የትላንት መነኩሴ የዛሬ ፓስተር በአደባባይ ሲጋለጥ የምስራች ሰበር ዜና.!

ሁሉም ኦርቶዶክሳዊ ወጣት መረጃው እንዲደርሰው Share ~Share~Share~
17361735_1030396897103738_8320381787133007480_n
17353464_1030396883770406_1958990634190049193_n
✔ቤተክርስቲያንን መብቷን ለማስከበር ወጣቶች ተደራጅተው መንቀሳቀስ ጀመሩ ።
✔ አሁንም የሚዘገንኑ የመነኮሳት ፣ የዘማሪያንና የሰባኪያን ድብቅ ሴራዎችን የሚያሳዩ ቪድዮዎችና ፎቶግራፎች እንዲሁም አስጸያፊ የስልክ ልውውጦችና ዶክመንቶች በገፍ ከእጄ እየገቡ ነው ። እግዚኦ አቤት አረ በእመቤቴ እኔ መፈንዳቴ ነው ጓደኞቼ ። አቤት ስንቱን ችላ ተቀምጣለች ቅድስት ቤተክርስቲያን ። አቤት እግዚኦ.!
✔ የጆሃንስበርግ ወጣቶች ኮራንባችሁ ።
✔ተነሳ ወገን ተነሳ.! እያልን አዲሱን የመምህር ምህረተአብ መዝሙር እየዘመርን ልንነሳ ግድ ይለናል ።
✔ ሃይማኖት አሰዳቢና ተልካሻ ቦታ የሚገኙ መነኮሳት ፣ ካህናት ፣ ዲያቆናት ፣ ሰባኪያነ ወንጌልና ዘማርያን ላይ ምእመኑ የማጽዳት ሥራ እንዲጀምር ተጠየቀ ።
ራሱን ቆሞስ አባ ተክለማርያም በማለት ሲጠራ የከረመው እና አሁን መቀመጫውን በደቡብ አፍሪካ ያደረገው ግለሰብ በጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓተ እምነትና ዶግማ ላይ ሲያላግጥ የሚያሳይ ቪዲዮን መልቀቄን ተከትሎ የስልኬ ቀፎ ግሎ ቀጥ እስኪል ድረስ በመላው ዓለም ከሚኖሩ የተቆጡ የተዋህዶ ልጆች ይደርሱኝ የነበሩት መልእክቶች በእጅጉ የሚያኮሩ የሚያስደስቱና የሚያኮሩ ነበሩ ።
ከዚሁ ጋር ተያይዞ እዚያው ደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ የእምዬ የዋህዶ ልጆችም ለእኔ በመደወል ምን ማድረግ እንዳለባቸው በሰፊው የሚያረካ ውይይት አድርገን በቀጣይ ማድረግ ስላለብን እርምጃዎች ውሳኔዎችን አሳልፈን የሥራ ምድባችንንም ተከፋፍለን በቀጠሮ ተለያይተናል ። እኔ ከጀርመን ከራየን ወንዝ ማዶ ሆኜ እነሱ ደቡብ አፍሪካ ከማንዴላ ሀገር ሆነው ሥራ ጀምረናል ። ደስስ ሲል ።
በዚሁም መሠረት ይሄ ቀሳጢና በቅዱሳኑ በእነ አባ እንጦስ ፣ በእነ አባ መቃርስ ፣ በእነ ጻድቁ አባ ተክለ ሃይማኖት ፣ በአቡነ አረጋዊ በቅድስት ክርስቶስ ሰምራ አስኬማና ቆብ የቀለደውና ያላገጠውን መናፍቅ ሰው ያለበትን ቦታ ፈልጎ ማግኘት እና ቀሳጢውን ያስጠጋውን ፓስተር ደውሎ ማነጋገር በሚለው ተነጋግረን ከዚያም በቀጣይ ስለሚሆነው ነገር ይህን መነሻ በማድረግ ወደ ቀጣዩ እርምጃ እንደምንሄድም በወሰነው ውሳኔ መሠረት ይኸው በትላንትናው እለት ተፈጻሚ ሆኗል ።
እኒሁ በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ከተማ በሚገኘው ጽርሐ ጽዮን መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የሚገኙት ማኅበረ ምዕመናን በትናንትናው ዕለት በደቡብ አፍሪካ ይህን ድንቅ ተግባር በኢስት ጌት ሞል ከቀኑ 9 ሰዓት እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ በመጠበቅ ድንቅ የሆነ ተጋድሎ ፈጽመዋል ።
እልህ ፣ ቁጣ ፣ እና አካላዊ ጥቃት እንዳይፈጸም አስቀድመን በወሰንነው ውሳኔ መሠረት ከሃዲውን በአካል ሲያዩት ራሳቸውን መቆጣጠር ያቃታቸው ወጣቶች ቢኖሩም በተረጋጋ ሁኔታ የሚፈለገውን ተልእኮና ተጋድሎ በድል ፈጽመው ተመልሰዋል ።
