የአዲስ አበባ የታክሲ ሾፌሮች አመጽ ቀስቃሽ የታክሲ ጥቅሶችን በአስቸኳይ እንዲያነሱ በኮማንድ ፖስት መታዘዙ ተነገረ

 ካለፈው ሳምንት ሚያዚያ 11 ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ስቴዲየም በሚገኘው የመንገዶች ባለሥልጣን አዳራሽ  ከወያኔ ሰዎች ጋር እየተወያዩ የሚገኙት ባለ ኮድ አንድ የታክሲ ሾፌሮች በቁጥር ከ5ሺ ይልቃሉ ተብላል፡፡
ውይይቱ የተዘጋጀው በአዲስ አበባ መንገዶች ባለሥልጣንና በኮማንድ ፖስቱ ሲሆን አዲስ የወጣውን የመንገድ ትራንስፖርት ትራፊክ መቆጣጠሪያ ደነብ ቁጥር 395/2009 ከሚመለታቸው አካላት ጋር ለማስተዋወቅ የተሰናዳ ነው በሚል ነበር፡፡
ኾኖም መድረኩ ቅሬታና የዓመታት ብሶት ገንፍሎ በወጣባቸው የታክሲ ባለንብረቶችና ሾፌሮች ቁጥጥር ሥር ወድቋል ለማለት ያስደፍራል፡፡
በሰባቱ ቀናት ስብሰባ የመናገር እድል የተሰጣቸው ተወያዮች መንግሥትን ክፉኛ የተቹ ሲሆን የብዙዎቹ አቤቱታ “መንግሥት እኛን እንደተቃዋሚ ፓርቲ እንጂ እንደ አገልግሎት ሰጪ አድርጎ አይመለከተንም” የሚል ነው፡፡
“እኛን ከመክሰሳችሁ በፊት ራሳችሁን ብትፈትሹ ጥሩ ነበር” ያሉ አንድ የታክሲ ባለንብረት “በአገሪቱ ሙስና የተፈለፈለው ከናንተ ቢሮ አይደለምን?” ሲሉ ጉቦ የማይጠይቅ ትራፊክ በአዲስ አበባ በተለይ ደግሞ በኦሮሚያ ፈልጎ ማግኘት እንደማይቻል የ15 ዓመት ልምዳቸውን በመጥቀስ አብራርተዋል፡፡
በየቀኑ ከ10 እስከ 20 የሚሆኑ ታዳሚዎች ሐሳባቸውን እንዲሰጡ በተደረገበት በዚህ ዉይይት ፖለቲካዊ መንፈስ የነበራቸው ድምጾችም ተሰምተዋል፡፡
“በ97 ምርጫ ዋዜማ ለሰልፈኞች ነጻ ትራንስፖርት ሰጥታችኋል ብላችሁ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በበጎ እንደማታዩን ይገባናል፡፡” ያሉ ሌላ ባለንብረት ንግግራቸው በጭብጨባ ከተቀቋረጠ በኋላ ሐሳባቸውን የቀጠሉ ሲሆን ሁሉም ዘርፎችን መንግሥት ባለው አቅም ሁሉ እየደጎመ ታክሲን ቸል ያለበት ምክንያት ከዚሁ የጠላትን ስሜት የመነጨ እንደሆነ እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡
“ለመንግሥት ሠራተኛ በሰበብ አስባቡ ደመወዝ ትጨምራላችሁ፣ የኛን ታሪፍ ለማሻሻል ግን አንድ ቀን እንኳ አስባቸሁ ታውቃለችሁ?” ሲሉ ጠይቀዋል፡፡
በዚህ አስተያየት የተበረታቱ ሌላ የታክሲ ባለንብረት የመናገር እድሉን ያገኙ ሲሆን “እዚህ አገር በሕዝብም በመንግሥትም እየተጠላን፣ ዘላለም እየተረገምን የምንሠራ እኛ ታክሲዎች ነን፡፡” ካሉ በኋላ “ተመስግነን አናውቅ፣ አትርፈን አናውቅ፣ ሕይወታችን ተለውጦ አያውቅ፡፡ እስቲ ከታክሲ ሥራ ተነስቶ እዚህ ደረሰ የተባለ ሰው ንገሩኝ” ሲሉ ታዳሚውን ጠይቀዋል፡፡
