ሩሲያ የሶሪያን የአየር ጥቃት የመከላከል አቅም እንደምታጠናክርና እንደምታሳድግ አሳወቀች

ትራምፕ ሀገራቸው በሶሪያ ላይ የምትወስደውን እርምጃ አጠናክራ እንደምትቀጥል ሲያሳውቁ ሌሎች ሀገሮችም በዘመቻው ከአሜሪካ ጎን እንዲሰለፉ ጥሪ ማቅረባቸውም ተሰምታል።Donald
በሶሪያ ጉዳይ ከአሜሪካ ጋር የደረሰችበትን ውል ውድቅ ማድረጓን ያሳወቀችውና የትራምፕ አስተዳደርን እርምጃ ያወገዘችው ሩሲያ በበኩሏ የሶሪያን የአየር ጥቃት የመከላከል አቅም እንደምታጠናክርና እንደምታሳድግ አሳውቃለች።
የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት በጉዳዩ ዙሪያ አስቸኳይ ስብሰባ የተቀመጠ ሲሆን የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ገተርስ አሜሪካ ጥቃቷን እንድታቆም ተማጽነዋል።
ሶሪያ ዓለማቀፍ ስምምነትን በመጣስ በኬሜካል ጦር መሣሪያ ህጻናትና ሴቶችን ጨምሮ በርካታ ሲቪሎችን ገድላለች የሚሉት ዶናልድ ትራምፕ ግን በሶሪያ ላይ የተጀመረው ጥቃት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል


ምዕራባውያንና የሶሪያ አማጽያን ከቀናት በፊት ኢድሊብ በሚባለው የሶሪያ ክልል በምትገኘውና ካሀን ሼይኩሁን ተብላ በምትጠራው የሶሪያ ግዛት የበሽር አላሳድ መንግስት የኬሚካል ጦር መሳሪያ እንደተጠቀመ ሲከሱ ሩሲያና የሶሪያ መንግስት ደግሞ ጥቃቱ የተፈጸመው በምዕራባውያን በሚታገዙት አማጽያን ነው ባይ ናቸው።


ፕሬዚዳንት ቡሽና ቶኒ ብሌዬር ሳዳም ሁሴን የኬሚካል ጦር መሣሪያ እንደተጠቀሙ በመክሠስ ኢራቅ ላይ በህብረ ብሔሩ ጦር አማካይነት መጠነ ሰፊ ጥቃት ማስፈጸማቸውና ሳዳምን በስቅላት ማስወገዳቸው አይዘነጋም። ይሁንና ከዓመታት በኋላ የቡሽና የብሌየር ክስ ውሸት ሆኖ መገኘቱ ይታወቃል።


ኢራቅ ግን ከያኔ ጀምራ እስካሁን ድረስ የሽብርተኞች መናኸሪያና የፍርስራሽ ክምር ሆና ቀርታለች።

አሁንስ ነገሩ ወዴት እያመራ ነው?

abbaymedia

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s