ወንድማችን ዲያቆን ታደሰ ወርቁን ዛሬም እግዚአብሔር ከግድያ ሙከራ አተረፈው!

 

ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት ፲፭ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም. ከምሽቱ ፲፪ ሰዓት ገደማ ከአድዋ ድልድይ ወደ መገናኛ በሚሔደው ጎዳና ወደ ጉርድ ሾላ እና ወደ ለም ሆቴል በሚያቋርጠው መንገድ ጫፍ ላይ ከፖሊስ ጣብያው አጠገብ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ታርጋው የንግድ መኪና በኾነ ብርማ ቀለም ባለው ኮሮላ ውስጥ የነበሩ ሰዎች ድንገተኛ ጥቃት አድርሰውበት በፍጥነት ተሰውረዋል፡፡ በእግሩ በመሔድ ላይ ሳለ በመኪናው ውስጥ ከነበሩት መካከል ጋቢና በቀመጠው ሰው አማካኝነት የግድያ ሙከራ ተደርጎበታል፡፡

ከየት መጣ ሳይባል ወደ ታደሰ የቀረበው መኪና ድንገት በሩን በኃይል ከፍቶ በመንገድ ዳር የነበረውን ወንድማችንን አሽቀንጥሮ በመምታት ወደ መሬት ጥሎታል፡፡ በዚህ ወቅት በአካባቢው የሚተላለፉ ሰዎች ስለነበሩ ወዲያው ከወደቀበት ያነሡት ወንድማችን ለጊዜው ከደረሰበት አስደንጋጭ ክስተት በስተቀር በአካሉ ላይ የደረሰ ጉዳት የለም፡፡ እነዚሁ ሰዎች የዛቻ ምልክት በእጃቸው እያሳዩ በፍጥነት ከአካባቢው የራቁ ሲኾን እነማን እንደኾኑ ለመለየት ግን አልተቻለም፡፡

ከዚህ ቀደም በመኖሪያ ቤቱ አካባቢ ከደረሰበት ጥቃት የተረፈው ወንድማችን አሁንም የጥቃት ሰለባ እንደኾነ ይገኛል፡፡ በጠንካራ ትችቶቹ የሚታወቀውን ይህን ወጣት የቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ እንዲህ እየደጋገሙ የሚዞሩት እነማን እንደኾኑ መጠርጠር አይከብድም፡፡ ከኹለት ወይም ከሦስት አቅጣጫ ሊኾን እንደሚችል ይገመታል፡፡

አንድ ነገር ግን ቁርጥ ነው፡፡ ጥቃት አድርሻቹ ማንም ይሁኑ ማን እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ እነርሱ ሊሰሙ ከቶውኑ አይችሉም፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ እና ቅዱስ ዮሐንስ በጌታችን ስም እንዳያስተምሩ ስሙን እንዳይጠሩ ባለጊዜዎቹ ከዛቻ ጋር እያስፈራሩ ሊያዝዟቸው ሲሞክሩ “እግዚአብሔርን ከመስማት ይልቅ እናንተን እንሰማ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት የማይገባ እንደኾነ ቍረጡ” በማለት ውልውል የሌለበት ውሣኔአቸውን ተናግረዋል፡፡

በዚህ መንገድ ክርስትናን ማሸማቀቅ ተሞክሮ ያልተሳካ እንደኾነ አያውቁም እና ከኹለት ሺህ ዓመታት በፊት በነበረው ሰይጣን የሠለጠኑ ሰዎች ዛሬም ሥራየ ብለው ይዘውታል፡፡ እነርሱ ተስፋ ይቆርጣሉ እንጂ ክርስቲያኖች ምንጊዜም ተስፋቸው ብሩኅ ነው፡፡

ወንድማችን ሰሞኑን “ቁርቁር ሲኖዶስ” በሚል ርእስ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር ዙሪያ ጠንካራ ትችት ሰንዝሮ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ትችቱ በራሱ አነጋጋሪ መልክ ያለው ሲኾን በዚህ ቅር ሊሰኙ ከሚችሉ አካላት ጥቃቱ የተሰነዘረ ነው ብሎ መገመት ይቻላል፡፡ ያም ኾነ ይህ ወንድማችን በመትረፉ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን፡፡ እንደዚህ ዓይነት የወርሮ በላ ሥራ በመሥራት ክርስትና አይቆምም፡፡ ይልቁንም ቀረብ ብሎ ሐሳቡን በመስማት የሚበጀውን እየያዙ ማረም መታረም እንጂ በተለያየ ካባ እየዞሩ ሰውን ለማሸማቀቅ መድከም እጅግ በጣም የወረደ አሳፋሪ ድርጊት ይኾናል፡፡ የመውጊያውን ብረት ብትረግጥ ለአንተ ይብስብሃልና!

Image may contain: 1 person
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s