አርበኞች ግንቦት ሰባት በህወሃት መከላከያ ጥበቃ እየተደረገለት አመልድ የመስኖ ፕሮጀክት ዋና መጋዘን አቃጠልኩ አለ

አርበኞች ግንቦት ሰባት የጀመረውን ትግሉን ይበልጥ በማስፋትና በማጠናከር በህወሃት መከላከያ የሚጠበቀውን በሰሜን ጎንደር ዞን ደንቢያ ወረዳ ጎርጎራ ከተማ ያለዉ የአመልድ የመስኖ ፕሮጀክት ዋና መጋዘን እና ጽ/ቤት ሙሉ በሙሉ ጋይቷል። በዛሬው ቀን ሚያዝያ 24/ 2009 ከጠዋቱ 4፡00 ሲሆን በከፍተኛ ጥበብና ስልት ወደ ድትጅቱ ሰርገው የገቡ የአግ7 ታጋዪች ልዩ ጥበብ በመጠቀም ነው ጥቃቱን የፈፀሙት ።

አመልድ በብአዴን የሚመራ የልማት ድርጅት ነው ቢባልም ከፍተኛ ፕሮጀክቶችን ከቻይናዎች በመውሰድ ወደ ገንዘብ ሰብሳቢነት በመግባቱ በጥረት ስር መንቀሳቀስ የጀመረ ድርጅት ነው። በመሆኑም ከባለፈው ጥቃት በኃላ በህወሃት መከላከያ ጥበቃ እየተደረገለት ይገኛል። የአግ7 ታጋዩች ይህን ጥብቅ ጥበቃ በማለፍ ነው ጥቃቱን ያደረሱት በጥቃቱ መጋዙኑ በውስጡ ከነበረው በርካታ ጀኔሬተሮች፣ ኮምፕዩተሮች ፣ ነዳጅ የያዙ በርሚሎች ፣ የፅሕፈት መሳሬያዎች ፣በርካታ የተሽከርካሪ እና የሊሎች መለዋወጫ ቁሳቁሶች የወደሙ ሲሆን የሰራተኞች ቢሮም ወድማል ከጎኑ የነበሩ የቻይናዎች ቢሮም በጥቃቱ እብሮ ወድማል ። የደረሰው ጉዳት በገንዘብ ሲሰላ በብዙ ሚሊዎን ገንዘብ ይገመታ። በወቅቱ በጥበቃ የነበሩ ወታደሮች ውድመቱን ከማዳን ይልቅ በድንጋጤ ወደ ህዝቡና ወደ ሰማይ ይተኩሱ ነበር ጥቃቱን የፈፀሙት ታጋዩች በሰላም ወደ ቦታቸው ተመልሰዋል።

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo