በወገራ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት

በወገራ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።

ከጎንደር ወደ ደባርቅ ከልክ በላይ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ (ሚኒባስ) ባለፈው ቅዳሜ አምባ ጊዮርጊስ ከተማ አቅራቢያ ወይላሆ በተባለ አካባቢ በመገልበጡ ነው የሰባት ዜጎች ህይወት የተጠቀፈው።

የወገራ ወረዳ ፖሊስ ፅህፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት ኢንስፔክተር ደርሶ ስንታየሁ እንደገለጹት፥ በፍጥነት ሲጓዝ የነበረው ተሽከርካሪ ሊገለበጥ የቻለው አሽከርካሪው መንገድ ላይ የገባበትን አህያ ለማዳን ሲሞክር ነው።

ከሟቾቹ በተጨማሪ 14 ተሳፋሪዎችም ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፥ የሟቾቹ ቁጥር ከዚህም ሊያሻቅብ ይችላል ተብሏል።

ከሟቾቹ ውስጥ ሁለቱ ህፃናት ሲሆኑ፥ ከቆሰሉት መካከልም ሶስት ህፃናት ይገኙበታል።

ከሁለት ልጆቻቸው ጋር ሲጓዙ የነበሩ እናትም ልጆቻቸውን በሞት ሲያጡ እርሳቸው ጉዳት ደርሶባቸዋል።

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s