ህወሓት “አይደገምም” የሚል ቲሸርት በማልበስ ፈታሁ ባለበት ማግስት በመላ ኢትዩጲያ አዲስ ዙር እስርና ግድያ እያካሄደ ይገኛል ።

የህወሓት ባለስልጣናት ኮማንድ ፕስት አፍኖ ያሰራቸውን ንፁሃን ዜጎች በቅርቡ የተወሰኑትን እጅግ በወረደና በዘቀጠ የስነልቦና ጫና መፍጠሪያ “አይደገምም” የሚል ቲሸርት በማልበስ ፈተሁ ባለበት ማግስት በመላ ኢትዩጲያ አዲስ ዙር እስርና ግድያ እያካሄደ ይገኛል ። • በበህርዳር ከተማ የህወሓት-ብአዴን በሚጠራቸው አስገዳጂ የይስሙላ ስብሰባወች ላይ ጥሬ ሃቆችን ሲናገሩ የነበሩ ሰወች በድብቅ እየተገደሉ እየተገኙ ነው ። * ከሳምንት በፊት ነዋሪነቱ ባህርዳር ቀበሌ 02 የሆነ ወጣት ተገድሎ በቀበሌ 04 ትልቁ መስጊድ አካባቢ ተጥሎ ተገኝቷል ። * ከትናንት በስቲያ ነዋሪነቱ ባህርዳር በቀበሌ 14 የሆነ የመንግስት ሰራተኛ ተገሎ ጣና ሃይቅ ውስጥ ተጥሎ ተገኝቷል ። እነዚህ ሁሉ ስለእውነት ፤በህዝብ ላይ ስለሚደርስው ግፍ ፊት ለፊት መናገራቸው ለህወሓት እረጂምና ስውር እጆች ሰለባ ሁነዋል። * ዛሬም ታኅሳስ 19 /2009 ዓ.ም የታላቁ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሚከበርበት በባህርዳር አባይ ማዶ ገብርኤልና ጎርደማ ገብርኤል ቤተክርስቲያናት ላይ የተሰባሰቡ ንፁሃን ወጣቶች በኮማንድ ፕስቱ እንደተያዙ ታውቋል ። በግፍ የታሰሩት ወጣቶች በእምነታቸው መሰረት አመታዊ በዓሉን ተሰባስበው በማክበር ላይ እንዳሉ ነው ። እጅግ ብዙ ወጣቶች በየቀበሌው በሚገኙ ኩሊወች ጠቋሚነት ታስረዋል ፥እየታሰሩም ይገኛል ። እስካሁንም ያሉበት ሁኔታ አድራሻቸው የማይታወቅ ብዙ ወጣቶች ይገኛሉ ። •በየቀበሌው ማጎሪያ ጣቢያወች የታጎሩ ንፁሀን ወንድሞቻችን ወደ ብርሸለቆ ወታደራዊ ካምፕና ማሰቃያ ስፍራ ሊወሰዱ እንደሆነ ልጆቻቸውን ሊጠይቁ የሄዱ እናቶች ይናገራሉ።

image

ናትናኤል መኮንን

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s