የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች ለ49ኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

ዞን ዘጠኝ (Zone9)]

Zone 9 bloggers news trial

አምስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች፣ ሶልያና ሽመልስ (በሌለችበት)፣ በፍቃዱ ኃይሉ፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ አቤል ዋበላና ናትናኤል ፈለቀ ነገ አርብ ታኅሣሥ 21፣ 2009 ለመጨረሻ የይግባኝ ብይን ይቀርባሉ፡፡ ሰባት የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎችና ሦስት ጋዜጠኞች ከታሰሩበት ሚያዚያ 17፣ 2006 ጀምሮ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት እየቀረቡ ቆይተው አምስት ተከሳሾች ከሳሽ የፌደራል ዓቃቤ ሕግ ያቀረበውን ክስ አንስቻለሁ በማለቱ ሐምሌ 01፣ 2007 የተፈቱ ሲሆን አራቱ ተከሳሾች ደግሞ ነፃ ናቸው ተብለው ጥቅምት 5፣ 2008 ከእስር ተለቀዋል፡፡ የዞን ዘጠኝ ጦማሪ የሆነው በፍቃዱ ኃይሉም የቀረበበት ክስ ከፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ጋር የማይገናኝ በመሆኑ በመደበኛው የወንጀል ሕግ አንቀፅ 257/ሀ መሠረት በጽሑፍ አመፅ የመቀስቀስ መተላለፍን ፈፅሟል፣ ይሄንም ይከላከል ተብሎ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በጥቅምት 10፣ 2008 በተሰጠው ውሳኔ መሰረት በሃያ ሽሕ ብር ዋስትና ከእስር መለቀቁ ይታወቃል፡፡

ነገር ግን የፌደራል ማዕከል ዓቃቤ ሕግ በታሕሳስ 04፣ 2008 በተፃፈ ይግባኝ ‹በከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ቅር ተሰኝቻለሁ፣ ተከሳሾቹ በነፃ መሰናበት የለባቸውም› በማለት ባቀረበው ይግባኝ መሠረት ላለፉት ዐሥራ ሁለት ወራት በስር ፍርድ ቤት መከላከያ ማስረጃዎቹን አቅርቦ ቢጨርስም የመጨረሻ ውሳኔ ያልተሰጠበት በፍቃዱ ኃይሉን ጨምሮ አምስቱ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ችሎት በመቅረብ ክሳቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ሲሆን በነገው ዕለትም ለ49ኛ ጊዜ የስር ፍርድ ቤቱ ውሳኔን ለማፅናት ወይም ለመሻር በሚሰየመው ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፡፡ ፍርድ ቤቱ “ይከላከሉ” የሚል ውሳኔ ካሳለፈ መልሰው ሊታሰሩ እንደሚችል ተጠርጥሯል።

ጦማሪ በፍቃዱ ኃይሉ ጥቅምት 18፣ 2009 አየር ላይ ለዋለው የአሜሪካን ድምፅ (Voice of America) ‹የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አጥላልተሃል› በሚል አርብ ሕዳር 02፣ 2009 ከመኖሪያ ቤቱ ተይዞ ከታሰረ በኋላ “በተሐድሶ” ታኅሣሥ 13፣ 2009 ተፈትቶ ከቤተሰቡ መቀላቀሉ ይታወሳል።

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s