“የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ” ውድ ኢትዮጵያውያን አስተውሉ!!!

በኛ አቆጣጠር በ 2007 ዓ.ም በጋዜጠኛና ደራሲ ፍስሀ ያዜ የተጻፈ “የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ “የተሰኘ መጽሀፍ አይተናል አንብበናል።በዚያ መጻህፍ ውስጥ ስለ G8 አገራት ዝግ ስብሰባና በስብሰባው ስለ ኢትዮጵያ የተዶለተውን ሁሉ ቃል በቃል ጸሃፊው በመጽሀፉ አስፍሮታል ።መጀመሪያ ጸሀፊው እንደ እብድ ተቆጥሮ ነበር።መረጃው ከራሱ ከኦባማ አፕል ላፕቶፕ ላይ ከሁዋይት ሀውስ ተሰርቆ የወጣ እንደሆነ ደራሲው ሲነግረንም ስቀን ነበር።ብዙም ሳይቆይ ግን ደራሲው ያላቸው ብዙ ነገሮች ወደ ተግባር መለወጥ ጀመሩ። ያኔ መጽሀፉን ማግኘት እስኪሳነን ድረስ ፈለግነው ።ብዙ በመጽሃፉ የተገለጹ ነገሮች በተግባር መሆን ጀመሩ።
በስብሰባቸው ወቅት #የሩሲያው ፕሬዘዳንት እንደሌሎቹ መሪዎች ሳይዘል ሳይጨፍርና ሳይዳራ ቀንድም ሳያበቅል በሰብሳቢያቸው በሳጥናኤል ፊት ሳያጎበድድ የቀረ ብቸኛ መሪ እንደነበር በመጵሀፉ ተገልጾዋል።ይህ ለምን እንደሆነ ፍስሀ ራሱ አለመረዳቱንና የሩሲያው መሪ ተግባር ሊገባው እንዳልቻለ ገልጾልን ነበር።የሩሲያው መሪ በዚያ ንቀት የተሞላበት ተግባሩ የዋና ሰብሳቢውን የዘንዶውን ምክትል አቡነ ፍራንሲስን ሳይቀር እንዳስቆጣ ነግሮናል።አቡነ ፍራንሲስ አዳራሹ ውስጥ የሩሲያውን መሪ በክፉ ዓይናቸው እያዩ የተናገሩትንና ያጉረመረሙትን ቃልም ቃል በቃል ደራሲው አስነበቦናል።ይህም በወቅቱ ለመላው ኢትዮጵያዊ አንባቢ ግራ መጋባትን ፈጥሮ ነበር።በሚገርም ሁኔታ ይህ ከሆነ ከዓመት በሁዋላ ሩሲያ ከ G 8 አገራት አባልነቱዋ ተስረዘችና G 8 አገራት የሚባሉት G 7 መባል ጀመሩ።የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ የሚለው የፍስሀ ያዜ መጽሀፍ የተጻፈው በኛ አቆጣጠር በ2007 ነው።በ 2008 ሩሲያ ወጥታ G 7 ተባሉና ጉባዔውን ቀጠሉ።በዘንድሮው ዓመትም G 7 ሆነው ያለሩሲያ ሊቀጥሉ ነው።ስብሰባውም ከግንቦት 19 ጀምሮ ነው።በማይታመን ሁኔታ ኢትዮጵያ የ G 7 ስብሰባ ላይ ተጋባዥ አገር ሆና ልትታደም ነው።በጣሊያን ሮም በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ለመገኘትም ጠቅላይ ሚንስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሮም ሊያቀኑ ነው።ይህን ዜና ፋና ብሮድካስትና ሌሌች ይፋ አድርገዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የአሜሪካው መሪ ትራምፕ በዛሬው እለት በቫቲካን ተገኝቶ ከአቡነ ፍራንሲስ ጋር ተገናኝቶ ስለ አየር ንብረት ለውጥ እና ስለ አሸባሪነት ተወያይቶዋል።ልብ በሉ።የአሜሪካ መሪ አንድን ጳጳስ ስለ አየር ንብረት ለውጥና ስለ አሸባሪነት ሲያወያይ!ምክር ፍለጋ ነው ወይስ ጸሎት ፍለጋ?ያውም ግብረሰዶማውያንን በቤተክርስቲያኒቱ ህግ እንዲጋቡ ፈቅዶ እያጋባ ካለ ጳጳስ ጋር!