አሁን በቀጣይ ይህንን መነኩሴ ነኝ ባይ በገንዘብ አባብሎና ደልሎ ያስኮበለለውን ፖስተር ኢዩኤልን በመጥራት እስከሰኞ ድረስ የሚደንቅና በሀገር ቤትም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጪ ለሚገኙ ወጣቶች ትልቅ መልእክት የሚያስተላልፍ ተግባር ለመፈጸም ተስማምተው ተለያይተዋል ።
በቀጣይ የሚፈጸሙ ተግባራት ።
፩ኛ፦ ቀሳጢው መነኩሴ ነኝ ባይ የተከበረውን የተክለሃይማኖትን አስኬማና ቆብ ከነመስቀሉና ፈረጅያው ከተቻለ ለሀገረ ስብከቱ ሊቀጳጳስ እንዲያስረክብ ። ሊቀጳጳሱ ጋር ለመድረስ የማይመች ከሆነ ደግሞ ትናንት አብረው ከወጣቶቹ ጋር እሱን ለማነጋገር ለሄዱት ካህን በክብር እንዲያስረክብና እሱ ወደ ዋና ቁምጣ መልበሱ መሄድ መብቱ እንደሆነ ነግሮ መለየት ።
፪ኛ፦ በመጀመሪያ ስለድፍረቱ ያሳዘነውን መላውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ልጆችን ይቅርታ በግልጽ እንዲጠይቅ ።

፫ኛ፦ በኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ እምነታችን ላይ ይሄንን ከሃዲ ሰው ራሱ በከፈተው ቸርች ውስጥ መድረክ ሰጥቶ በግልጽ እንዲህ አፉን እንዲከፍት የፈቀደውን ” ቅባታሙ ፓስተር ” ፓስተር ኢዩኤልም ለጥፋቱ ግልጽ ይቅርታ እንዲጠይቅ ብቻ ሳይሆን በተመሳሳይ ሁኔታ መሰል ጥፋት ፈጽሞ ቢገኝ ለሁሉም ሰው መልካም ያልሆነ ሁኔታ እንደሚፈጸም ተነጋግረው የደቡብ አፍሪካ የእምዬ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች የሚያኮራ ተግባር ፈጽመዋል ።

እንግዲህ ቅዱስ ሲኖዶሳችን ቤተክርስቲያንን ለማስከበር ምንም አይነት እንቅስቃሴ የማያደርግ ከሆነ የቤተክርስቲያን ልጆች አይናቸን እያየ ሀገራችንም ሃይማኖታችንም ሲጠፉ ማየት ያለብን አይመስለኝም ።
በኢትዮጵያ አሁን በግልጽ እንደሚታየው አቦይ ስብሐት ነጋ እንደነገሩን የኦርቶዶክስን አከርካሪ ለመስበር ፕሮቴስታንቶችና ሙስሊሞችን በሙሉ መንበረ ስልጣኑን እንዲይዙ አድርገዋል ። በኦሮምያና በደቡብ በግልጽ ኦርቶዶክስተዋህዶ እምነት ተከታይ መሆን ከማኅበራዊ ህይወት የሚያስገልል እንዲሆን ተደርጓል ። ሌላው ቢቀር ፕሮቴስታንቶች በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ቁልፍ የሆኑ ሥፍራዎችን እንዲይዙ ተደርጓል ። ለምሳሌ የፓትርያርክ አባ ማትያስ የውጭ ግኑኝነት ኃላፊው አባ በአሜሪካን የሰው ሚስት አማግጦ የተባረረ ሰው ሲሆን አሁን ግን መንግሥት ለተለየ ጥፋት የቅዱስነታቸው የውጭ ረዳት አድርጎ ሾሞታል ። ሌላው የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሥራ አስኪያጅ የሆነው አቶ ጎይቶም በግልጽ የምንፍቅና አራማጅና በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ቁልፍ የሆነ ሥልጣን በማግኘት መንግሥት በፖሊሲ ደረጃ ሊያፈርሳት እቅድ ለያዘላት ቤተክርስቲያን የሾመባት ክፉ ሰው ነው ። አሁን ጎይቶም የቃለ ዓዋዲውን አገልጋይ የፓስተር አሰግድን አሽከር መኳንንትን በአያት ኪዳነምህረት በመሾም ተልእኮውን በደንብ እየተወጣ ይገኛል ።
እናም ወገኖቼ ልንነቃና ልንነሳ ይገባናል ። በእኛ ዘመን ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ሃይማኖታችን ፈረሰች የሚል ጥቁር ታሪክ እንዲጻፍብን አንፍቀድ ።
በቀጣይ ማድረግ ስላለብን ነገሮች በግልጽ መወያየትና እርምጃ መውሰድ እንጀምራለን ።
፩ኛ፦ የመነኩሴ መኖሪያው ከተማ አይደለም ። እናም መነኮሳትን ወደ በአታቸው መመለስ ። የጣመ የላመ በመልመዳቸው ምክንያት አይ አንመለስም የሚሉ ከሆነ ደግሞ አስኬማና ቆቡን መልሰው እንደማንኛውም ዜጋ በላባቸው በወዛቸው እየሠሩ እንዲኖሩ ማድረግ ።
