ኮማንደር ሙሉጌታ አያልነህን ጨምሮ ሌሎች ሶስት የፀጥታ ሀላፊዎች ከሀላፊነታቸው ተነሱ

እስከ ባለፈው ጥቅምት ወር ገደማ የአማራ ክልል የወንጀል መከላከል ዘርፍ ሃላፊ ሆኖ ያገለገለው እና የባህር ዳር አለመረጋጋት ከእለት ወደ እለት ስለተባባሰ ወደከተማው ያዞሩት የልዩ ዞኑ ፖሊስ ኮሚሽን ኮማንደር ሙሉጌታ አያልነህን ጨምሮ ሶስት የፀጥታ አመራሮች ከሀላፊነታቸው መነሳታቸው ተነገረ።

ሰሞኑን ባህር ዳር ከተማ በተካሄደው “የፍትህ ሳምንት” ምክንያት አድርገው የፀጥታ ሀይሉን እርስ በርሱ እንዲገማገም አድርገው ነበር ይታወቃል።

እንደዚህ አይነት ጊዜ ያልተሰጠው የአጭር ጊዜና ሰፊ ህዝብ የሚሳተፍበት ውይይት የሚካሄደው ቀድሞውንም ለመምታት የተዘጋጀ አካል ሲኖር ነው ተብላል።

በዚህ መሰረትም የባህር ዳርን ህዝብ ለህወሃት በማቀበል፣ ራሳቸውም በደል በመፈፀምና በማስፈፀም የሚታወቁ የስርዓቱ የቀኝ እጅ የነበሩ ሁሉ ባልተጠበቀ ሁኔታ እዛው መድረክ ላይ ከሀላፊነት እንደተነሱ ተነግሯቸው ደብዳቤ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸው ተነግራል።

የባህር ዳር ሰላም አለመስፈን  ያስጨነቀው ህወሃትና ለስልጣኔ ያሰጋኛል ያለው ብአዴን እነዚህ ሰዎች ላይ እርምጃ ወሰድኩ ማለቱ ምን አይነት ፋይዳ እንዳለው ባይታወቅም ለህብረተሰቡ ግን ቢያንስ በስልጣን ሽግግር ወቅት እስራቱ ሊቀንስ ይችላል ተብሎ አይጠበቅም።
የሆነው ሆኖ ግምገማው “የባህር ዳርን ሰላም ማስጠበቅ አልቻላችሁም” በሚል የፖለቲካ አመራሩ ራሱን ከደሙ ንፁህ ለማድረግ የሄደበት መሆኑ ግልፅ ማሳያ ነው ተብላል።

ከላይ የመጣን ትዕዛዝ እንዳለ የሚፈፅመው ብአዴን ችግሩን ከምንጩ ከማየት ይልቅ ውጤቱ ላይ ብቻ በማተኮሩ ለውጥ እንደማያመጣ አሁንም ቀድሞ መተንበይ ይቻላል።
በአሁኑ ከሀላፊነት ከተነሱት ውስጥ ከነሀሴ ጀምሮ በአይነቁራኛ ሲታይ የነበረው የኮማንደር ሙሉጌታ አያልነህ ግምገማና መልስ አስገራሚ ነበር ተብሏል።

የመረጃ ምንጮቻችን ኮማንደሩ ከየካቲት ወር ጀምሮ ምክንያታዊ ባልሆኑ ነገሮች ሰዎችን ዝም ብሎ ማሰር መቆም አለበት ማለቱ (የቀበሌ 13 ወጣቶች እንዲፈቱ አደርጓል የሚልም ጭምጭምታ አለ) ከሀላፊነቱ እንዲነሳ መደረጉን በምክንያትነት ቢያስቀምጡም

በግምገማው እለት “ለድርጅታዊ አሰራር ቅድሚያ አትሰጥም” በሚል የራሱ ድርጅት አባላት ያነሱት ሀሳብም ዋናው ጭብጥ ይሆናል ማለት ይቻላል።
ኮማንደሩ በበኩሉ “ከድርጅታዊ አሰራር ይልቅ እኛ ሲቪል ስለሆን ህዝባዊነት ይቀድማል” የሚል የመከራከሪያ ሀሳብ አንስቷል ተብሏል።
ከእርሱ በተጨማሪ ኮማንደር ውበቱ አለ፣የምርመራ ክፍል ኃላፊውን ኮማንደር እንየው እና የመረጃ ክፍል ኃላፊው ዋና ኢንስፔክተር መኮንን አለነን/ ከኃላፊነታቸው እንዲዎገዱ አድርጓል።
ከኃላፊነት ለመነሳታቸው ምክንያት የተደረገው የከተማውን ፀጥታ መቆጣጠር አልቻላችሁም በሚል ሲሆን በአማራ ህዝብ ላይ በተለይም ባሕርዳርና ሌሎች አማራወጣቶች ላይ በዙ ግፍ መፈፀማቸውን የመረጃው ምንጮቻችን ይጠቅሳሉ።
ከዚህ ስብሰባ ጎን ለጎን ስጋት የገባው ህወሃት ተወካይዎቹ አባይ ፀሀየን እና ስብሃት ነጋን ባህር ዳር ከትመዋል ተብላል።

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s