እናተ ሸክማችሁ የቀለለባችሁ …እንዳትጥሉት ! ! (አሌክስ አብርሃም)

እንዴት ናችሁ ጓዶች ?. . . እኔ ሰላም ነኝ ! ሆሳእና እንዴት ነበር ?. . . እሱማ እንዴት ይሆናል ያው ወደቀልባችሁ መለስ ብላችሁ ደግ ደጉን ስትለጥፉ አይቻለሁ ! እኔ የምላችሁ እንደው የሆሳእናን ነገር እያሰብኩ የሆነ ነገር ትዝ ብሎኝኮ ለምን አንጫዋወታትም ብየ አሰብኩ ! ይወራ አይደል . . .? ለነገሩ እንደው ለወጉ ነው እንጅ <<አይ>> ብትሉም ዝም አልልም:) ዳይ ወደጉዳያችን … ዛሬ ወደኢየሩሳሌም ግድም ነው የምንሄደው . . . .

እንግዲህ ኢየሩሳሌም ያልተነገረላትም ያልተነገረባትም ትንቢት የለም ! እንግዲህ ከትንቢቱ አንዱ ‹‹ንጉስሽ ይመጣል›› የሚል ነው ….መቸስ እነዛ ህዝቦች እግዚአብሔርን ያውቁታል ….በምድረበዳ አንዴ ተራራ ሲንጥ አንዴ ባህር ሲከፍል …ከደረቅ ድንጋይ ውሃ ሲያንዠቀዥቅ …ከሰማይ መና ሲያወርድ ያውቁታል ….እና አሁን ደግሞ ይመጣል የሚለውን ትንቢት እንቅ አድርገው ይዘው ግን ‹‹አመጣጡ እንዴት እንዴት ነው ?›› ብለው ሲየጠብቁ ነበር … ደግሞኮ በሮም ቅኝ ተገዝተው በስጋም በነፍስም ባርነት ውስጥ ሁነው ነው የሚጠብቁት ….

ቅኝ ገዥዎቻቸው በሚገርሙ ስልጡን ፈረሶች ላይ ጉብ ብለው …ሰረገላቸውን እያንካኩ እና ጦራቸውን እየሰበቁ ረግጠው ሲገዟቸው ነፃ አውጫቸው ከሮማ ወታደሮች ሽ ጊዜ በሚያስፈራ ግርማ በእሳት ሰረገላ ምድሩን እየገለባበጠው እንደሚመጣ አልተጠራጠሩም !

እና((( ንጉሱ መጣ )))….አዳኛቸው ወደኢየሩሳሌም መጣ ….ከዘላለም ባርነት የሚያወጣቸው ታዳጊያቸው ደረሰ ….እንዴት መጣ ?…ደመናውን ሰንጥቆ በሚያስፈራ ግርማ ተከሰተ …..? አልተከሰተም!! ….መሬትን ፈነቃቅሎ እንደገሞራ ሽቅብ ኢየሩሳሌምን አሸበራት ??…..በጭራሽ! …..እና እንዴት መጣ ?????…..((ሚስኪን ባለች ሁርጭላ ላይ ተቀምጦ መጣ በቃ !!)) እንዲህ አይነት ነገር ሲገጥመውኮ ነው ፈረንጅ ‹‹Are you kidding me ? ›› የሚለው …. እስካሁንም ጌታን ያክል ነገር እንዴት ሁርንጭላ ላይ ተቀምጦ መጣ ይባላል ብሎ የሚገረም አለም ላይ ነን ! ወደዛ ዝርዝር ሳንገባ አሁን በቀጥታ ወደአህያ ሁርንጭላዋ ጉዳይ እንሂድ ….መነሻየም እሱ ነው !!

ጓዶች …. ኢየሱስ በአህያ ሁርንጭላ ወደታላቋ ከተማ ከመግባቱ በፊት ምን እንደተፈጠረ ተመልከቱ ….ከተማዋ አቅራቢያ ደብረዘይት የሚባለው ተራራ ላይ ወደምትገኘው ቤተ ፋጌ ወደምትባል ስፍራ ሲደርሱ ኢየሱስ …ደቀመዛሙርቱን አዘዛቸው ‹‹በአቅራቢያችሁ ወዳለው መንደር ሂዱ … እንደደረሳችሁም አንዲት አህያ ከነውርጭዋ ታስራ ታገኛላችሁ ፣ ፈታችሁም ወደኔ አምጧት …ማንም ሰው ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ ቢላችሁ ((ጌታ ይፈልጋቸዋል)) በሉት ወዲያው ይሰዳቸዋል !!

