በሰሜን ጎንደር የሚደረገው ፀረ-ወያኔ ዘመቻ ቀጥሏል

የነጻነት ኃይሎች የተጠና ስልታዊ ጥቃት እየፈፀሙ ነው፡፡ (ሌሎች ይህንን ዜና በዝርዝር ሊሠሩት ይችላሉ ወይም መልክት በሚያስተላልፍ መልኩ)፡፡ ዝርዝር ጉዳዮን መግለፅ አስፈላጊ ባልሆነ ዘመቻ እጅግ ከባድ የደፈጣ ጥቃት ፈፅሟዋል፡፡ ስለዚህ ጥቃት በዝርዝር ማውራት ጠቃሚ ስላልሆነ እና ከነጻነት ኃይሎች በተቃራኒ በተሰለፉ ወንድሞቻችን ሞት አንጨፍርም፡፡ ይህን ጦርነት ተገደን የገባንበት መሆኑ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ የሆነው ሆኖ የነጻነት ኃይሎች የወሰዱት ይህ አስደማሚ ጥቃት የነጻነት ሰራዊቱ እና የመረጃ ምንጮች በተጠና መልኩ እየተናበቡ እንደሚሰሩ አሳይቷል፡፡ መሰል ጥቃቶች በቀጣይም በተከታታይ ይኖራሉ፡፡
የነጻነት ኃይሎች በቀጣይ በሚወስዱት ጥቃት ወያኔ ላጠመቃቸው ፀረ-ህዝብ ኃይሎች ሰሜን ጎንደር የኤርታሌ እሳተ-ጎሞራ ነው የምትሆነው፡፡ ለነፃነት ኃይሎች ቅርበት ያላቸው እንደገለፅልን፤ የነፃነት ኃይሎች ሰሜን ጎንደር ላይ ማንኛውንም የወያኔ ኃይል በየትኛውም ቦታና ግዜ ማጥቃት የሚያሰችላቸው የተሟላ ወታደራዊ መረጃ እና ኃይል አላቸው፡፡ ሆኖም ግን የሃገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ዘመቻ እየተደረገ ነው ተብላል፡፡
ወያኔ የነፃነት ኃይሎችን ጫና መቋቋም ሲያቅተው የሃገሪቷን የግዛት አንድነት የሚንድ ችግር ይፈጥራል ተብሎ ይገመታል፡፡ ያንን ለመከላከል በነፃነት ኃይሎች በኩል ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡ ይህ ትግል እጅግ ውስብስ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል፡፡
በተያያዘ ዜና ወያኔ የነፃነት ኃይሎች እንዲዋጋ የላከው አንድ ሻምበል ጦር የት እንደገባ አልታወቀም፡፡ አንዳንድ ምንጮች ጦሩ፤ ለነጻነት ኃይሎች እጅ ሰጥቷል የሚል ዜና እየተሰማ ነው፡፡ ይህ ዜና በተመለከተ መረጃውን ተከታትለን እንደምናቀርብ እንገልፃለን፡፡

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s