የውጭ ምንዛሪ ማዕቀብ እንዲደረግ ለትውልደ-ኢትዮጵያውያኑ ጥሪ ቀረበ

የአስቸኳይ ጊዜ የዉጭ ምንዛሬ ማዕቀብ አዋጅ!

ውድ ኢትዮጵያዊያን፣

ሁላችንም በሚገባ እንደምናውቀው፤

ሀገራችን ኢትዮጵያ በሕወሓት መራሹ ዘረኛ የግፍ አገዛዝ ሥር ሆና ዜጎች እንደ እንስሳ እየተገደሉ ባሉበት በዚህ ፈታኝ ወቅት፣ አስከፊውን ስርዓት ከስሩ ነቅለን ሕዝባችንን እና ሀገራችንን ለመታደግ ዛሬ ነገ የማይባልበት አጣዳፊ ጊዜ ላይ የደረስን በመሆኑ፤
ጠላት ሌት ተቀን ሥልጣኑን ለማራዘም በሽዎች እያሰረ፣ እያሰቃየና እየገደለ ባለበት ወቅት፣ ዝም ብለን በመቀመጥ ወይንም ወያኔ በሚፈፅመው ግፍ በማዘን እና በመቆጨት ብቻ ተጠምደን እያንዳንዳችን የቻልነውን ያህል ጠጠር ከመወርወር ከተቆጠብን ፣ “ነገ ሀገር እና ሕዝብ የሚባል ይኖረናል ወይ?” ብለን የምንጠይቅበት ደረጃ ላይ የደረስን በመሆኑ፣
በሀገር ቤት ያሉ ወገኖቻችን የእለት ጉሮሯቸውን ዘግተው እየተራቡ እና እየተጠሙ በሕዝባዊ እምቢተኝነቱ ዐውድ የሚያደርጉትን የሞት ሽረት ትግል፤ በውጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ወገን የበኩሉን እርምጃ በመውሰድ አጋርነቱን ማሳየቱ ትግሉን እንደሚያጎለብት የታመነበት በመሆኑ፣
ሀገራችን ኢትዮጵያን ለ25 ዓመታት በግፍ እንዲገዛ የኢኮኖሚው ጀርባ አጥንት ሆኖ ያገለገለው ከውጭ ሀገራት በተለያዬ መንገድ እና ምክንያት የሚገባው የውጭ ምንዛሬ በመሆኑና ከዚህም ዉስጥ በዉጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ለግንባታ፣ ለንግድ እና ለዘመዶቻቸዉ በባንክ በኩል የሚልኩት ህዋላ (remittance) ከፍተኛ ድርሻ ያለዉ በመሆኑ፣
በህዝባዊ እምቢተኝነቱ መቀጣጠል ምክንያት ወያኔ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ ውስጥ የገባ በመሆኑ እና ወደ ሀገር ቤት በተለያዬ ምክንያት በሚላከው የውጭ ምንዛሬ ላይ ውጤታማ ተአቅቦ ከተደረገ ሕወሓት መራሹን ዘረኛና ወንበዴያዊ አገዛዝ ውድቀት በእጅጉ የሚያፋጥነው በመሆኑ፣
እኛ ስማችን ከታች የተጠቀሰው የሲቪክ እና ፖለቲካ ድርጅቶች፤ ከላይ የተዘረዘሩቱን ወቅታዊ የሀገራችንን ሁኔታዎች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እና መነሻ በማድረግ፣ በውጭ የምንኖር፣ ፍትህ፣ እኩልነት እና ነፃነት ወዳድ ኢትዮጵያዊያን፣ በሕወሓት መራሹ ዘረኛ አገዛዝ ላይ የዉጭ ምንዛሬ ማዕቀብ እንድናደርግ ወገናዊ ጥሪ እናቀርባለን።

ከዚህ ‘ከዲሴምበር’ ወር ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ወራት የሚዘልቅ የአስቸኳይ ጊዜ የኢኮኖሚያዊ ማዕቀብ አዋጅ በማወጅ፣ ወደ ሃገር ቤት ለግንባታም ይሁን ለቤተሰብ ድጎማ የሚላከው የውጭ ምንዛሪ እንዳይላክ፣
የሦስት ወሩ አስቸኳይ የኢኮኖሚ ማእቀብ የጊዜ ገደብ ከተጠናቀቀ በኋላ፤ የስርዓቱን የገንዘብ አቅም የበለጠ ማሽመደመድ እንዲቻል፣ ቢያንስ ለስድስት ወር ያህል የሚላከው ገንዘብ በአንድ ሶስተኛ እንዲቀንስ ማድረግ። ይህም ማለት መቶ ዶላር የሚልክ ሰው ሰባ ዶላር እንዲልክ ወይም በአመት አምስት ጊዜ የሚልክ ሦስት ጊዜ ብቻ እንዲልክ ማድረግ፣
የማእቀቡ ጥሪ በተላለፈበት የጊዜ ገደብ ውስጥ የግድ ለቤተሰብም ይሁን ለሌላ ጉዳይ ገንዘብ መላክ ካለበት፤ ገንዘቡ ለስርዓቱ ሊደርስ የማይችልበትን መንገድ በምንኖርበት ከተማ በማፈላለግ ገንዘቡን መላክ። ይህ ማለት ከባንኮች እና ገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች እንዲሁም የወያኔ አባላት እና ደጋፊዎች ከሚቆጣሩት የአላላክ ዘዴ ውጭ የውጭ ምንዛሬውን መላክ።
ውድ ወገኖቻችን፣

ወያኔን የውጭ ምንዛሬ ማሳጣት በእጃችን ውስጥ ያለ የትግል መሳሪያ ስለሆነ ለተግባራዊ እርማጃ በመነሳት ኢትዮጵያዊ ግዴታችንን እንድንወጣ ለነፃነቱ እና ለእኩልነቱ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈለ ባለው የኢትዮጵያ ህዝብ ስም እንጠይቃለን።

ድል ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ!!

No automatic alt text available.
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s