የ666 የማይክሮ ችፕ ገጠማ በኢትዮጵያ እና በሌሎች አገሮች ተግባራዊ ሊሆን ነው#50 ሺ ቸርችchurchs 

ውድ ኢትዮጵያውያን ይህን ፅሁፍ ታግሳችሁ እንድታነቡት እፈልጋለሁ፡፡1ኛ፣ሰሞኑን የክሮስ ቸርች አባላት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ሃምሳ ሺ ቸርች በኢትዮጵያሊገነቡ ፈቃድ አግኝተዋል፡፡

2ኛ፣የ666 የማይክሮ ችፕ ገጠማ በኢትዮጵያ እና በሌሎች አገሮች ተግባራዊ ሊሆን ነው፡፡

3ኛ፣የኢትዮጵያ መንግስት ይህን አይነትነት አሰራር የኢትዮጵያ ዜጎች እንዳያውቁና ስለዚህ ጉዳይ እንዳይወሩ የሚያግድ ህግ አርቅቆ ሊያፀድቅ ነው፡፡በእነዚህ ሶስት ነጥቦች ዙሪያ መነጋገር አለብን፡፡

በቅርቡ የሰማችሁት ዜና እንዳለ እርግጠኛ ነኝ፡፡ክሮስ ቸርች ግሎባል ሚሽን የተባለ እምነት ድርጅት በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ገብቶ 50 ሺ ሃምሳ ሺ ቤተክርስቲያን ሊያቋቁም ነው፡፡ስራውን በደቡብ ኢትዮጵያና በሌሎች ክልሎች በይፋ ሊጀምር ነው፡፡እነዚህ ቡድኖች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ከአገራችን ባለስልጣናት ጋር ተወያተዋል፡፡ፕሬዘዳንታችን ጨምሮ ሁሉንም አግኝተው ተነጋግረው አስፈቅደውና ተፈቅዶላቸው ነው ስራቸውን የጀመሩት፡፡ሁኔታው እንግዳ ብቻ ሳይሆን አስደንጋጭም ነው፡፡ዓላማቸው ወንጌልን መስበክ እንደሆነና በኢትዮጵያ ከፍተኛ በጀት መድበው 50 ሺ ቤተክርስቲያን መትከል ነው፡፡እንግዲህ ይህን ጉዳይ በሚመለከት እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ለየራሳችን መጠየቅ ያለብን ጥያቄ ይኖራል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ እነዚህ ሰዎች የሚያስፈቅዱት መንግስትን ወይስ የሚመስላቸውን ምዕመን?ማለት ስለወንጌል ሰበካ ነው አይደለም የሚለውን መንግስት ነው የሚያጣራው?ወይስ የመፅሐፍ ቅዱስ አማኞች?እንደ ሐይማኖተኛ ሳይሆን እንደ መፅሐፍ ቅዱስ ቃል ለነሱ ጥያቄ ማቅረብ ያለበት ማነው?ለምሳሌ መፅሐፍ ቅዱስ ‹‹በመጨረሻው ዘመን ብዙ ሐሰተኛ /ሃሳዊ/ሰዎች ይነሳሉ ብዙ ታዓምራትንም ያደርጋሉ ህዝቡንም ያስታሉ ስለዚህ መርምሩ›› ይላል፡፡ይህን የመመርመርና መንፈስን የመለየት ተግባር የማን ነው?ኢትዮጵያ ውስጥ ማንን ነው የሚመለከተው?የኔ ጥያቄ ነው፡፡

ምንም ይሁን በብዛቱ አስደንጋጭ መሆን ብቻ በርካታ ጥያቄዎችን እንድናነሳ እንገደዳለን፡፡

ልብ በሉ 50 ሺ ቤተክርስቲያን እንዲሁ በአይምሮዋችሁ፤ጎንደር 44 ታቦት፣ጎጃም 44 ታቦት፣ወሎ 44 ታቦት አዲስ አበባ ይህን ያህል፣ ጂማ ይህን ያህል፣እያላችሁ ቁጥሩን ለመገመት ሞክሩ፡፡በተመሳሳይ ሁኔታ ቦሌ አንድ መካነ ኢየሱስ፣ጦር ሃይሎች አንድ፣ ኮተቤ፣ ሸጎሌ፣ እያላችሁ ለመቁጠር ሞክሩ፡፡በተመሳሳይም የሌላውን ኢትዮጵያዊ ሐይማኖት የማምለኪያ ስፍራ ቁጠሩ፡፡ወይም ለመገመት ሞክሩ፡፡

