የህወሃት ደህንነቶች በአዲስ አበባ ቦምብ ለማፈንዳት እያሴሩ ነው

በህወሃት ሥርዓቱ ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ለማስቆም ወይም የሕዝቡን ስሜት ለማስቀየር መወሰድ በሚገባቸው እርምዳዎች ላይ ምክክር ሲደረግበት መቆየቱን ከደህንነቱ መሥሪያ ቤት የሾለከው መረጃ ያመለክታል።
በዚሁ የሴራ ስብሰባ ላይ ለደህንነት መሥሪያ ቤቱ ስጋት መባባስ ውጫዊ ምክንያቶችም መኖራቸው በስፋት ተነስቷል። የአሜሪካና የእንግሊዝ ኤምባሲዎች ለዜጎቻቸው ባወጧቸው መግለጫዎች ወደተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች እንዳይንቀሳቀሱ የጉዞ ማስጠንቀቂያዎች ሰጥተዋል።
የአገዛዙ የደህንነቱ መሥሪያ ቤት ወደፊትም አዲስ አበባም ተመሳሳይ ጥቃት ሊደርስባት ይችላል የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሱን የጠቀሱት ምንጮች፤ በስብሰባው ላይ ለዚህ በመፍትሄነት ከቀረቡት አስተያየቶች አንዱ የደህንነቱ መሥሪያ ቤት አዲስ አበባ ውስጥ በሰላማዊ ዜጎች ላይቦምብ በማፈንዳት እና ሰላማዊ ዜጎችን በመፍጀት በአርበኞች ግንቦት 7 ላይ ማላከክ ነው መባሉን ይገልጻሉ።
በመሆኑም የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በዘወትር እንቅስቃሴዓቸው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መረጃ አቅራቢዎቹ አሣስበዋል።
አገዛዙ እንዲህ ዓይነት ድምዳሜ ላይ የደረሰው ዛሬ በጎንደርና በጎጃም የሚታየው ሕዝባዊ አመጽ ነገ አዲስ አበባን ጨምሮ ወደ መላው ኢትዮጵያ እንደሚሰራጭ ስለሚያውቅ ነው ያሉት አንድ ከፍተኛ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራር፤የአዲስ አበባ ብቻ ሳይሆን የመላው ኢትዮጵያ ሕዝብ ከሽብርተኛው የህወሓት አገዛዝ ራሱን እንዲጠብቅና ለተባበረችና ፍትህ ለሰፈነባት ኢትዮጵያ ከድርጅታቸው ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።efe30-handgrenade

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s