ለአቡነ ማቲያስ – የዝምታ ዋጋው ስንት ነው!? የሞራል ልዕልናስ ድንበሩ የት ላይ ነው!?

መስቀሉ አየለ

በአስራ ዘጠኝ ሃያዎቹ መጀመሪያ ላይ ከአንደኛው የአለም ጦርነት ፍርስራሽ ውስ ጥ ገና በቅጡ ያልወጣው የሶቪዬት ቦልሸቪክ አብዮት ከነበረው አስከፊ የአገሪቱ ኢኮኖሚ ጋር እንዴት ተጣጥሞ መሄድ እንዳለበት ሊረዳው ከባድ ፈተና ሆኖበት ነበር።በወቅቱ ዋነኛ የሶቪየት ኤምፓየር የስንዴ ቀበቶ (ዊት ቤልት) ይባል የነበረውን የዪክሬን የእርሻ መሬት በግለሰብ ደረጃ የያዙ ሃብታም ገበሬዎች በመንግስት ስር ተደራጅተው በማሕር ለማምረት ባለመፍቀዳቸው የተነሳ ስታሊን በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዩክሬን ገበሬዎችን ገደለ። ያን  እልቂት ተከትሎ አገሪቱ ውስጥ ምርት የሚያመርት ሰው በመጥፋቱ የተነሳ በነበረው እረሃብ የዩክሬን ዜጎች ልጆቻቸውን ቀቅለው በልተዋል። በዚያ አስደንጋጭ ክስተት ግራ የተጋባው የዩክሬን አስተዳደር በዋና ከተማዋ ኬይቭ ዋና ዋና አደባባዮች ላይ “የሰውን ስጋ መብላት ነውር ነው ” የሚሉ መፈክሮችን ሰቅሎ እንደ ነበር ታሪክ በጥቁር ማህደር ላይ መዝግቦታል። ዴቶቭስኪ እንዳለው እግዚአብሔር ከሌለ የሚከለከል ነገር አይኖርም ። አምልኮተ እግዚአብሔርን ሗላ ቀርነት ብሎ ኮሚኒዝምን እንደ ሃይማኖት የተቀበለ ማህበረሰብ ይሕን ድርጊት ቢፈጽም አይገርምም። abune mathias
ቦብ ጊዶልፍ ለሊቪንግ ኤይድ የገንዘብ መዋጮ ዝግጅት የድርቁን አስከፊነት በአካል ተገኝቶ ለመገምገም በሰባ ሰባት አመተ ምህረት የድርቁ እምብርት (ሆት ስፖት) ወደ ነበረው ወሎ ራያ ለመሄድ ገና ከአገሩ ሲነሳ ደርዘን ሙሉ በጣም የሰለጠኑ የሴኩቱሪቲ ቦዲ ጋርዶች ተቀጥረውለት  የተጓዘው በቦታው ሲደርስ ግን ያየውና የታዘበው እራሱን ለሁለት የሚሰነጥቅ እውነት ነበር። የወሎ ገበሬዎች በጠኔ የተያዙ ህጻናቶቻቸውን በክንዳቸው ታቅፈው የዱቄት ወረፋቸውን በትእግስት አክብረው ሲጠብቁ የህጻናቶቹ ህይወት  ያለፍ የነበረበትን መራር እውነት በታዘበበት ማታውን  ቦዲ ጋርዶቹን ወዳገራቸው አሰናብቶ ብቻውን በተፈናቃዮች መንደር ለመክረም ተገዷል። ቦብ ጊዶል ከጥቂት ሳምንታት ቆይት ቦሃላ ወደ አገሩ ሲመለስ በቦሌ ኤርፖርት ላይ ሃጢያቱን ለአለም አቀፍ ጋዜጠኞች እንደ ተናዘዘው ዕቦዲ ጋርዶቹ የተቀጠሩልኝ ሰዎች (ከመራባቸው የተነሳ ሊበሉህ ይችላሉዕ  የሚል ስጋት በመኖሩ  ነበር ሲል ይቅርታ ጠይቆ ዛሬ ከህሊና እዳ ነጻ ሆኖ ይኖራል።አንድ ሰው ሌላውን መለካቱ በሚያውቀው ነገር ላይ ተመስርቶ  መሆኑ የተፈጥሮ ህግ ነው። እኛ ደግሞ ኢትዮጵያውያን ነን።
ካሁን በፊት ለመግለጥ እንደ ሞከርኩት ወያኔዎች ለኢትዮጵያ አምባገነናዊ የአገዛዝ ቀንበር ብቻ አይደሉም፤ ዘረኛና ከፋፋይ ብቻም አይደሉም፤ ጸረ ሃይማኖትም ብቻ አይደሉም።ነገር ግን ሰውን  ከመንፈስ ከፍታ የሚያወርዱ በጣም ስር የሰደዱ የሞራል ፈተና ጭምር እንጅ፣ እነሱ ገና ጫካ በአርማጮሆ ግንባር በኩል እያሉ በደርግ ጦር ለቀናት ተከበው ሲከርሙ የሚበሉት ቢያጡ እርስ በእርሳቸው እንዴት እንደ እንደ ተበላሉ  ካነበብነውና ከተረዳነው እውነት ለመግለጥ ሞክሬ ነበር። ዛሬ በካህኑ መልከ ጸዴቅ እድሜ፣ ቅድስና እና ቁመት የሚለካውን የዚህችን አገር የሞራል መሰረት ለመናድ ሲነሱ ግብረ ሰዶማዊነትን ሲያስፋፉ፣ የህግ ማደሪያ የሆኑትን ጽላቶች ለገባያ ሲያቀርቡ፣ ነውር ያለባቸውን ነፍሰ በላ ታጋዮች ከመክርካቶ በተገዛ ቆብና ቀሚስ “ጳጳስ” አድርገው ሲሾሙ ብሎም ዛሬ ደግሞ ምድሩን የአህያን  ደም በማፍሰስ ሲያረክሱ ከማንም በፊት ቀድመው ፊታውራሪ መሆን የነበረባቸው ቅዱስ ሲኖዶሱ ውስጥ በጴጥሮስ ወጳውሎስ፣ ተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊቦናስ መንበር ላይ የተቀመጡት ነበሩ። እነርሱ ዛሬ ካህኑ ኤሊ  በቤተ መቅደስ ጓሮ የተሰራውን ነውር አይቶ ዝም እንዳለ ዝም እንዳለ ዝም ብለዋልና ኤሊን የቀሰፈው መላከ ሞት ከበር ቆሞ ይጠብቃቸዋል።
የአንድ ህብረተሰብ ሞራል የሚጠበቀው በመርህ ነው።ህግም የሚወጣው እንዲህ ያሉትን እሴቶች ጠብቆ ወደ ሚቀጥለው ትውልድ ለማሻገር ነው። ለኛ ለኢትዮጵያውያውን ደግሞ  ለአንድ ሽህ አመታት ባለትቋረጠው የጦርነት አዙሪት ውስጥ በደረሰብን መውደቅና መነሳት ሳንፈርስ የቆየንበት ምስጢሩ ይኸው ለድርድር ሳይቀርብ የኖረው የመንፈስ ከፍታችን ነው። ሶማሊያ በዚያድ ባሬ ስር መንግስት ነኝ እንዳላለች ዚያድ ባሬ ሲገለበጥ በፊሽካ የፈረሰችበት፣ ሊቢያ ጋዳፊን፣ ኢራቅ የሳዳምን መውደቅ ተከትሎ የፈረሱት አገዛዝ ብለው ካቆሙት መዋቅር ውጭ እነሱን እንዳገር ያቆመ ምንም አይነት የህብረተሰብ መስተጋብር ስላልነበራቸው ነው። ዛሬ እኛ ኢትዮጵያውያን በሰንበት የተቀዳ ውሃ መጠጣት የሃጢያት መጨረሻ ተደርጎ ሲወሰድባት በኖረችው አገራችን ውስጥ የአህያን ስጋ አርዶ መሬቷን የሚያረክስ በላዬ ሰብ ሲመጣ ዝም ማለት የሌለብን በዚሁ ከቀጠለ ነገ እኛን እንደ አገርም እንደ ማህበረሰብም የሚያቆመን ምንም ነገር ስለማይኖር ነው። ሃያ ሚሊዮን ያህል የሶቪየት ህብረትን ዜጎችን በቀይ ሽብር የገደለው ስታሊን እንዳለው ዕእኛ ህግ የሻርነው የመጀመሪያን  ሰው የገደልን ቀን ነው፤  ከዚያ ቦሃላ የሆነው ሁሉ ግን የቁጥር ጉዳይ ነውዕ ነበር ያለው።ልጆቿን የበኩር ልጅና የእንግዴ ልጅ ብላ በምትለይ አገር የተወለዱና ትናንት በለጋ እድሜያቸው እረሃብን በስደት ሊያሸንፉ ተገፍተው መንገድ የገቡ አንድ ፍሬ ለጋ ወጣቶች በሊቢያ በረሃ  አይሲስ ለተባለ የጨለማው አበጋዝ ለወደረው ሳንጃ “እምቢ ለማተቤ” ብለው አንገታቸውን በኩራት የሰጡት አያቶቻቸው ካሰመሩላቸው የማንነታቸ ውሃ ልክ ላለመውረድ እንደነበር አይናችሁን አፍጣችሁ የተመለከታችሁት ምስክር ሊሆንባችሁ እንደሆነ አታውቁም። ትውልድ እንደ ጅረት እየተከታተለ እንዲህ ዋጋ ሲከፍልባት በኖረችው አገራችን ላይ ነቢየ እግዚአብሔር እንደተናገረው “የበጉን ላት የምትበሉትም ሆነ ጸጉሩን የምትላጩት” እናንተው ሆናችሁ ሳለ ዛሬም ስርዓትና ህግ ሲጣስ ምድራችንም በአህያ ደም ስትረክስ ዝም ብላችሗል ።አባ ማቲያስ፤ ዘይሴሰይ እክልዬ አንሳ ሰኮናሁ ላእሌየ ተብሎ የተጻፈው በእናንተ ላይ ነው። የደጅህን ፍርፋሪ የበሉት ተረከዜን ነከሱኝ ማለቱ ነው።
የትንሳኤ በኩራት ሆይ፦ አቤቱ ሰናኦርን ባየኽበት አይንህ ተመክልከታቸው !!!
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s