፪ኛ፦ በየ መጠጥ ቤቱ የተክልዬን አስከፀማ አድርገው ባለጌ ወንበር ላይ ተቀምጠው የጋለሞታና የሴተኛ አዳሪ መቀመጫ ቸብ እያደረጉ ልቅ የዝሙት ተግባር በመፈጸም ተዋህዶ ሃይማኖታችንን ሰድበው ለሰዳቢ የሚሰጡትን ልክ ማስገባትና ሃይማኖታችንን ማስከበር ። እዚህ ላይ እንዲህ አይነት ተግባር የሚፈጽሙ ሰዎች ገና አባ እዚህ ምን ይሰራሉ ስትሏቸው ምን አገባህ ብለው ፍልጥ የሚያክል ማካሮቭ ሽጉጥ ታጥቀው የሚዞሩ ወንበዴዎች ስለሆኑ ጥንቃቄ ማድረግኣና ለዚሁም ተመጣጣኝ ዝግጅት ማድረግ ያስፈልጋል ።
፫ኛ ፦ በመኪናና ድለላና ሽያጭ ፣ ከተለያዩ ሴቶች ጋር በየ ቤርጎው የሚልከሰከሱትን መነኮሳት አደብ ማስገዛት ።
ይህንና ይህን የመሳሰለውን ተግባር በሚፈጽሙ ዘማውያን አምቡላ ገፊና የሃይማኖት አሰዳቢ የከተማ አውደልዳይ ወደል መነኩሴ ነኝ ባዩን ሁሉ ልክ በማስገባት ሃይማኖታችንን ማስከበር ይቻላል ። እንዲህ ማድረግ ደግሞ መብታችን ነው።
መነኩሴ ወደ ከተማ የሚገባው ለአስተዳደራዊ ስራ ብቻ እንጂ በቆቡ ተከልሎ እየነገደ እና እያስነገደ ተንደላቅቆ እንዲኖር አልተፈቀደለትም ።
መነኩሴ ለየትኛውም ምእመን የንስሐ አባት እንዲሆንም የሚያዝ የሥርዓት መጽሐፍ የለም ። የሴት ድምጽ ካለበት ስፍራ ርቆ እንዲቀመጥ እንጂ የሴት መንጋ እያግተለተለ በብቱ ስር ከቶ እንዲዞር የሚያዝ ህግም የለም ። የንስሐ አባት መሆን የሚችለው ካህን ብቻ ነው ። የባልና የሚስትን ጣጣና ችግር ለመፍታት ችሎታውም አቅሙም ልምዱም ያለው ካህን እንጂ መነኩሴ አያገባውም ። አራት ነጥብ ።
በዚህ በኩል የኤርትራ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን 1 ሚልየን እጥፍ በልጣናለች ። ከካህናት በቀር አንድም የኤርትራና የግብጽ መነኮስ በከተማ አያውደለድልም ። በገዳሙ ተከትቶ በዚያ ለሀገር ለወገን ይጸልያል እንጂ ። እንደኛ መነኮሳት የፓርቲ አባል ሆነው ፣ ደላላ ሆነው ፣ ኢንቨስተር ሆነው ፣ ወልደውና ከብደው የሚኖሩ ደፋሮች አይደሉም ።
በጎደለ ይቀራል የምትሉትን እናንተው ሙሉበት ። እንወያይ ቪድዮውን በጥንቃቄ እንመልከት ።
እኔ ግን እላለሁ !!! እምዬ ኦርቶዶክስ አንቺ የእነ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፣ የእነ ቅዱስ አትናቴዎስ እና ቅዱስ ቄርሎስ የእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፣ የእነ ቅድስት አርሴማ ፣ የእነ አቡነ ተክለሃይማኖት ፣ የእነ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ፣ የአባ ሳሙኤል ዘዋልድባና የአቡነ አረጋዊ ሃይማኖታቸው የሆንሽ ንጽህት ተዋሕዶ ሃይማኖቴ ሆይ ! ብረሳሽና ብከዳሽ ቀኜም ትርሳኝ፣ ትክዳኝም ። ባላስብሽና ባልሞትልሽ ምላሴ ከጉሮሮዬ ይጣበቅ ። ሳለጎበድድ ሳለከዳሽ እንድኖር አምላክሽ ይርዳኝ ። ይህን ባለደርግና ሳልጮህልሽ ዝም ብዬ ብሞት ስሜ ከህይወት መጽሐፍ ይደምሰስ ።
“ጌታሆይ በሆነውና እየሆነ ባለው ነገር የኔ ጌታ ክብሩን ሁሉ አንተ ውሰድ ። አሜን “
“ድንግል ሆይ እናቴ ! አዛኝቱ ዛሬም እንደትናንቱ ቅደሚ ከፊት ከኋላዬ “
ይህንንም ራሴው በእጄ ጻፍኩት ። +4915217428134 ደግሞ የቫይበር ፣ የኢሞና የኋትስአፕ መልእክቶችን የምቀበልበት የእጅ ስልኬ ነው ።
ሻሎም.! ሰላም.!
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
መጋቢት 10//2009ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s