ከዚህ በፊት በአገራችን የነበሩት እነዚያ ሁሉ የማምለኪያ ስፍራ በረጅም ዘመናት ሂደት እየተገነቡና እየተስፋፉ የመጡ ናቸው፡፡በአንድ ጊዜ 50 ሺ የማምለኪያ ስፍራ በኢትዮጵያ የገነባ የእምነት ድርጅት ወይም ተቋም የለም!!

50 ሺን በብር ደረጃ ብትስሉት ወይም ብትገምቱት አምስት እስር ብቻ ናት፡፡በምንም ብትስሉት ቁጥሩ ብዙ ላይመስል ይችላል፡፡በቸርች ወይም በማምለኪያ ስፍራ ደረጃ ሲሆን ግን ምን እንደሚፈጠር አስቡት፡፡

ቦታን በካሬ እየሸነሸናችሁ በደንብ አብሰልስሉት፡፡ለማመን እንቸገራለን፡፡ይህን ያህል ቸርች በመገንባቱ ደስ የሚለው ሊኖር እንደሚችል ሁሉ የሚከፋም ይኖራል፡፡ያ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ነገር ግን ደስ የተሰኘው አካል እሱ ልክ ነው ብሎ ከያዘው እምነት ጋር እነዚህ ይዘውት የመጡት አይቃረንም ወይ?የሚለውን ማሰብ ለምዕመኑ የሚተው ይሁን በሚል ብንተተወው እንኳን፤ የአካሄዱ አስደንጋጭነት ብቻውን ወደ ሌላ ጥርጣሬ ያመራናል፡፡ጥርጣሬ ብቻ አይደለም ወደ ሌላ ዕውነት ያመራናል፡፡

በእርግጥ ለኢትዮጵያ 50 ሺ ቸርች ያስፈልጋታል?አያስፈልጋት

ም! ብሎ የሚወስነው አካል ማነው?እስከዛሬስ የት ነበሩ?50 ሺ ቸርች የሚያስፈልገው ምዕመን ስለመኖሩስ እርግጠኞች ናቸው?ወይስ ምዕመኑ በዝቶ ስለተጥለቀለቀና ቸርቾች ስለጠበቡ?የነዚህ ሰዎች ትክክለኛ ኣላማ ምንድነው?ዓላማቸውንስ ለኛ ነግረውናል?ኦኬ መንግስት ማለት ህዝብ ስለሆነ መንግስት ካመነበት በቂ ነው ልትሉ ትችላላችሁ ነገር ግን መንግስት የሰዎችን የነብስ አዳኝ መርጦ ሊሰጥ አይችልም፡፡በዚህ ዙሪያ ያለውን ነገር ለሌላ ጊዜ እናቆየውና ስለተፈቀደላቸው ወይም ስለተሸጠላቸው ቦታ ብቻ እናስብ፡፡ ሃምሳ ሺ ቤተክርስቲን!መቸም ፈረንጅ ሳያቅድና ሳይዘጋጅ እንዲህ አይነት ነገር ይፋ አያደርግም፤ወደ ተግባርም አይገባም፡፡ሲመጡ ደግሞ እኛ ሰይጣን ነን አይሉም፡፡ በቂ ዝግጅት አድርገው ቅዱሳን እንደሆኑ አድርገን እንድቆጥራቸው የሚያደርግ ተግባር እየፈፀሙ ሊያሳዩን ይችላሉ፡፡ብቻ ተዘጋጅተው የመጡ መሆናቸው ለማንም ግልፅ ነው፡፡ተመልከቱ፤ለአንድ መኖሪያ ቤት እንኳን 500 ካሬ ሜትር ነው በተለምዶ የምናውቀው፡፡ለቸርች ሲሆን ስንት ይሆናል?አንድ ቸርች በስንት ካሬ መሬት ላይ ያርፋል?ይህ ብቻውን ቀና ነገር ይዘው እንዳልመጡ ያረጋግጥልናል!

