ለዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት ዳይሬክተርነት የሚወዳደረው ቴድሮስ አድሃኖም የመመረጡ ጉዳይ አደጋ ገጥሞታል ተባለ

ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ሜይ 13፤2017 ዓም “የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅትን ለመምራት የሚወዳደረው እጩ ወረርሽኝ በመደበቅ ተከሰሰ” በሚል ርዕስ ባስነበበው ዜና የቴድሮስን የመመረጥ ተስፋ ስለሚያጨልመው የኮሌራ ወረርሽኝ ምሥጢር በዝርዝር አትቷል፡፡

በያዝነው የግንቦት ወር (ከሜይ 22፣ 2017) ጀምሮ በጄኔቫ በሚካሄደው የአንድ ሳምንት ስብሰባ ድርጅቱን ለመምራት ከሚወዳደሩት ሦስት እጩዎች (ቴድሮስን ጨምሮ እንግሊዛዊው ዶ/ር ዴቪድ ናባሮና ፓኪስታናዊቷ ዶ/ር ሳኒያ ኒሽታር) መካከል አንዱ የዳይሬክተርነቱን ቦታ ይወስዳል፡፡ ስብሰባው ሊጀመር አንድ ሳምንት አካባቢ ሲቀረው በቴድሮስ ላይ የቀረበው ይህ ክስ ራሱንም ያስደነገጠው ይመስላል፤ “አልገረመኝም ግን ቅሬታን አሳድሮብኛል፤ ይህ ባለቀ ሰዓት የሚካሄድ የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው” ብሎታል፡፡

ምሥጢሩን ይፋ ያደረጉት የቴድሮስ ተፎካካሪ የሆኑት የዶ/ር ናባሮ ኢ-መደበኛ አማካሪና በጆርጅ ታውን ዩኒቨርሲቲ የኦኒል የብሔራዊና ዓለምአቀፍ የጤና ሕግ ተቋም ዳይሬክተር የሆኑት ሎውረንስ ጎሰቲን ናቸው፡፡ ጎስቲን እንደሚሉት ቴድሮስ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በነበረበት ዓመታት (2005 – 2012) እኤአ በ2006፣ 2009 እና 2011 በኢትዮጵያ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ ይፋ እንዳይሆን በምሥጢር እንዲያዝ አድርጓል፤ ይህም ዓለምአቀፉን የጤና ጥበቃ ድርጅት እንዳይመራ ከበቂ በላይ ምክንያት መሆን ይችላል የሚል መከራከሪያ ነው፡፡

ዶ/ር ናባሮ ስለጉዳዩ ሲጠየቁ “እኔ በጭራሽ ይህንን አላውቅም፤ ዶ/ር ቴድሮስ ብቃት ያለው የጤና ባለሙያ ነው፤ ጎስቲን ይህንን የተናገረው እኔን ሳያማክር ነው፤ ሆኖም ግን ቴድሮስ እውነቱን መናገር፤ ለረጅም ጊዜ የተከሰተውን የኮሌራ ወረርሽኝ ሪፖርት ማድረግ፤ ለእውነት መናገር ይገባዋል” በማለት ከቻይና በስልክ ለኒው ዮርክ ታይምስ ተናግረዋል፡፡ ጎስቲን ከኢመደበኛ አማካሪነት በተጨማሪ ከናባሮ ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያላቸው መሆኑ ቢታወቅም ጎስቲን ይህንን ያጋለጡት ለዓለምአቀፉ ድርጅት ከመቆርቆር የተነሳ መሆኑ ተነግሯል፡፡

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s