ስለ አቡነ ፍራንሲስ እና ስለ አሜሪካ መሪዎች ማንነትና ከፍራንሲስ ጋር ስላላቸው ግንኙነት እንዲሁም ዕቅድና ጎል ማንም ምንም በማያውቅበት ወቅት ነው ፍስሀ ያዜ ፍርጥርጥ አድርጎ ዛሬ እየሆነ ያለውን ነገር በሙሉ ገና ከመሆኑ በፊት የነገርንና ግራ አጋብቶ ሲያወዛግበን የነበረው።በዚህም ምን ማለቱ ነው?ሲባል የኖረው።እውነት እና ንጋት እያደር እንደሚጠራ እርግጥኛ ስለነበርም ነው በድፍረት ሊታመን የማይችልን እውነት ደፍሮ የነገረንና ያነቃን።ይህ በእንዲህ እንዳለም አላዋቂ ወገኖቻችን እንደ ድል የቆጠሩትን የዓለም ጤና ድርጅት የመሪነትን ስልጣንን ለኢትዮጵያ መስጠታቸውን ስናይ ምን እየተከናወነ እንዳለ ካልገባን እርግማን እንጂ ምንም ሊባል አይችልም።ይህ ጨለምተኝነት አይደለም።ኢትዮጵያ ሌላም ሌላም ለውጥ ላይ ብትገኝ የሚጠላ ዜጋ የለም።ነገር ግን ይህ ሀሉ የሚሆነው ኢትዮጵያ ተስፋ ኖሮዋት አድጋ ተለውጣና ሃያል ሆና አይደለም። ጫዋታው ሌላ ነው።ይህን ማለት ያስፈለገውም ጫወታው እምን ድረስ እንደደረሰ እናውቅና እናስተውል ዘንድ ብቻ ነው።
ልብ በሉ ቴድሮስ አድሃኖም እንኩዋ የገባቸው አይመስልም እንኩዋን ሌላው ደጋፊያቸው።ምን አሉ ካንሰርን፣ዚክ ቫይረስን፣እና ኢቮላን በአጭር ጊዜ አጠፋለሁ።ትብብራችሁንም እሻለሁ አሉ።ኢቮላ፣ዚክ ቫይረስ እና ኤች አይ ቪ የዓለም ጤና ድርጅት የፈበረካቸው በሽታዎች አይደሉምን?የዓለም ጤና ድርጅት የፈበረከውንና ሆነ ብሎ ያሰራጨውን በሽታ የዓለም ጤና ድርጅት ዳያሬክተር ሊያጠፉት!ያውም ያለ እውቀታቸው ያለ ችሎታቸው ያለ ተሞክሮዋቸው።.መድሃኒት በእርዳታ ካልመጣና እርዳታው ከተቁዋረጠ የምንሞትበት አገር ላይ ሆነው ምንነቱ ያልተለየን ዚክ እና ኢቮላን ማጥፋትስ ይቻላልን?በአንቡላንስ እጥረት ምክንያት ዜጎች በሚሞቱበት አገር ያሉ መሆናቸውን እያወቁ በሚንስቴር መ/ታቸው በኩል መቅረፍ ያልቻሉ ጭራሽ ኢቮላን ዚክን ቀልድ ይባላል ።
ስለዚህ ነገሮች በሙሉ እውነት ናቸውና መንቃትና መከታተል ብሎም ራሳችንና በዙሪያችን ያሉትን ወገኖቻችን ማንቃት ከሁላችንም የሚጠበቅ ጉዳይ ነው።
ለማንኛውም ኢትዮጵያ በ G 7አገራት ስብሰባ መገኘቱዋም ሆነ መመረጡዋ ትራምፕም ሆነ ፍራንሲስ፤ ጳጳሳቶቻችንም ሆኑ ሌላው ወቅታዊ ነገር ሁሉ በተባለውና አፈንግጦ ወጥቶ በአምላክ ፈቃድ በኢትዮጵያውያውያን እጅ እንዲገባ በተደረገው ቀድሞ በታወቀባቸው መረጃ መሰረት እየሆነ ያለ እንደሆነ አስታውሱ ለማለት እወዳለሁ።
ሼር ይደረግ!
#ቀረመንዝ ዐዛገ

Image may contain: 3 people, people smiling, text
Image may contain: 11 people, people smiling
Image may contain: 12 people, people smiling, people standing and wedding
Image may contain: one or more people, text and outdoor
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s