50 ሺ ቸርች ሊሰሩ ነው፡፡እያንዳንዱ ቸርች በጣም በጣባቡ 1ሺ ካሬ ቢይዝ ብለን እናስብ፡፡ከዚያ በላይ እንደሆነ ሁላችንም እናውቃለን፡፡ግን ነገሩን እናቅልለው ብለን በ 1ሺ ካሬ አረፈ እንበል፡፡እንዲሁ ጠባባብ ቸርች፡፡50000 ሲባዛ በ 1000 50000000/ሃምሳ ሚሊዮን ካሬ ሜትር ቦታ ይሆናል፡፡በ2ሺ ካሬ ካረፈ 100 ሚሊዮን ካሬ ሜትር ቦታ ይሆናል፡፡ወደ ሄክታር ቀይሩት!የሚዘገንን ነው!ይህ በእንዲህ እንዳለ ሌላ ነገር እንድታስቡ ልጋብዛችሁ፡፡አንድ ቸርች በአማካይ በጣም በትንሹ ስንት ሰው ይይዛል?ወይም ስንት አባል ይኖረዋል?ቸርች ሲባል አገልጋይ አስተዳዳሪ ሰባኪ ወዘተ…ብዙ ሰው ይኖራል፡፡ምዕመንም ይኖራል፡፡ስለዚህ እያንዳንዱ ቸርች በጣም በትንሹ 1ሺ ሰው ቢይዝ/እስከ 5ሺ እስከ 10 ሺም ሊደርስ ይችላል/በትንሹ አንድ ቸርች 1ሺ ሰው ቢኖረው ብለን ካሰብን 1ሺን በ 50 ሺ ብናበዛው 50000000/ሃምሳ ሚሊዮን ሰው ይኖረዋል፡፡አንድ ቸርች በትንሹ 2ሺ አባል ቢይዝ የ 50 ሺ ቸርች አባላት ብዛት 100000000 /መቶ ሚሊዮን/ ሆነ ማለት ነው፡፡የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር እ.ኤ.አ በ2015 99 ሚሊዮን ነው፡፡ጠቀለሉት ማለት አይደል?ይህንን ነው አቡነ ፍራንሲስ አንድ ዓለም አንድ ሐይማኖት እያሉ በየአገሩ እዞሩ የሚያሳምኑት!መቸም አንድ ቸርች ከ አምስት መቶ ያነሰ ሰው ይዞ ቸርች አይሆንም፡፡ስለዚህ ጉዳዩ የአንድ ሐይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ጉዳዩ የኢትዮጵያ እንደሆነ ማሰብ አለብን!ይህን እየሰማንና እያየን ምን እየተከናወነ እንዳለ ማሰብ ካልቻልን ሙሉ በሙሉ ክፉ መንፈስ አይምሮዋችን ተቆጣጥሮታል ማለት ነው! 50ሺ ቸርች!!!

