ፍርድ ቤቱ የቀድሞ አንድነት ፓርቲ ም/የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሽ ክሱን እንዲከላከል ብይን ሰጠ፤ አቶ አብርሃ ደስታ ታስሮ እንዲቀርብ ተባለ!!!

በእነ ዘላለም ወርቅአለማሁ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው በነፃ የተሰናበተው አቶ ዳንኤል ሽበሺ ተከላከል ተባለ፡፡የፈደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ በነፃ እንዲለቀቁ የሰጠውን ብይን በመቃወም የፌደራል ዓቃቢ ህግ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መዝገቡን በድጋሜ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት መምራቱ ይታወቃል፡፡ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት አቶ ዳንኤል ሺበሽ ክሱን እንዲከላከል ጉዳዩንም ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ሆኖ እንዲከታተል ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡በዚሁ መዝገብ የተከሰሰው አቶ አብረሃ ደስታ በዛሬው ቀጠሮ ባለመቅረቡ በቀጣይ ቀጠሮ ለግንቦት 15 ቀን 2009 ዓ.ም ታስሮ እንዲቀርብ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

በተመሳሳይ ለብይን ተቀጥሮ የነበረው አራት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራሮች ማለትም አቶ በቀለ ገርባ፣አቶ ደጀኔ ጣፋ፣አቶ አዲሱ ቡላላ እና አቶ አያኖ ጉርሜሳን ጨምሮ 22 ተከሳሾች መዝገብ በድጋሜ ተቀጠረ፡፡ብይኑ ያልተሰጠው ያልተያያዘ መረጃ በመኖሩ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ገልጧል፡፡መረጃውን አያይዞ ብይን ለመስጠት ለግንቦት 30 ቀን 2009 ዓ.ም በድጋሜ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s