መምህር ዘመድኩን በቀለ “ሰከን በል” – ሰባኪዎችን እና መዘምራንን ከወያኔ ጋር ተባብረህ ማስፈራራትህን አቁም አለዚያ ተራው ያንተ ነው

 አቤል ዮሐንስ ከዳላስ
ይህን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ እጅግ በተሰበረ አንደበት በቭዲዮ (Video) ያስተላለፈውን መልዕክት ከተመለከትኩ በኋላ ነው:: ለዚህ ድንቅ ዘማሪና አስተማሪ መፍራትና ልብ መሰበር ዋነኛው ተጠያቂ ደግሞ ጀርመን ሃገር በስደት ገባሁ ያለው የወያኔው መልዕክተኛ ዘመድኩን በቀለ ነው::zemedkun-768x768

ዘመድኩን በቀለ ከቲያንስ ኢትዮጵያ ጋር በተያያዘ የሠራቸውን ሥራዎች በቀጣይ የምመለስበት ይሆናል:: ሆኖም ግን አንድ ጣትህን ወደ ሰው ስትዘረጋ አራቱ ወደ አንተ እንደሚዘረጉ አስተውል በሚለው መሠረት ዛሬ በፌስቡክ ገጹ ዘማሪዎችን እና ሰባኪዎችን የሚያስፈራረውና እንደፈለገ ስም የሚሰጠውን ዘመድኩን በቀለን ማንነቱን በተከታታይ አዝረከርከዋለሁ::
እንደ አለመታደል ሆኖ ወያኔ በፈጠረው የፖለቲካ ልዩነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፈተና ውስጥ ከወደቀች ሰንብታለች:: የቤተክርስቲያን አንድነት እንዲመለስ በተለያዩ ቦታዎች የሚሰሩ ጥሩ ጥሩ ኦሮዶክስታውያን እንዳሉ ሳይዘነጋ:: እነዚህ የተዋሕዶ ልጆች በዲያስፖራው በጎራቸው በቆሙት በሃገር ቤቱ ሲኖዶስ በሚመራው; በገለልተኛውና በስደተኛው ሲኖዶስ በሚመራው አብያተክርሲያናት በመሄድ አባቶችን ያነጋግራሉ ያስቀድሳሉ ይማራሉ::
እነዚህ በ3 ጎራ በቆሙት ኦርቶዶክስ ውስጥ የሃይማኖት ልዩነት የለም:: ሆኖም ግን እንደዘመድኩን በቀለና በኒዮርክና አካባቢዋ ያሉት አብያተ ክርስቲያናት ሊቀጳጳስ አቡነ ዘካሪያስ ም ዕመናንን በመከፋፈል ኪሳቸውን በገንዘብ ሲያደልቡ መመልከት ያሳምማል:: ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዘካሪያስ ሃገር ቤት በጎደለ ገንዘብ እና በዚያም ሰበብ የሰው ሕይወት ጠፍቷል ስለሚባል ወደ ኢትዮጵያ ሄደው ከቅዱስ ፓትሪያርኩ አንድም ቀን ቡራኬ ተቀብለው አያውቁም:: የሙስናውን ክስና ሌሎችንም የሚያውቀው ዘመድኩን ዛሬ ከሊቀጳጳሱ ጋር በመመሳጠር በፌስቡ የዘማሪያንን እና ሰባኪያንን ስም በማጥፋት ላይ ይገኛል::
ዘመድኩን ሃገር ቤት በሚኖርበት ወቅት በሚያስተዳድረው መዝሙር ቤት ሲዲ ያላሳተሙ ዘማሪዎችን “ተሃድሶ’ ናቸው በማለት ስም በማጥፋት ይታወቃል:: በዚህም የተነሳ ብዙዎቹ ዘማሪዎች ከርሱ ጋር መስራት አይፈልጉም:: ከበጋሻው ጋርም ያጣላቸው መጀመሪያ ይኸው ነው:: አንዲት ዘማሪት ሲዲ ጌልገላ መንፈሳዊ መዝሙር ቤት ስታወጣ ይሄና በጋሻውን “ቤት እየሰራሁ ስለሆነ ገንዘብ ስለሌለኝ በነጻ ድምጽህን በማስገባት እርዳኝ” ሲል ይጠይቀዋል:: ከዚያ በፊት ብዙ ሥራ አሰርቶ ስላልከፈለው በጋሻው እምቢ ይለዋል:: የዚህን ጊዜ ዘመድኩን “ተሃድሶ ነህ’ ብዬ ስምህን አጠፋዋለሁ ብሎ እስካሁን ስሙን በማጥፋት ላይ ይገኛል::
ውጭ ሃገር ድረስ ለህክምና የሄደውና “ቋንቋዬ ነሽ” እያለ ስለሚዘምረው ዘማሪ ጉዳይ ያሉ ምስጢራዊ ጉዳዮችን እንዲሁም ሌሎችን በቀጣይ የማጋልጥ ሲሆን አሁን ግን በሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ ላይ የፈጸመውን ማስፈራራትና ስም ማጣፋት ላጋልጥ::

