በጃዊ ባለፈው ሳምንት 37 የሚሆኑ አጋዚ ወታደሮች ተገድለዋል

ባንኮች ከ10 ሺህ ብር በላይ ወጪ እንዳያደርጉ እቀባ ተጥሏል፤ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ 2.3 ቢሊዮን ብር ደንበኞች ከባንኮች አውጥተዋል
 ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚደረግ በረራ ሁሉ በመከላከያ እውቅና እንዲሆን ተደርጓል
ጎንደር፤ ዛሬ ጳጉሜ 4 ቀን 2008 ዓ.ም. ከጠዋቱ 1፡00 ጀምሮ የመብራት፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በጎንደር ከተማ በማቋረጥ ከአየር ማረፊያ ጀምሮ በሁሉም ቀበሌዎች የአጋዚ ጦር አባላት ቤት ለቤት በመግባት መሣሪያ በመፈተሸ ሲቀሙ ውለዋል፤ የመገናኛ ዘዴዎች ሁሉ በመቋረጣቸው ብሎም ወጣቶች መነጋገር ባለመቻላቸው የተነሳ ቁጥራቸው የማይታወቅ በርካታ ዐማሮች መታሰራቸው ተሰምቷል፤ የባጃጅና የታክሲ ትራንስፖርት በግዴታ እንዲቆም ተደርጎ መረጃ ቶሎ ቶሎ እንዳይደርስም ጥረት ተደርጓል፡፡
ጎንደር በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የመከላከያና የፖሊስ አባለት የተጥለቀለቀ ሲሆን ከፍተኛ የትግሬ ወታደራዊ መከነኖች ፍሎሪዳ ሆቴል ይህ ሪፖርት እስከ ተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ስብሰባ ላይ ነበሩ፡፡
በተያያዘ ዜና አራዳ የሚባለው የገበያ አካባቢ የዐማራ ወጣቶችና በአጋዚ ወታደሮች መካከል ፍጥጫ መኖሩን መረጃው ደርሶናል፡፡ የጎንደር ወጣቶች ወንድሞቻችን አሳልፈን አንሰጥም እያሉ ሲሆን ከባሕር ዳርና ከቻግኒ ወደ ብር ሸለቆ የተወሰዱ ወጣቶች ከፍተኛ ስቅይት እየደረሰባቸው እንደሆነም እየወጡ ያሉ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
ከጎንደር ከተማ ዛሬ ነው የወጣነው የሚሉ ሰዎች እንደነገሩን የመረጃ አውታሮችን ሙሉ በሙሉ በመቆለፍ የጎንደር ከተማን ዳግም ወደ ዕልቂት ለመውሰድ የታለመ ይመስላል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡
ጃዊ፤ በጃዊ ነዋሪውን በማሰርና በማንገላተት ላይ በነበሩ 37 የሚሆኑ የትግሬ መከላከያ ሠራዊት አባላት በሳምንቱ መጀመሪያ አካባቢ መገደላቸውን ተሰምቷል፡፡ ቁጥራቸው ያልታወቁ ወታደሮች ደግሞ ጃግኒ ሆስፒታል ለእርዳታ መምጣታቸው የታወቀ ሲሆን እስካሁን ድረስ በአካባቢው ይህ ነው የሚባል ሰላም የለም ብለዋል መረጃውን ያቀበሉን ምንጮቻችን፡፡
አጠቃላይ፤ በአገሪቱ ያሉ ባንኮች አንድ ደንበኛ በቀን ከ10 ሺህ ብር በላይ እንዳያወጣ በአገዛዙ ታዘዋል፡፡ ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ ከ2.3 ቢሊዮን ብር በላይ ከንግድ ባንኮች ደንበኞች ገንዘባቸውን ወጪ አድርገዋል፡፡ ይህም በጥቂት ቀናት ብቻ የባንኮች ካዝና ባዶ ይሆናል በሚል ስጋት አገዛዙ ደንበኞች በቀን የሚያወጡትን የገንዘብ መጠን እንዲወስ እንዳስገደደው ምንጮች ገልጸዋል፡፡ በአዲስ አበባና በአንዳንድ ትልልቅ ከተሞች 10 ሺህ ብር ይባል እንጅ በብዙ የወረዳና የዞን ከተሞች ከአንድ ሺህ ብር በላይ ገንዘብ እንዳያወጡ ታግደዋል፡፡
በባሕር ዳር ያሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ለደንበኞቻቸው ለመክፈል ከግል ባንኮች እየተበደሩ እንደሆነም ለማወቅ ችለናል፡፡
በተያያዘ መረጃ ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የሚደርገውን በረራ ሙሉ በሙሉ በመከላከያ ሚንስትር እውቅና እንዲሆን ተወስኗል፡፡ አንድ የመንገደኞች አውሮፕለን ከመነሳቱ በፊት በየአካባቢው ያሉ የትግሬ መከላከያ ክፍለ ጦሮች እውቅና ከተሰጠ በኋላ ነው ተብሏል፡፡ ከኢትዮጵያ ሲቪል አቬየሽን መሥሪያ ቤት ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ተጠልፈው ድንበር የሚሻገሩ የአውሮፕላን አብራሪዎችን በመፍራት የሲቪል አቬሽን መስሪያ ቤት ምንም ሥራ በመከላከያ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

13942395_10205155496405616_1008799724_n

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s