የመንግስት መስሪያ ቤቶች ገቢ እየተመናመነ እንደሚገኝ ተገለጸ

የኢትዮጵያ መንግስት ከማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አገኛለሁ ብሎ ያቀደውን የውጭ ምንዛሪ ሳያገኝ መቅረቱ ተገለጸ፡፡ በስድስት ወራት ውስጥ ከተጠቀሰው ዘርፍ 349 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ የነበረ ቢሆንም፣ ሊገኝ የቻለው ግን 198.5 ሚሊዮን ዶላር ብቻ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አህመድ አብተው ባቀረቡት ሪፖርት ላይ የስድስት ወራቱ የገቢ መጠን በመቶኛ ሲሰላ 56.5 በመቶ ብቻ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡


የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የበጀት ዓመቱን የስድስት ወራት ሪፖርት እያቀረቡ ቢሆንም፣ ሁሉም በሚያስብል መልኩ ከውጭ ንግድ ሊያገኙት ያቀዱትን የውጭ ምንዛሪ እያገኙ እንዳልሆነ በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡ በዚህም የተነሳ መንግስት በወጪ ንግድ ላይ ከተመሰረቱት መስሪያ ቤቶቹ ያጣው የውጭ ምንዛሪ፣ አስቀድሞ የነበረውን የውጭ ምንዛሪ እጥረት በእጥፍ እያባባሰው እንደሆነ ከመረጃዎች ለመረዳት ተችሏል፡፡

ከማኑፋክቸሪንግ በተጨማሪም የኢንዱስትሪ ምርቶች እያስገኙ የሚገኙት የውጭ ምንዛሬ ከታቀደው በታች ሲሆን፣ የጨርቃ ጨርቅ፣ የቆዳና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም የሥጋ የወጪ ንግድ ከታቀደላቸው በታች ውጤት በማስመዝገብ መንግስትን ለኪሳራ እንደዳረጉት ነው የተገለጸው፡፡ በዚኽኛው በጀት ዓመት ኪሳራ ያስመዘገቡት የመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ የመንግስትን ኢኮኖሚ በማቃወስ ለተጫማሪ በጀት ምደባ እንደዳረጉት ይታወቃል፡፡ አሁን ያለው የኢኮኖሚ ሁኔታም ጠኔኛ እንዳልሆነ የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡BBN

13819494_611651515666849_1114674654_n

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s