በሰዓሊተ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በተደረገው የፕሮቴስታንቶች ርኵሰትተጠያቂ መኾን ያለባቸው ፓትርያርኩ ናቸው፡፡

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጁ አጥማቂ ፍለጋ ከአባቶቻቸው ይልቅ ወደ ፕሮቴስታንቶች ማዘንበላቸውን በራሳቸው አንደበት ተናገሩ፡፡ በሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንደተከናወነ የተነገረው ቅብዓት አይሉት ጥምቀት በእርሳቸው ብቻ ሳይኾን በፓትርያርኩ ቡራኬ ሰጪነት የተከናወነ መኾኑ አነጋጋሪ ነው፡፡

እኛ እነርሱን ስናጠምቅም ይሁን ስንቀባ ብንገኝ ደግ በኾነ፤ አንድ ፓስተር ብድግ ብሎ አንድን በቁምስና ማዕርግ ያለ የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛው አስተዳደር ውስጥ ተዋናይ የኾነን ሰው ሲቀባም ይሁን ሲያጠምቅ ማየት ከየት እንደመጣ እስካሁን ማንም አልነገረንም፡፡ ለጊዜው የነገሩ ሙሻዙር ወደ ም/ሥ/ አስኪያጁ ያጠንጥን እንጂ ዋናው ተጠያቂ መኾን ያለባቸው ፓትርያርኩ ናቸው፡፡ ሰውየው አድርግ የተባሉትን አድርገው ይኾናል፡፡ ይህም መለካዊነታቸውን ከሚያሳብቅባቸው በቀር ከተጠያቂነት ነፃ ያደርጋቸዋል ማለት አይደለም፡፡

እንኳን በማዕርገ ቁምስና በምእመን ደረጃም እንዲህ ያለ የሚፈጽም በሌለባት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይህን የኃፍረት ካባ ሊያከናንቡን መቁረጣቸው ብርቱ ጽዩፍ አድራጎት ነው፡፡ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ለማን እንዴት መቼ እንደሚፈጸም በጉልህ የምታስተምርን ቤተ ክርስቲያን በቅጽሯ ውስጥ ነውረኛ ሥራ በማድረግ መሠማራት አደጋው ቀላል አይደለም፡፡ “የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩ፥ አንባቢው ያስተውል” ያለውን ልብ እንበል፡፡ ማር ፲፫፥፲፬።

ለመኾኑ እርሳቸው አሉ እንደሚባለው ጉዳዩ የተከናወነው በውኃ ነው ከተባለ፤ ጥምቀቱ ለልጅነት ነው ወይስ ለፈውስ? ቤተ ክርስቲያን የሰጠቻቸውን ልጅነት የት ጥለውት ይኾን? አሞኝ ነው ካሉ ደግሞ ጠበል ቤት እንጂ ኪታ ለባሽ ፓስተር ይዞ ወደ መቅደስ መግባትን ምን አመጣው? ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በየትኛው አንቀጽ እንደሚወድቅም ሊነግሩን ይገባል፡፡ ኢኩሚኒካል ግንኙነትን ስለማጠናከር ነው ከተባለም በምሥጢር ተካፋይነት የሚፈጸም አይደለም፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንኳን ለመናፍቅ ትምህርተ ክርስትናን በመከታተል ላይ ያሉ ባለ ተስፋዎችን በቅዳሴ ጊዜ ምሥጢር ለመካፈል የበቁ አይደሉምና (ማለትም አልደረሱምና) ፃዑ ብላ ታሰናብታለች፡፡ እኒህን ጳጳስ አደርጋለሁ ብሎ . . . መነሣት ነገ ደግሞ ማንን አምጥተው በማን እንዲቀቡ ይኾን? ከአባቱ ውጭ ሌላ አባት መፈለግ . . .