screen-shot-2017-03-15-at-7-54-12-pm

ወያኔ በዲያስፖራ ውስጥ ያለበትን የፖለቲካ ኪሳራ ለማካካስ ቤተከርስቲያንን መያዝ ይፈልጋል:: ለዚህም በገለልተኛው እና በስደተኛው ሲኖዶስ ያሉ ቤተክርስቲያናትን በ እጁ ማስገባት ነው ዋና አላማው:: በተለይ በስደተኛው ሲኖዶስና በገለለተኛው ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ ም ዕመናን ናቸው ዲያስፖራውን እንዳልቆጣጠረው ያደረጉኝ ብሎ ያምናል:: እነዚህን ቤተክርስቲያናት ለማዳከምና ለመያዝ ያልፈነቀለው ወይም የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም:: እናም ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ ምዕመናን አማካኝነት ወደ አሜሪካ አገልግሎት እንዲሰጥ ነበር የተጋበዘው:: የዳላሱ ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ በሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ስር ያለ አይደለም:: አቡነ ዘካሪያስ ይህን ቤተክርስቲያን በሃገር ቤቱ ሲኖዶስ ስር ለማስገባት ያልፈጸሙት ሴራ አልነበረም:: እነ መጋቤ ሃዲስ ጨምሮ በርከት ያሉ የተከበሩ የሃይማኖት ሰዎች ሄደው የ እግዚአብሄርን ቃል በማስተማራቸው በኚሁ ሊቀጳጳስ አማካኝነት እግድና ውግዘት ደርሶባቸው ነበር:: ወደዚህ ቤተክርስቲያን ዘማሪዎችም ሆነ ሰባኪያን እንዳይሄዱ በማከላከል በ እግድ ስም አሳፋሪ ሥራ የሚሰሩ ሊቀጳጳስ ናቸው አቡነ ዘካሪያስ::
ሰው የፈለገው ቤተክርስቲያን ይሂድ እንዴት በዚህ ዘመን የ እግዚአብሄርን ቃል አትስማ? አትማር ይባላል? እኚህ አባት ም ዕመናንን ቀስ በቀስ እንደማስማማት ገና ለገና መንፈሳዊ ስልጣን አለኝ በሚል ወደ ሰሜን አሜሪካ ለመጣ ዘማሪና ሰባኪ ሁሉ የ እግድና ውግዘት ደብዳቤ መጻፉ ምን ይሉታል? የርሳቸው ጉዳይ ብዙ የሚባልበት ቢሆንም እንደዘመድኩን ያሉ አንዴ በኢሳት ራድዮ እየቀረቡ ወያኔን አወግዛለሁ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሙስና አለ የሚሉ አስመሳይ ወያኔዎች ከኚሁ አባት ጋር በመተባበር ዘማሪዎቹንም ሆነ ሰባኪዎቹን ሲያስፈራሩና ሲያጓጥጡ ማየት ያማል:: (በነገራችን ላይ በመምህር ምህረተአብ ላይም ዘመቻውን ቀጥሏል)::
ለማንኛውም ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ በዳላስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ካገለገለ በኋላ በነዘመድኩን በቀለ በደረሰበት ስድብና ማንጓጠጥ እንዲሁም በ ዕምነቱ ላይ ላደረሱበት መገለል ሲል ወደ ሃገሬ እመለሳለሁ ብሏል:: በአሜሪካ የትኛውም ከተማ ሄጄ አልሰብክም አልዘምርምም ብሏል:: ማን ተጎዳ? – የ እግዚአብሄርን ቃል መስማት የሚፈልጉት ምዕመናን:: ማን አሸነፈ? እነዘመድኩን እና አቡነ ዘካሪያስ በቤተክርስቲያን ም ዕመናን ላይ ቁማር የሚጫወቱት::
በቀጣይ ጽሑፌ እንገናኝ::
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s