እናም ደቀመዛሙርቱ እንደተባሉት አደረጉ ! አሁን ለአህያዋ የሆነውን ተመልከቱ …አንድ የተናቀችውን አህያ ያውም ጌታ በአድራሻዋ ሰው ልኮ ፈለጋት ….ሁለት አህያም ሁና በዛ ላይ እስረኛ አህያ ነበረች በኢየሱስ ትዛዝ ተፈታች …ሶስት በሉ … ከእስራቷ እንዳትፈታ ዘብ የቆመ ማንም ሰው ለምን ትፈቷታላችሁ ቢል የጌታ ስም ወላ ጠባቂ ወላ አስሮ የሚያስቀምጥን ባለቤት ዝም ከነሚያስብል ክብሩ አብሮ ተላከ !! ‹‹ጌታ ይፈልገዋል›› የተባለን ነገር …በዚች ምድር ማንም መንገድ ዘግቶ ትእዛዙን የመከልከል አቅም ያለው የለም !! ከዚህ ሁሉ ነገር በላይ የሚደንቀው ግን አህያዋ ከነሁርጫዋ ከመጣች በኋላ ልብስ በላይዋ ላይ አስቀመጡባት ይላል ….

መቸም አህያን ማዘነጥ የሚያስብ ማንም የለም ….ጌታ በላይዋ ላይ ተቀመጠባት …. መቸም አህያ ምንም ነገር መሸከም ብርቋ አይደለም ….ድንጋይም ትሸከማለች ዱቄትም ትሸከማለች በህይዎት ዘመኗ ብዙ ነገር ትሸከማለች አህያ !…. ተሸክማም እየተዠለጠች ትነዳለች ….የዛን ቀን ግን …ጌታ በላይዋ ላይ ተቀመጠ ! ልክ ሲቀመጥባት ሲዠልጣት የኖረ ህዝብ ከፊቷ ግማሹ ልብሱን ግማሹ የዘንባባ ዝንጣፊ እያነጠፈ ‹‹ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ …በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው›› እያለ በከፍተኛ እልልታና ክብር ከአህያዋ ፊት እየተደፋ !! በፊት ክብር ገፎ እርቃን ያስቀረ ሳይቀር ዛሬ የራሱን ልብስ እያወለቀ የራሱን ክብር እየጣለ ማልበስና ማክበር ጀመረ ..ለምን ….. እስከዛሬ ለተሸከመችው ዱቄት ነው ?…ወይስ እስከዛሬ የቀጠቀጧት ፀፅቷቸው ?….ለሁሉም አይደለም !!በላይዋ ላይ ለተቀመጠው ክብር ሲሉ! ለጌታ ሲሉ! ((ለተሸከመችው ክብር)) !!

ጓዶች . . . በተለይ ክርስትና ገብቷችሁ የእግዚአብሔርን አደራ ተሸክማችሁ ሰው የሆናችሁ ጓዶች ….ወላ ሰባኪ ወላ ዘማሪ ወላ ፌስቡከር ወላ ሰፊው ህዝብ…. ክብራችሁ ኢየሱስ ነው ….አለም ያከበራችሁ በሰው ፊት ከፍ ከፍ ያላችሁት በእናተ ማንነት በእናተ ችሎታና ብቃት አይደለም …በተሸከማችሁት ክቡር ስም ነው !! ጭብጨባው ሲበዛ ልነጠፍ ልዘርጋ አፈር አይንካችሁ የሚል ሲበዛ በማንነትና ችሎታችሁ ወይም በምርጥ ወግ አዋቂነታችሁ …አልያም በምርጥ ዘራችሁ … ብትፈልጉ በጉልበትና ገንዘባችሁም የተከበራችሁ መስሏችሁ የተሸከማችሁትን ክብር አትጣሉ !! የጣላችሁት ቀን የሳቀችላችሁ አለም ዱላዋን ይዛ ነው የራሷን ኮተት አሸክማ በውርደት የምትነዳችሁ !! ከዛ አውጥታ ለጅብ ! እንደዛ ነው ዓለም አሰራሯ ! ሸክማችሁ ሸክም አይደለም ክብር ነው !!ቀለለን ብላችሁ እንዳትጥሉት !!

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s