በሰውየው ላይ ብዙ ችግር እንዳለ እየታወቀ ብዙ ጊዜ በዝምታ ታለፉ፡፡ አሁን ብለው ብለው በአደባባይ ቤተ ክርስቲያንን የማይመጥኑ መኾናቸውን በይፋ አጋለጡ፡፡ የሰውን ዲዘርቴሽን ግትም አድርገው ገልብጠው ፒኤች ዲ አለኝ ሲሉ ኖሩ፡፡ ዝም ተባሉ፡፡ በሆለታ ገብርኤል አካባቢ ያለባቸውን ብዙ ነውረኛ ሥራ ሲሠሩ ኖሩ ዝም ተባሉ፡፡ አሁን ደግሞ ሌላ . . .

በቅርቡ ቅዳሴ ረዘመ ብለው በሸገር ሬድዮ ሲነዛነዙ የነበሩት ፓትርያርክ አሁን ደግሞ እንዲህ ባለ ተግባር ላይ መሰለፋቸው ሒደቱን በጥሞና የሚያየው አካል ይፈልጋል፡፡ የእናት ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እንዲህ በዋዛ በዋዛ እየታለፈ መቀጠል የለበትም፡፡ የሃይማኖት ጉዳይ ቀስ በቀስ እንዲሸረሸር ብርቱ ጥረት የሚደረግ ይመስላል፡፡ በሰዓሊተ ምሕረት በተደረገው ይህ ኩነትም እንደ ደኅና ነገር ጳጳስ አስከትለው የደብር አለቆችን ጠርተው ታዳሚ ኾኖ መገኘት ምን ይሉታል? ቅዳሴው እንዲያጥር የሚከራከሩት ሰው ቀድሞም ቢኾን ምክሩን ያገኙት ከአንድ የፕሮቴስታንት ፓስተር እንደነበር ነግረውን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ፓስተሮቹን ወደ ቤተ መቅደስ ይዘዋቸው ገቡ፡፡

በአሁኑ የግንቦቱ (፳፻፱) ሲኖዶስ ጉባኤ መካከል አንዱ ተነሥተው “መሠረት ስብሐት ለአብ መናፍቅ አይደለም” ብለው ድምፅ አሰምተዋል መባሉ ሌላው አነጋጋሪ ጉዳይ ነው፡፡ አለማወቅ እንዲህ ካለ ድፍረት ያደርሳል፡፡ ክርስቶስ አማላጅ ነው ብሎ የቅዱሳንን ሥራ ለእግዚአብሔር ሰጥቶ የተናገረን ሰው መናፍቅ አይደለም ብሎ መከራከር ምን ይሉት ጥብቅና ነው፡፡ ሰውየው ሔደው የሙጥኝ ብለው የተጣበቁበት ድርጅት ምን ብሎ የሚያስተምር እንደኾነ በገሃድ እየታወቀ ለክርክር መሰናዳት ምን ይባላል?

የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን አቋም የሚሸራርፉትን በጥብቅ የሚቃወሙት አቡነ ቄርሎስ የሰጡት ምላሽ አንጀት አርስ ነው፡፡ የሚቅበዘበዝ ሀሳብ የሚያመጡትን እዚያው መገሠፁ የተገባ ለመድረኩ የሚመጥን ነውና፡፡ ግን እንዲሁ በቀላሉ መታየት አለበት ተብሎ መወሰድ የለበትም፡፡ ያንን ቃል የተናገሩት ጳጳስ ናቸውና በሀገረ ስብከታቸውም ብዙ ሃይማኖታዊ ውዝግብ እየፈጠሩ የሚገኙ ናቸውና ጉዳያቸው ለብቻ መታየት ይገባዋል፡፡ እኒህን ጳጳስ ሰውየው ራሱ ቢሰማቸው እንዴት በሳቀባቸው፡፡ ጥብቅናውን አይፈልገውም፡፡ ይብላኝ ለእርሳቸው እንጂ በአደባባይ ማንነቱን ደጋግሞ የተናገረ “ምስጉን” መናፍቅ ነው፡፡ ታዲያ ለሞተ ሰው ጥብቅና መቆሙን ምን አመጣው? ነገር ዝም ብሎ አይመዘዝምና ደጋግሞ ማጤኑ ይበጃል፡፡

እነዚህ ሦስት ጉዳዮች በለበጣ የሚታዩ አይደሉም፡፡ ይታሰብባቸው!

Image may contain: 1 person, indoor
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s