“እኔ ንግግሬን በሌላ አትውሰዱብኝና እኛ ታክሲዎች ጧት ተነስተን ባንሠማራ እኮ አገሪቷም ትቆማለች፡፡ መንግሥትም የሚሽመደመድ ይመስለኛል፣ ከናንተ ውስጥ ግን ይህን የሚያስብ ያለ አይመስኝም” ሲሉ ሐሳባቸውን ቋጭተዋል፡፡ ታዳሚውም በጭብጨባ ድጋፉን ገልጾላቸዋል፡፡
” ለመሆኑ የመኪና መለዋወጫ ዋጋን ታውቃላችሁ? ስፔርፓርት ስንት ነው?” በሚል ጥያቄ የሰነዘሩ ሌላ የታክሲ ባለንብረት፣ “ዛሬ አንድ ስፖኪዮ ቢሰበር ስንት ብር እንደሚያስወጣን ብታውቁ ደፍራችሁ እዚህ ባልጠራችሁን ነበር” ሲሉ ጠንከር ያለ ሀሳብ ሰጥተዋል፡፡
“ለነገሩ መንግሥት ሕዝብን መስማት ካቆመ ስለቆየ በናንተ አልፈርድባችሁም፤ እኛ ትዝ የምንላችሁ እኮ አድማ ስንመታ ብቻ ነው፤ ጃንሆይንም ታክሲ ነው ያወረዳቸው፣ ታሪክ ብታውቁ ደፍራችሁ እዚህ አትጠሩንም ነበር” ሲሉ አስተያየት የሰጡ አባት በመድረኩ አስተናባሪዎች ተግሳጽ ደርሶባቸዋል፡፡
” እዚህ መድረክ ስላገኘን ብቻ እንዳመጣልን መናገር ተገቢ አይመስለንም፡፡ ታክሲዎች ለሕዝብ አገልግሎት እንዲሰጡና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ ነው፡፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ገቢ ይቅርብኝ ብሎ ያለቀረጥ ከአንድ ሺ በላይ ታክሲዎች ወደ አገር ቤት እንዲገቡ የተደረገውም በዚህ ምክንያት ነው፡፡ የትርፍ ህዳጋችን መጨመር አለበት፣ ሥራው በሚፈለገው መልኩ እያተረፈን አይደለም የሚለው ተገቢ ጥያቄ ነው፡፡ እኛ ካመጽን አገር ትቆማለች ማለት ግን ኃላፊነት የጎደለው ንግግር ነው፤ መንግሥት እናንተ የምታገኙት ትርፍ ወቅቱን ያገናዘበ እንዳልሆነ ይረዳል፡፡ ለዚህም ጥናት እያደረገ ነው፡፡ በዚህ ዓመት የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ እየሠራ ነው፡፡” የሚል ምላሽ ከመድረክ መሪዎች በአንዱ ተሰጥቷል፡፡
በተለይም መንግሥት እኛን እንደተቃዋሚ ፓርቲ እንጂ እንደ አገልግሎት ሰጪ አድርጎ አይመለከተንም ላላችሁት ግን በየ ታክሲ ውስጥ የተለጠፉ አመፅ ቀስቃሽ ፅሁፎች እንዳለ እናካለን እናም ይህንን አመፅ ቀስቃሽ የሆኑና ህዝብን የሚያበጣብጥ ፅሁፍ ባስቸካይ እንድታስወግዱ መባላቸውን ከተሳታፊዎቹ አንዱ ገልፆልናል።
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s