ህዝብ አትግደሉን እያለ ይጮሃል እነሱ የባቡር መስመር ዝርጋታችን ተጓተተብን እያሉ ይቀዉጡታል

ስለ እነዚህ ሰዎች ሳስብ አንዳንዴ ያስቀኛል:: እረ በደንብ ላሰበዉ ሰዉ ሁሉ ያስቃሉ:: ህሊና ቢስነታቸዉ እና አይናዉጣነታቸዉ:: የኢትዮጵያ ህዝብ በአጠቃላይ አትግደሉን: የመኖር ህልዉናችንን አክብሩልን:
በሀገራችን ላይ እንደ ሰዉ እንኑር: ብንራብም ብንጠማም ያፈራንዉን ንብረት ባይኖርም እንደ ዜጋ ከምንኖርበት ቦታ ላይ አታፈናቅሉን እያለ ይጮሃል:: ኦሮሞዉ መሬቴን በልማት አሳባችሁ ስትነጥቁኝ ቢያንስ አግባብ ያለዉ ካሳ
ስጡኝ:: እንደ አርሶ አደር መሬቴ ከተወሰደ የምልሰዉም የምቀምሰዉም የለኝም እና ያለኝን መሬት ነጥቃችሁ ስትወስዱ የሚገባኝን ካሳ ስጡኝ ብሎ ሲጠይቅ
ይሄን መጠዬቅህ ጥጋብ ነዉ ብለዉ ጥይት ያጎርሱታል::ጉራጌዉ ነግጄ የምበላባትን: ልጆቼን የማሳድግባትን ሱቄን አለአግባብ እና አለ ህግ አትዉሰዱብኝ ብሎ ሲማጸን ወደ እስርቤት ይወረዉሩታል::መርካቶን ለመቆጣጠር
ልዩ አዋጅ ይወጣል::
የአዲስ አበባን ነዋሪ መሬት አፈናቅሎ ለወያኔ ቅልብ ኢንቨስተሮች እና ወሮ በሎች ለመስጠት አዳዲስ አዋጆች ታዉጀዉ ያድራሉ:: ህዝብ ቤትና መሬት አለኝ
ብሎ መቶ አመት እና አምሳ አመታታ ሙሉ የገበረበትን ቦታ ይሄ ያንተ አይደለም::ያንተ ንብረት እዚህ መሬት ላይ የቆሙት እነዚህ ብስባሽ እንጨቶች
ብቻ ናቸዉ እና እነሱን ለቃቅመህ ተሸክመህ ጥፋ ይባላል::ህዝብ ያነባል:: አማራዉ 26 አመታት ሙሉ በአባቶቹ ሀገር ኢትዮጵያ እንደመጤ እንዲቆጠር እና
የዘር ፍጅት እንዲደርስበት ማኒፌስቶ አብጅቶ አንድም ቀን ሳያሰልስ ተግባራዊ እያደረገ ያለ የራሱን ህገ መንግስት እንኳን በጠራራ ጸሀይ ጥሶ ወንጀል
ሲፈጽምና ሲያስፈጽም ይገኛል:: በብዙ አስር ሽህ የሚቆጠሩ እስረኞች በእስር ቤት ያለፍትህ ይደበደባሉ: ይወገራሉ: ይሰቃያሉ: ይገደላሉ: ይራባሉ:
ይዋረዳሉ::ምንም ስላደረጉ አይደለም::ፍትህ እና ሰበአዊ ክብር ያለዉ የሰበአዊነት ጥያቄ ስለጠዬቁ ነዉ::
በደቡብ ኢትዮጵያ ትንንሽ ጎሳዎች እርበርሳቸዉ እንዲፋጁ ሲደረግ ይሄዉ ሀያ ስድስት አመታት አለፈዉ::ጋንቤላ ፍጅት ነዉ::ሶማሌ መከራዉን ይጠብሳል::አፋር
በገዛ መሬቱ ላይ የባለቤትነት መብት የለዉም:: ኢትዮፕያ ከዳር እስከዳር በግፍ እንባ ትጣጠባለች::ልማት እና ብልጽግና ግን ለኢትዮጵያ ህዝብ እንደ ተረት
ተረት ይተረትለታል::
ይሄ ሁሉ በምድሪቱ ላይ እየተከናወነ እያወቁ የወያኔ ካድሬዎች እንዲህ እያሉ ያላዝናሉ:: “…የወልዲያ- መቐለ ባቡር መስመር ዋና ግንባታ ከቆመ አምስት ወር ሆኖታል…::የኢትዮጵያ ህዝብ በደል እየተሰራበት ነዉ::”
ሆሆይ አሉ እማማ ማሚቴ…
ህሊናም የለ? ሀፍረትም የለ?
ለነገሩ የት መቼ የፈጠረባቸዉን ህሊና?

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s