ሰሜን ጎንደር በወገራ ወረዳ የወያኔ ጦር ከገበሬዎቹ ጦር ጋር ከባድ ጦርነት አካሄዱ

04356-barefoot2btplf2bsoldiers2b-2bethiopia

የወገራ ገበሬዎች የወያኔን ጦር ሰብረው በሰላም ወጥተዋል፤ በሰሜን ጎንደር በወገራ ወረዳ የእንቃሽ ገበሬዎችን ለማፈን በሌሊት የተንቀሳቀሰው የወያኔ ሙሉ መካናይዝድ ጦር ዛሬ የካቲት 7 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 12.00 ጀምሮ ከበባ አድርጎ ነበር፡፡ ከቦታው መረጃውን የሰጡን የአካባቢው ገበሬዎች እንደሚሉት ጠዋት ከመኝታቸው ከመነሳታቸው በፊት ነበር የወያኔ ጦር ከገበሬዎቹ ላይ ጦርነት የከፈተው፡፡
ገበሬዎቹ በጎበዝ አለቆቻቸው አማካይነት እስከ እኩለ ቀን ድረስ ሲዋጉ ከዋሉ በኋላ የወያኔ ጦርን ከበባ ሰብረው ለመውጣት ችለዋል፡፡ አሁን ላይ በጫካ ተበትነው እንዳሉ የሚናገሩት የጎበዝ አለቆች ‹‹በሰላም ወጥተን መግባትም ሆነ ሰላማዊ ሕይወታችን መቀጠል አልቻልንም፤ አሁንም በጫካ ተበትነን ነው ያለነው›› ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ባገኘነው መረጃ መሰረት እስካሁን በሰውና በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም የወያኔ ጦር ኃይሉን አጠናክሮ በአካባቢው እንደሚገኝ ተገልጧል፡፡ ‹‹ማዶ ለማዶ እየተያየን አለን›› ሲሉ ከቦታው ያገኘናቸው አባት ተናግረዋል፡፡

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s