8 kinds of readers

የትኛው አይነት ናችሁ?

እናውቃቸዋለን ፤ እንወዳቸዋለን፤ እነሱን ነን―የመፅሀፍት አፍቃሪዎች! ልክ በየትኛውም መስክ እንዳለው ሁሉ፣ አንባቢዎችም አይነት አላቸው። አብረን እንያቸው ፦

1) የሰንበት አንባቢዎች

ከቀላሉ እንጀምር። እነዚህ ዘና ያሉ አንባቢዎች ናቸው። ንባብን ቀለል አድርገው ነው የሚወስዱት። የሚያነቡትም በእረፍት ቀን ወይም ሌላ ምቹ አጋጣሚ ሲገኝ ነው። የሚያነቡትም ለመዝናናት ሲሉ ብቻ ነው። እውነቱን እንነጋገር ከተባለ እነዚህ አሪፍ አንባቢዎች ናቸው።

2) ቸካይ አንባቢ

እነዚህ “የሰንበት አንባቢዎች” ፣ ፍፁም ተቃራኒዎች ናቸው። በእጃቸው የገባ ፅሁፍ ሁሉ ይነበባል ። ንባብ በቃኝ የማይሉና እስከ መጨረሻዋ ፊደል ድረስ ተጋድለው የሚያነቡ ናቸው። በቀን አንድ ወይም ከዚያ በላይ መፅሀፍት አንብበው፣ ጨርሰው የሚያድሩ ናቸው። በርቱ!

3) ደራሲ ተኮር አንባቢ

እያንዳንዳችን ከሌሎች አብልጠን የምንወደው ደራሲ ይኖረናል። እኔ ለምሳሌ ለዶስቶቭስኪ የተለየ ፍቅር አለኝ። በዚህ ዘውግ ውስጥ ያሉ አንባቢዎች ለሚወዱት ደራሲ ታማኝ ናቸው። የዚያን ደራሲ ሁሉንም ስራ አሳደው ያነባሉ። ይበል የሚያሰኝ ነው!

4)ጊዜያዊ አንባቢ

እነዚህ አንባቢዎች ደግሞ ስለሚያነቡት ነገር ምንም እርግጠኝነት የላቸውም። እያነበቡ ያሉትን መፅሀፍ ይወዱታል? ከነጭራሹ ማንበብ ያስደስታቸዋል? እነሱም አያውቁትም! ስለነሱ እርግጠኛ መሆን የሚቻለው ሁሌም ወደ ንባብ ጎትቶ የሚያመጣቸው ነገር አለ!

5) ምሁር አንባቢ

ምሁራን አላማቸው ግልፅ ነው― መማርና የአለምን እውቀት መሰብሰብ። ይህን የሚያደርጉት ደግሞ በንባብ ነው። ምሁር አንባቢዎች ፣ ኢ―ልብወለድ እና ታሪካዊ ልብወለድ ምርጫዎቻቸው ናቸው።
የሚከበር ምርጫ ነው!

6) የተኮፈሰ አንባቢ

እነዚህ የሚያነቡትን አለም ሁሉ እንዲያውቅላቸው ይፈልጋሉ። አንባቢ ለመባል ይሻሉ። ክብር ያስገኝልናል ብለው ስለሚያስቡ ፣ ያላነበቡትን መፅሀፍ አንብበናል ከማለት አይመለሱም። እነዚህን አትጠጓቸው!

7) አይናፋር አንባቢ

እነዚህ ማንበባቸው ፍፁም እንዲታወቅ አትፈልጉም። ወደ የመፅሀፍት ውይይት ክበብ አይሄዱም፤ ማህበራዊ ድረ ገፆችን አይጎበኙም። ለነሱ ንባብ ለብቻ የሚደረግ የግል ጉዳይ ነው!

8) የሕይወት ዘመን አንባቢ

እነኚህ ከመፅሀፍት ጋር አብረው ተወልደው፣ አብረው የሚያረጁ ናቸው። ሲያድጉም አንገታቸውን መፅሀፍ ውስጥ ቀብረው ነው። ንባብ ከማብዛታቸው የተነሳም፣ ወዳጅ ዘመድ አንዳንዴ ጣልቃ እየገባ ” ተው! ቀንስ!” የሚሏቸው ናቸው ።

እናንተስ የትኛው አይነት ናችሁ? አስተያየት መስጫው ላይ ንገሩን!

Image may contain: people sitting and indoor
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s