ለኤጲስ ቆጶስነት ምርጫ ተወዳድረው ያለፉት ዕጩ አባ ገብረ ሥላሴ ተስፋ ዘኢየሩሳሌም ብቁ አይደለሁም አሉ

” ከዚህ በላይ ሓላፊነት ለመጨመር ብቁ አይደለሁም ፤ በተሰጠኝ የክህነት ሥልጣን ከሠራኹበት ይበቃኛል” አባ ገብረ ሥላሴ ተስፋ (ዘኢየሩሳሌም)

11. Juni 2017 — አባ ገብረ ሥላሴ ተስፋ (ዘኢየሩሳሌም) በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ተጠቁመው፣ ለኤጲስ ቆጶስነት የታጩት አባ ገብረ ሥላሴ ተስፋ ዘኢየሩሳሌም፣ በሞያቸው የቅኔ መምህር ናቸው፤ በወንበር አስተምረዋል፤ ትርጓሜ መጻሕፍትም ያውቃሉ፡፡ በሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ከፍተኛ መንፈሳዊ ት/ቤትም ተምረዋል፡፡
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ፣ ግንቦት 10 ቀን ባካሔደው ምርጫ ተወዳድረው ካለፉት ዕጩ ቆሞሳት አንዱ የኾኑት፣ ቆሞስ አባ ገብረ ሥላሴ ተስፋ፣ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት አገልጋይ እንደኾኑና ከቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት በደብዳቤ እና በስልክ ለተላለፈላቸው ጥሪ፣ የጀመሩት ሥራ እንዳለ በመጥቀስ፣ ዕጩነቱን እንደማይቀበሉትና በሹመቱም ለመገኘት እንደማይችሉ ከዚህ በላይ ሓላፊነት ለመጨመር ብቁ አይደለሁም ፤ በተሰጠኝ የክህነት ሥልጣን ከሠራኹበት ይበቃኛል በማለት ማስታወቃቸውን አዲስ አድማስ፤ ቅጽ ፲፮ ቁጥር ፱፻፰፤ ቅዳሜ፣ ሰኔ ፫ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም በአወጣውን እትም ገልጻል
” ከዚህ በላይ ሓላፊነት ለመጨመር ብቁ አይደለሁም ፤ በተሰጠኝ የክህነት ሥልጣን ከሠራኹበት ይበቃኛል”
“የአበውን አሠረ ፍኖት የተከለተ አቋምና ምላሽ ነው” አስተያየት ሰጭዎች
…እኛም እንዲህ ያሉ አባት ተዋህዶን ይወክላሉ የአባቶቻችን አሰረ ክህነት እንዲህ ባለ ትህትናና ልዩ ፍቅር የተከተለ ነው እንላለን
…ይፍቱን አባ ቡራኬዎ ይድረሰን

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s