ዳሬ ሰላም፤ታንዛኒያ 500 ዶክተሮች ወደ ኬንያ ልትልክ ነው

የኬንያ የሕክምና ባለሙያዎች አድማ በመንግሥት ሆስፒታሎች የፈጠረውን እክል ለመቅረፍ ታንዛኒያ 500 ዶክተሮች ለጎረቤቷ እንደምትልክ የፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት ዛሬ አስታወቀ። የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ የኬንያው የጤና ጥበቃ ሚኒሥትር ክሌዎፓስ ማይሉ ያቀረቡትን የእገዛ ጥያቄ መቀበላቸውን ሬውተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። ፕሬዝዳንት ማጉፉሊ «የኬንያ ችግር የታንዛኒያም ችግር ነው» ብለው መናገራቸውም ተጠቅሷል። ኬንያ ለታንዛንያውያኑ የሕክምና ዶክተሮች ወርሐዊ ደሞዝ እንደምትከፍል እና የመኖሪያ ቤት እንደምትሰጥ ከፕሬዝዳንቱ ጽ/ቤት የወጣው መግለጫ አትቷል። የታንዛኒያው የጤና ጥበቃ ሚኒሥትር ኡሚ ምዋሊሙ አገራቸው በርካታ ብቁ ግን ደግሞ ሥራ አጥ የህክምና ዶክተሮች እንዳሏት መግለጣቸውን ሬውተርስ ዘግቧል። የደሞዝ ጭማሪ እና የተሻለ የሥራ ሁኔታ የጠየቁ የኬንያ ዶክተሮች ካለፈው ታኅሳስ ወር ጀምሮ የሥራ ማቆም አድማ ላይ ናቸው። በዚህ ሳምንት ከኬንያ መንግሥት ጋር የደረሱበት ሥምምነት ለሥራ ማቆም አድማው መፍትሔ ለመፈለግ የድርድር መንገድ ይከፍታል ቢባልም አብዛኞቹ ዶክተሮች ወደ ሥራ ገበታቸው አልተመለሱም። የሥራ ማቆም አድማው በመጪው ነሐሴ ፕሬዝዳንት ኡሑሩ ኬንያታ ለሁለተኛ የሥልጣን ዘመን ለመመረጥ በሚያደርጉት ጥረት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይኖረዋል ተብሏል።

africa-eth-col

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s