በምዕራብ ጐጃም ታላቁ የቅኔ ጉባኤ ቤት በእሳት ወደመ

ታላቁ የቅኔ ጉባኤ ቤት በእሳት ወደመ
ጥር ፰ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በምዕራብ ጐጃም ሀገረ ስብከት በቋሪት ወረዳ ቤተ ክህነት ልዩ ስሙ ፈንገጣ በሚባል ቀበሌ በጨጎዴ ሐና የተቋቋመው፤ ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንትን ሲያፈራ የኖረውና እስከ አሁን ድረስም ሊቃውንትን የመተካት ተልእኮውን በመወጣት ላይ የሚገኘው የሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራው የቅኔ ምስክር ጉባኤ ቤት ጥር ፯ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም ረፋድ ላይ ድንገት በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ወደመ፡፡
የጉባኤ ቤቱ መምህር ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራው ከከፊል ደቀ መዛሙርታቸው ጋር በቦታው የተገኙ የዓይን እማኞች እንደሚያስረዱት በአካባቢው ያለው የአየር ጠባይዕ ነፋሻ ከመኾኑ፣ ጉባኤ ቤቱ ከእንጨትና ከሣር ከመሠራቱ ባሻገር ደቀ መዛሙርቱ ለክብረ በዓል በወጡበትና የአካባቢው ሕዝበ ክርስቲያን ወደ ቤተ ክርስቲያን በሔዱበት ሰዓት ቃጠሎው መከሠቱ ጉዳቱን የከፋ አድርጎታል፡፡
ከማእከሉ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ጉባኤ ቤቱ ከአምስት መቶ እስከ ስድስት መቶ የሚደርሱ ደቀ መዛሙርት ይማሩበት የነበረ ሲኾን በአሁኑ ሰዓትም በከፊል ከቃጠሎው በተረፈው የጉባኤ ቤቱ ማኅበር ቤት ተጠልለው ይገኛሉ፡፡
በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ቤት ላይ በደረሰው ጉዳት ለጉባኤ ቤቱ መምህር ሊቀ ሊቃውንት ያሬድ ሽፈራው፣ ለደቀ መዛሙርቱና ለአካባቢው ሕዝበ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን መጽናናትን ይመኛል፡፡
በመጨረሻም ጉባኤ ቤቱን ወደ ነበረበት ህልውና ለመመለስ፤ ደቀ መዛሙርቱን ከመበተንና የጉባኤውን ወንበርም ከመታጠፍ ለመታደግ መላው ሕዝበ ክርስቲያን ድጋፋችሁ አይለየን ሲል ጉባኤ ቤቱ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
የእሳት ቃጠሎው ያደረሰው ጉዳት በከፊል
የተወደዳችሁ የድረ ገጻችን ተከታታዮች! የጉባኤ ቤቱን የአመሠራረት ታሪክና ከደረሰበት የቃጠሎ አደጋ ጋር የተያያዙ ተጨማሪ መረጃዎችን በሌላ ዝግጅት ይዘን እንደምንቀርብ ከወዲሁ እንገልጻለን፡፡
Image may contain: 40 people, outdoor
የጨጎዴ ሐና ቅኔ ጉባኤ ቤት ደቀ መዛሙርት በከፊል (ጉባኤ ቤቱ በእሳት ከመቃጠሉ በፊት)
Image may contain: outdoor, nature and water

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out / Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out / Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out / Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out / Change )

Connecting to %s