መፅሐፍ ቅዱስ ‹‹ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ስበኩ›› ይላል፡፡ነገር ግን እነዚህ ሰዎች ወይም ይህ ድርጅት መጀመሪያ ቸርቹን ከዚያ ስብከቱን እያሉ ነው፡፡ሙሉውን የኢትዮጵያ ህዝብ ቀስ በቀስ በቁጥጥር ስር እንደሚያውሉትና ሌላ የሐይማኖት ተቋማት እንደሚጠፉ እርግጠኞች ናቸው ማለት ነው፡፡ወንጌል ተሰብኮ ምዕመን እየበዛ ሲሄድ ነው ቸርች የሚስፋፋው፡፡ያውም በራሱ በምዕመኑና በሐይማኖቱ ተከታይ በሚዋጣ ገንዘብ! እንደዚህ ዘሎ እንደ መንገድ ስራ ፕላን 50 ሺ ቸርች የሚባልበት የሐይማኖት ስርዓት የለም፡፡መንግስትስ መሬት መሸጥ ነው የያዘው ወይስ የሀይማኖት ነፃነትን ለማንሰራፋት? እኔ ኦርቶዶክስ ብሆንና አንድ የውጭ የሐይማኖት ድርጅት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ 50 ሺ ቸርች ልሰራ ነው!ቢለኝ ‹‹ኧረ አባ 50 ሺ ቤተክርስትያን በዚች ጠባብ አገር?››ብየ እሞግታለሁ፡፡እኔ ፕሮቴስታንት ብሆን ‹‹50 ሺ የፕሮቴስታንት ቸርች ልናቋቁም መጣን!›› ቢሉኝ፤‹‹ኧረ ፓስተር 50 ሺ ቸርች?››ብየ መቃወሜ አይቀርም፡፡እኔ ካቶሊክ ብሆንና የሌላ አገር ቅርንጫፍ ተቁዋም መጥቶ ‹‹50 ሺ ቸርች በኢትዮጵያ!››ሲለኝ ብሰማ፤‹‹እንዴት?››ብየ መቃወሜ አይቀርም፡፡እኔ ሐይማኖት አልባ ብሆንና ይህን ነገር ብሰማና ባይ፤ ‹‹እንዴ እንዴት?ያገሬ ገበሬ ምን መሬት አርሶ ሊበላ ነው?››ማለቴ አይቀርም፡፡እኔ ከየትኛውም ወገን ብሆን ይህን ዜና መቃወሜ አይቀርም፡፡መንግስትም ብሆን ‹‹ከፍተኛ የሆነ የመሬት ወረራ›› እለዋለሁ፡፡ስለሚፈናቀለው ሰው አስባለሁ፡፡ይህን ያስቀደምኩት ጉዳዩ የሐይማኖትና የሐይማኖተኞች ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የአገር ህልውና ጉዳይ መሆኑንም ጭምር ለማስገንዘብ ነው፡፡ይህ ጉዳይ በቀጥታ የኢትዮጵያን ህዝብ ከሌላው ዓለም ህዝብ በፊት የአውሬው ምልክት የሚባለውን የ666ን ወይም የማይክሮ ችፕ ገጠማን ለማከናወን የተጀመረ ጅምር ወይም የመሰረት ድንጋይ እንደሆነ ከመጠርጠርና ከማሰብ ውጭ ሌላ ስያሜ ልንሰጠው አንችልም!ሌላ ማሰብና መገመት የምንችለው ነገር የለም፡፡ይህን አርማ ደግሞ በቀላሉና በቶሎ አይቀበሉም ተብለው የተፈሩት የኢትዮጵያዊ ዜጎች ናቸው፡፡ በዚህ ሀሳብ የሚስቅ ሰው ካለ ቀስ እያለ እንደሚያለቅስ የታወቀ ነው፡፡‹‹ኢትዮጵያን ይፈልጉዋታል፡፡ኢትዮጵያ ከመጨረሻው ዘመን ጋር በተያያዘ ትልቅና ወሳኝ የሆነ መንፈሳዊ ነገር በውስጡዋ አለ፤ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ልዩ አገር ናት››ሲባል የሚያፌዙ ምሁራን እንዳሉን እናውቃለን፡፡ግድ የለም ሁሉም በዘመኑ ይፋ ይሆናል!ለታወሩት ሳይሆን ላልታወሩት ነው ነገሩ ግልፅ የሚሆነው፡፡

ይህን ጉዳይ በስተኋላ የምንመለስበት ይሁንና ስለተያያዡ ነገር እንይ፡፡

መፅሐፍ ቅዱስ በዮሐንስ ራዕይ ምዕራፍ 13 ቁጥር17-18 እንዳይጠየቁ

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s