አማራ ስለሆነክ አማራን ትወክላለህ ማለትም እኮ አይደለም!!!

No automatic alt text available.

ከብዙዎቹ አንዱ እንጂ ብዙዎቹ አይደለንም!! ችግራችን ከዚህ ይጀምራል። የአማራን ድምጽ ወይም አማራን ወክሎ ስለ አማራው ወኪል መሆን የሚቻለው፤ የአማራው ህዝብ ይወክለኛል ብሎ በድምጽ ለሚሰጠው አካል ብቻ ነው። ኦሮሞም ቢሆን እንዲሁ!!

ህወሃት ወያኔ ብአዴንን ወኪላችን ነው ብሎ ሲሰጠን የአማራ ህዝብ በብአዴን እንዳልተወከለ የአደባባይ ሚሰጥር ነው። የብአዴን መሪዎች አንዳቸውም ህወሃት በሚጠራው የይስሙላ ምርጫ እንኮን በታሪክ የተመረጡበት ጊዚያት የሉም።

ወደቁምነገሩ ስመለስ ሰሞኑን የትግል አቅጣጫን ለማስቀየር እንደህወሃት ሁሉ የዘር ካርድ በመምዘዝ የአማራው ትግል ለኦሮሞው ምኑ ነው? የአኦሮሞው ትግል ለአማራው ምኑ ነው? ወዘተ.. ትግሉን እኛ ነን የምንመራው…ወዘተ… አርበኞች ግንቦት 7 አማራን አገለለ.. ወዘተ.. አማራው ተደራጅ.. ወዘተ.. የአማራው ድርጅቶች 16 ደረሱ ወዘተ.. የአማራው ልሳን ሬዲዮ ህዝብ ጥሪ ስብሰባ ገንዘብ ያስፈልገናል ወዘተ… ዜማዎች ተበራክተዋል።

የሰለቸን ግን የድል አጥቢያ ድርጅቶችና ግለሰቦች እየተነሱ የትግሉ መሪህ እኛ ነን ና እኔ ነኝ የሚለው ነው።

የነጻነቱ ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ በአንድ ወቅት ከአሜሪካ ድምጽ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ላስታውስ። <ድርጅታችን ጊዚየውን እየገደለ ያለው አራትና አምስት እየሆኑ ድርጅቶች ነን ከሚሉ ሰዎች ጋር ለመጣመርና ለመወሃድ የሚያደርገው ሂደት ጊዚያችንን እያጠፋብን ነው> ያሉትን መሪ ነጥብ አሁን ላይ ሁኜ አስታወስኩት።

እናም በዚህ ረገድ አርበኞች ግንቦት 7 መወቀስ ካለበት በየጊዜው ከማህበራዊ ገፆች እና በየፓልቶኩ ከሚወለዱ የብሄር ድርጅቶች ጋር በማተኮር ጊዜውን በማጥፋት እነ እከሌ ቀሩ.. እነ እከሌ አሉ.. በታዛቢነት ይገኙ… ወዘተ እያለ የማርያም መቀነቱን ማብዛቱ ላይ ነው።

ከዚህ ባሻገር ግን አርበኞች ግንቦት 7 ለምትወቅሱ፡- ድርጅቱ የኢትዮጵያ ችግር የሚፈታው የእያንዳንዱ ዜጋ መብት ሲከበር ነው ቢልም የኢትዮጵያዊነቱን ብሄራዊ ድርጅትነቱን ውክልና የሚያገኘው ግን በህዝብ ሲመረጥ ብቻ ነው ።

ስለዚህ ገና የህዝብ ውክልናን ያላገኘን ድርጅት የእከሌና የእነ እከሌ ጠላት፣ እከሌን ዘነጋ..ወዘተ ማለት እንቶ ፈንቶ ነው ባይ ነኝ።

ማንኛውም ኢትዮጵያዊነቱን ለማስከበር በብሄር ድርጅት ገብቼ በአካባቢዪ የተደቀነብኝን አፈና በተግባራዊ ትግል እታገላለሁ ካለ ጥሩ ነው። ስለዚህ ድርጅት ከመፈጣጠር ይልቅ በአርበኞች ግንቦት 7 ገብተው የጋራ ትግሉን ማጠናከር የሚበረታታ ነበር። ነገር ግን ትግሉን ከወያኔ ላይ አንስተው የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የገቡት ምንም አይነት የአማራነት ውክልና ሳይኖራቸው አማራ ስለሆንኩ ብቻ የአማራ ህዝብ ወኪል ነኝ ብሎ ከበሮ መምታት መሰዋእትነት እየከፈሉ፣ ስለ ነፃነታቸው እየተዋደቁ ባሉ የአማራ ወጣቶች ላይ የመቀለድ ያህል ነው። ምንም እንኳ ትግል ብዕርንም ቢጨምር ቅሉ፤ አሁን ያለው ትግል ግን ከዛ ባለፈ የህይዎት መሰዋእትነትን እየጠየቀ በመሆኑ ብእራችን ለትግሉ የሚጠቅሙ ስልቶችን በመተየብ ልንጠቀምበት ይገባል እንጂ እኔ ከለለሁበት የሚል የቆዪ አይነት ቀለም መቀባባት ለአማራው ህዝብ አይጠቅምም።

