ጥያቄ ፍትሃዊ ምላሽ የሚያገኘው በማያሻማ ሁኔታ የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባርና ተባባሪ ባንዳዎቹ ግብአተ መሬት ሲዎርዱ ብቻና ብቻ መሆኑን ልሳነ ግፉዓን በጥብቅ ያምናል።
በመሆኑም ይህን ፋሽስትና እኩይ ቡድን የጥፋት እድሜ ለማሳጠርና ለህዘባችንና ለሃገራችን ሰላምና ፍትህን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጎናፀፍ ይቻል ዘንድ ልሳነ ግፉዓን የሚከተሉትን ህዝባዊ ጥሪዎች ያቀርባል።
1ኛ. ከትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ድርጅት ጋር በማበር በወገናችሁ ላይ በመንገድ መሪነት፣ በጠቋሚነት፣ በተላላኪነትና፣ በገዳይ አስገዳይነት የተሰለፋቹህ የአማራ፣ የኦሮሞና፣ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የተለቃቀማችሁ ባንዳዎችና ሆድ አደሮች ሁሉ ከህወሃት ጋር ያላችሁን ትስስር በማቆም አሁኑኑ በትግል ላይ ወደሚገኙው ህዝባቹህ ተቀላቀሉ፤
2ኛ. በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ድርጅትና በተለጣፊዎቹ በብአዴንና በኦህዴድ አሻንጉሊት ድርጅቶች ስር ያለህ የአማራና የኦሮሞ ልዩ ኃይልና የፈዴራል ጦር አባላት ለታላቋ ትግራይ ምስረታና ተስፋፊነት ስትል በራስህ ወገን ላይ ከመተኮስ እንድትታቀብና ይልቁንም አፈሙዝህን አሁኑኑ በህወሃት መሪዎችና የጦር አዛዦች ላይ እንድታዞርና ዛሬውኑ የህዝብ አጋርነትህን እንድታሳይ ትጠየቃለህ፤
3ኛ በተለይም በጎንደርና በጎጃም ውስጥ የምትገኙ የብአዴን ሚሊሽያዎች በሙሉ!  ከትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር በኩል በቀረበላችሁ የ50,000 ብር ጉርሻ ተደልለህ ወንድምህ ላይ እንድትተኩስና እርስ በራሳችን እንድንተላለቅ የጠላት መሳሪያ አትሁን!   የትግሬ ምርጥ ዘሮች በአንተና በዘርህ ደም ላይ ተንደላቀው እንዲኖሩ አትፍቀድላቸው! በጠላትህ እኩይ ሴራ ላይ ንቃ! ሰሞኑን በጎንደር በወገራ  አውራጃ በዳባት ከተማ አረደጃን ጊዎርጊስ ውስጥ በሃዘን ተቀምጦ የሰነበተው ስፍር ቁጥር የሌለው ወገን ጎንደሬው የአማራ ዘር እንጂ የህወሃቶቹ ምርጥ ዘር የሆነው ትግሬዎቹ አይደሉምና ምን እየሰራህ እንደሆን ቆም ብለህ አስብ! ይህን «እጄን በእጄ ቆረጥኩት» ታሪክ በህዝባችን ላይ እንዲፈፀም ምክንያት በመሆን ላይ ያለህ የአማራ ሚሊሺያ በአስቸኳይ ህዝባዊ ትግሉን ተቀላቀል! መሳሪያህንም በህወሃትና በህወሃት ላይ ብቻ አዙር!
4ኛ. ሀገር ውስጥ ያላቹሁት የእምነት ተቋማትና በተለይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የእምነት መሪዎችና አባቶች የታላላቆቹን ሰማእታትና የህዝብ ወገን የሆኑትን የእነ አቡነ ጴጥሮስ ፈለግ በመከተል የህዝባችሁን መከራና ሰቃይ የሚያራዝም ተግባር ከመፈጸም እንድትቆጠቡና ከህዝባቹህ ጎን እንድትሰለፉ እንማፀናለን! በተለይም ህወሃት በህዝባችን ላይ እያደረሰ ለሚገኘው መከራና ስቃይ ቀጥተኛ ድጋፍ በማድረግ ላይ ከሚገኙት ፓትርያርክ አባ ማትያስ ጋር የምታደርጉትን ትብብርና ህብረት ከወዲሁ ታቋርጡ ዘንድ በአከብሮት እንጠይቃለን!
