ሰበር ዜና – በዝቋላ ቃጠሎ ወቅት ወድቆ የተጎዳው ወጣት ሸገና ሉሉ(ወልደ ዮሐንስ) ዐረፈ

በዝቋላ ቃጠሎ ,አዱላላ ,ወጣት

Advertisements
  • ለከፍተኛ ሕክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ተልኮ ርዳታ እየተደረገለት ነበር፤
  • አስከሬኑ ከሆስፒታሉ ወጥቶ፣ ድሬ ወደሚገኙት ቤተሰቦቹ እየተጓጓዘ ነው፤
  • የቀብር ሥነ ሥርዓቱ፣ ሰኞ፣ መጋቢት 4 ቀን በትውልድ ስፍራው ይፈጸማል፤

*                    *                    *

17155372_1689427188023769_8239244954073712111_n[1]

17265267_1818455838429085_2788959503118677550_n[1]
Ziquala monastry pilgrims to chase the fire

ፎቶ: ፋይል

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት፣ ሊበን ወረዳ፣ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ፣ ትላንት፣ መጋቢት 1 ቀን 2009 ዓ.ም. ከቀትር በኋላ የተቀሰቀሰውን እሳት ለማጥፋት ሌሊቱን ሲረባረቡ ከነበሩት ምእመናን አንዱ የነበረው ወጣት ሸገና ሉሉ(ወስመ ጥምቀቱ ወልደ ዮሐንስ) ዐረፈ፡፡

ለወጣቱ የተጋድሎ ላይ ኅልፈት መንሥኤ የኾነው፣ እሳቱ በተቀሰቀሰበት ስፍራ ባለ ገደል ሲወድቅ ጭንቅላቱ ላይ በደረሰበት ጉዳት የውስጥ ደም መፍሰስ ስላጋጠመው መኾኑን የስፍራው ምንጮች ተናግረዋል፡፡

ሌሊት ላይ ወድቆ ከቆየበት ስፍራ፣ አብረውት በሔዱት ምእመናን ርዳታ ንጋት ላይ ከተገኘ በኋላ፣ በአዱላላ ጤና ጣቢያ የመጀመሪያ ደረጃ ርዳታ ተደርጎለት፣ ወደ ደብረ ዘይት ሆስፒታል ተወስዶ ነበር፤ ይኹንና ጉዳቱ ከፍተኛ በመኾኑ ለተሻለ ሕክምና ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በሪፈር ተልኮ የሕክምና ክትትል እየተደረገለት ሳለ ሕይወቱ ማለፉን ለመረዳት ተችሏል፡፡

ቃጠሎውን በጥብዐት ከተጋፈጡት ምእመናን አንዱ የነበረው ወጣቱ፣ በአኹን ሰዓት፣ አስከሬኑ ከሆስፒታሉ ወጥቶ፣ ድሬ(በደብረ ዘይትና በአዱላላ መሀል የምትገኝ ከተማ) እየተሸኘ መኾኑ ተገልጧል፤ ኦርቶዶክሳዊው ወጣት፣ በደብረ ዘይት ሪፍት ቫሊ ኮሌጅ ትምህርቱን በመከታተል ላይ ነበር፡፡

በአኹኑ ወቅት፣ የተቀሰቀሰው እሳት ሙሉ በሙሉ ባይጠፋም፣ እንደ ኦርቶዶክሳዊው ወጣት፣ ሸገና ሉሉ (ወልደ ዮሐንስ) ባሉት ምእመናን የሌት ተቀን ጥረት፣ ተጨማሪ ጉዳት በማያደርስበትና አስጊ በማይኾንበት ደረጃ መስፋፋቱን ለመግታት መቻሉ እየተነገረ ነው፤ ቀትር ላይ በአራት አይሱዙ መኪኖች ተጓጉዘው የደረሱት የአዱላላ ነዋሪዎች ርብርብም ከፍተኛውን አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s