ማናችንም ቢሆን የ45 ሚሊዮን የአማራው ህዝብ ውክልና የለንም!!! ከብዙዎቹ አንዱ መሆን እና በብዙሃኑ መወከል የተለያየ ነው።

እንደ አርበኞች ግንቦት 7 አባባል ይህን ውክልና ለማምጣት ወይም የዲሞክራሲያዊ ውክልና እንዲኖረን የሞት ሽረት የነፃነት ና የአንድነት ትግል እያደረግን ነው እንጂ በኢትዮጵያ ላይ ምንም አይነት ውክልና ገና የለንም የሚለው አራት ነጥብ ነው። ስለዚህ ማንንም የሚጠላበት አሊያም የሚኮነንበት ታምር አይኖርም።

በመጨረሻም በአንድ ወቅት ብልጭ እያላችሁ የምትጠፉ ድርጅቶች እንደዚህ አይነት የህዝብ ማአበል የእምቢተኝነት ትግል ባገረሸ ቁጥር ቀኝ አዝማች እየሆናችሁ ግራ አታጋቡ!!
ይህ ትግል የህዝብ ትግል ነው። የማንም የብእር ተያቢና የፓልቶክ አውሪዎች አይደለም!!! (ፓልቶክና ብእር ትየባን ለጥሩ ነገር የሚጠቀሙ በርካታ ሀገር ወዳዶች ብዙ ናቸው እንደ ኢካድፍ ያሉ)

እናም ባህርዳር፣ ጢስ አባይ፣ ጎንደር፣ ደብረታቦር፣ መራዊ፣ ኮሶበር፣ ማርቆስ፣ ዳንግላ፣ ቲሊሊ፣ መሸንቲ፣ ወረታ፣ እብናት፣ ፍኖተሰላም እና ዱርቤቴ ያለው ስለነጻነቱ የሚዋደቀው ህዝብ ማናችንንም እኛው ሁለት ሶስት ሆነን በውጪ የምንፈጥረውን ፡- ቤተ አማራ አንድ እና ሁለት፣ የአማራ ህዝብ ንቅናቄ፣ ሞረሸ ወገኔ፣ ዳግማዊ አማራ፣ የአማራ ህዝብ መድህን፣ የአማራ ወጣቶች ተጋድሎ፣ ጎህ አማራ፣ ዳግማዊ መዐህድ፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ እና ህብረት ወዘተረፈ…. አያውቀንም!!! ይሰማል!!! ነጻነቱን በሚፈሰው ደሙ ለማሰከበር ሲወድቅ በየበርሃው ሲወረወር እማማ ኢትዮጵያን እያለ እንጂ እናንተ የምትሰብኩትን የብሄር ካርድ እንዳልሆነ ልንግራችሁ እወዳለሁ!!! አሁንም ይሰማል!! ስለ አንድነቱ ነው እየተዋደቀ ያለው!!!

አማራው በታሪኩ እኔ እወክልሃለሁ በሚሉ ነቢያት የተኖረበት እንጂ፤ አማራው የሚወክለውን እንዲመርጥ እድል የተሰጠበት ጊዚያት የለም። ለዚህም ነው እምቢ ብሎ የተነሳው…

የአካባቢው ልጆች ስለሆንን ወይም በመሆናችን እና በውጪም በተሻለ የመረጃ አለም ስለምንኖር፣ በሀገር ውስጥ ያለው የአማራው ወገኔ በአማራው እየደረሰ ያለውን በደል ለአለም ተናገሩልን አሰሙልን በሚል የሚደርሰንን መረጃ በመለወጥ የአማራው ወኪል ነን ብለን መቅረብና ድምጻችንን አሰሙልን ሌላ ነው። ይህ ትግል መሰዋእትነት ይጠይቃል። ይህ ትግል አንድነትን ይጠይቃል!!! ጎንደር ላይ የኦሮሞው ደም ደሜ ነው ሲል የልዩነት እትብታችንን ቋጥሮልን ሄዶል። የቀረው የግለሰቦች የግል ፍላጎት ነው።

አምሳሉ ፀጋዪ

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s