‹‹ሸራተን ከ5 ኮከብ በላይ ይገባኛል አለ››

Image may contain: sky and outdoor

በቅርቡ ይፋ በተደረገው የአዲስ አበባ ሆቴሎች የኮከብ ደረጃ ምደባ ሸራተን አዲስ፣ ኢሊሊ ዓለም አቀፍ ሆቴልና ካፒታል ሆቴልና ስፓ፤ 5 ኮከብ የተሰጣቸው ሲሆን ሸራተን አዲስን ጨምሮ 20 ሆቴሎች በኮከብ አሰጣጡ ላይ ቅሬታ አቅርበው ምላሽ እየተጣበበቁ ነው፡፡
ባለ 5 ኮከብ ደረጃ ይሰጣቸዋል ተብሎ የተጠበቁት ሂልተን አዲስና ራዲሰን ብሉ ሆቴል ባለ 4 ኮከብ ሆነዋል፡፡
5 ኮከብ የተቀዳጁት ኢሊሊ እና ካፒታል ሆቴል በተሰጣቸው ደረጃ ደስተኛ መሆናቸውን የገለፁ ሲሆን ሸራተን አዲስ ግን ከ5 ኮከብ በላይ ይገባኛል የሚል ጥያቄ አቅርቧል፡፡
ካፒታል ሆቴል 12 በሚደርሱ መስፈርቶች መመዘኑን የጠቆሙት የሆቴሉ ሴልስና ማርኬቲንግ ማናጀር አቶ ሚካኤል ተካ፤ ከመቶ 85.68 በማግኘትም ባለ 5 ኮከብ ሆቴል ለመሆን መብቃቱን ገልፀዋል፡፡ ሆቴላችን የ5 ኮከብ ባለቤት መሆኑ በአለማቀፍ ደረጃ ያለው ተቀባይነት እንዲጨምርና ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲዘልቅ ይረዳዋል ያሉት ማናጀሩ፤ ሆቴሉ ወደፊት ሊጀምር ያቀዳቸው ሌሎች አገልግሎቶች ሲሟሉ፣ ወደ “ግራንድ ሌግዠሪ” ደረጃ ማደግ እንደሚችል መዛኞቹ መጠቆማቸውን ተናግረዋል፡፡
የኮከብ ደረጃ ከተሰጣቸው መካከልም 3ቱ ባለ 5 ኮከብ 11ዱ ባለ 4፣ 13ቱ ባለ 3፣ 10ሩ ባለ 2 ኮከብ ደረጃ ሲያገኙ አንድ ሆቴል ባለ 1 ኮከብ ደረጃ ተሰጥቶታል፡፡ ለሁሉም ሆቴሎች ተመሳሳይ 12 የመመዘኛ ነጥቦች የተዘጋጁ ሲሆን ባገኙት የመቶኛ ውጤት መሠረት ደረጃው ተሰጥቷቸዋል ተብሏል፡፡ የሆቴሎች የኮከብ ደረጃ ምዘናው ከተጀመረ 5 ወራት ገደማ ያስቆጠረ ሲሆን በአሁን ወቅት በክልል ከተሞች ለሚገኙ ሆቴሎች ተመሳሳይ የምዘና ሥራ እየተከናወነ እንደሆነ ከባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የሆቴል ምዘናው የሚከናወነው በተባበሩት መንግስታት የአለም ቱሪዝም ድርጅት ሲሆን ለስራው የሚውለው በጀት የተገኘው ከአለማቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) እንደሆነም ታውቋል፡፡
ምንጭ፡ አዲስ አድማስ

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s