5ኛ. ለመላው የጎንደርና አማራ ህዝብ፤ ወያኔ የትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት አሁንም የአማራውን አንገት ለማስደፋት ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ከጎንደር እስር ቤት አፍኖ በመውሰድ አሰቃይቶ ለመግደል ሙከራ እያደረገ እንደሆነ በመገንዘብ ይህን ብርቅዬና ቆራጥ መሪ ከህወሃት ጥቃት የመከላከልና ከእስርና ስቃይ የማዳን ግዴታና ሃላፊነት እንዳለብን በመገንዘብ አሁኑኑ በአንድነት በመነሳት ተገቢውን እርምጃ እንድንወስድ እናሳስባለን!
በመጨረሻም በሃገራችን ጉዳይ ያገባናል በማለት በህዝባዊ ትግሉ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በመሳተፍ የአቅማችሁን አስተዋፅኦ ለማበርከት ለምትደክሙ የፖለቲካም ሆነ የሲቪክ ተቋማት፣ ጋዜጠኞችና፣ አክቲቪስቶች በሙሉ አሁን በአገራችን እየተካሄደ ያለው ወገንና አገር ማዳን ትግል እንጂ አንዱ የፖለቲካ ድርጅትም ሆነ የሲቪክ ተቋም ወይም ፖለቲከኛ የበላይነቱን ወይም እበልጥ ባይነቱን የሚያሳይበት ሰላማዊ የፖለቲካ ውድድር ወቅት ላይ አይደለንም ብለን እናምናለን። ይልቁንም ዛሬ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ በህወሃት አስቸኳይ የዘር ፍጅት አዋጅ ታውጆበትና ይፋዊ የሆነ ወታደራዊ ዘመቻና ጥቃት ተከፍቶበት በጭንቅ ላይ ያለውን ወገንና አገርን ለማዳን ከፍተኛ ትብብርና መናበብን ልናሳይበት የሚገባ ወቅት ነው የሚል ፅኑ እምነት አለን። ከዚህ በተለየ መንገድ በመሄድ የወገንና የሃገርን ስቃይ የሚያራዝም ተግባር ውስጥ ተሰልፎ መገኘት የህዝባችን ጠላት የሆነው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጭ ግንባር አጋዥ መሆን ነው ብለንም እናምናለን። ስለዚህም ዛሬ ለህዝብ በመቆርቆር ሽፋን የሚደረገው በነገር መጎነታተልና የጎንዮሽ የመነቋቆር ተግባር በአስቸኳይ ቆሞ እርስ በእርስ በመናበብና በመከባበር ከህዝባዊው ትግል ጎን በመሰለፍ ትግሉን ከታለመለት ቦታ ማድረስ የሁላችንም ግዴታና ሃላፊነት መሆኑን አውቆ መታገል ይጠበቅብናል ብሎ ልሳነ ግፉዓን ያምናል። ነገር ግን ይህን ታላቅና ህዝባዊ ትግል በመደገፍ ሽፋንና ለህዝብ ተቆርቋሪ በመምሰል ሽፋን ከህወሃት ቅጥረኞች ባልተናነሰ ሁኔታ ታጋዩን ህዝብ ማወክና የትግሉን አቅጣጫና ኢላማ ከህወሃት ወደ ሌላ ማንኛውም አካል ለማዞር በሚደረግ አሳፋሪና አስተዛዛቢ ተግባር ተሰማርቶ መገኘት ዛሬም ይሁን ነገ ከተጥያቂነት የማያድን መሆኑን በወልቃይት ጠገዴና ጠለምት ህዝብ ስም አበክረን ማሳሰብ እንወዳለን!
ድል ለተገፋው ህዝባችን!
ሞት ለትግራይ ነጻ አውጭ ድርጅት!
ሞት ለባንዳዎች!
ልሳነ ግፉዓን
ታህሳስ 17 2009 ዓም
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s