ዝቋላ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ የተነሳው ሰደድ እሳት ዛሬ ከሰዓት በኋላ በቁጥጥር ስር ውሏል

ዝቋላ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም ,ሰደድ እሳት, fire brokout on Monastery

Advertisements

በደብረ ከዋክብት ዝቋላ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ የተነሳው ሰደድ እሳት ዛሬ ከሰዓት በኋላ የቤተክርስቲያን የቁርጥ ቀን ልጆች በሆኑ የቤተክርስቲያን ልጆች እንዲሁም በመከላከያ ሰራዊት የተቀናጀ ጥረት በቁጥጥር ስር ውሏል እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን።


እሳቱን በማጥፋት ላይ ከነበሩት ወጣቶች መሀከል የአንድ ወንድማችን ወጣት ህይወት ያለፈ ሲሆን ነፍሱን በአፀደ ገነት በደጋግ አባቶቻችን አጠገብ ያሳርፍልን ጻዲቁ ለነፍሱ ዋስ ጠበቃ ይሁኑለት።እሳቱን ለማጥፋት የተባበራችሁትን ምንም ሳይበግራችሁ ያንን ከባድ ዳገት ጋራ ወጥታችሁ እሳቱን ተጋፍጣችሁ ገዳሙን የታደጋችሁ በሙሉ ጻዲቁ ይታደጉዋችሁ እግዚአብሔር ይጠብቃችሁ።
ተዋህዶ ለዘላለም ትኑር።
ጠላት ይፈር
ዲያብሎስ ይዋረድ
የተዋህዶ ልጆች ለዘላለም እንደ ከዋክብት ሲያበሩ ይኑሩ።
የፊታችን እለተ ማክሰኞ መጋቢት 5 የሚከበረው የጻዲቁ አባታችን ከአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ በዓለ እረፍት ረድኤት በረከት ያሳትፈን።
ምንጭ፦ ሄኖክ ተፈራ

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s