በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የታጠቁ ሰዎች 900 እስረኞችን አስመለጡ

ታጣቂዎች በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ 900 እስረኞችን ከእስር ቤት ማስመለጣቸው ተነገረ፡፡ በወህኒ ቤቱ ላይ ጥቃት የከፈቱት ታጣቂዎቹ፣ የታጠቁት መሳሪያም ትላልቅ እንደነበር ከቢቢሲ መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ጥቃቱ የተፈጸመውም በሀገሪቱ ቤኒ በተባው ግዛት ውስጥ በሚገኘው እስር ቤት ላይ ሲሆን፣ በተካሔደው ጥቃትም በተለያዩ ወንጀሎች የተፈረደባቸው 900 እስረኞች አምልጠዋል፡፡

በእስር ቤቱ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት ተከትሎ በመንግስት ወታደሮች እና በታጣቂዎች መካከከል በተደረገው የተኩስ ልውውጥ አስራ አንድ ሰዎች የሞቱ ሲሆን፣ ከሟቾቹ መካከልም ስምንቱ የእስር ቤቱ ጠባቂዎች መሆናቸው ተነግሯል፡፡ የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ መንግስት እንዳስታወቀው ከሆነ፣ እስካሁን ድረስ ጥቃት ፈጽመው እስረኞችን ያስመለጡት ሰዎች ማንነት ባይታወቅም፣ ቤኒ በተባለው ግዛት የሚንቀሳቀሰው እና ማይ ማይ የተባለው ታጣቂ ቡድን ምናልባት ከጥቃቱ ጋር ንክኪ ሳይኖረው እንደማይቀር ተጠርጥሯል፡፡

በዴሞክራክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዋና ከተማ ኪንሻሳ ባለፈው ወር በእስር ቤት ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከአራት ሺህ በላይ እስረኞች ማምለጣቸውን የዜናው ምንጭ አስታውሷል፡፡ ይህ ወህኒ ቤት ከፍተኛ ጥበቃ ከሚደረግባቸው የሀገሪቱ ወህኒ ቤቶች አንዱ ቢሆንም፣ የታጠቁ ሰዎች ከአራት ሺህ በላይ እስረኞችን ማስመለጥ ችለዋል፡፡ 900 እስረኞች እንዲያመልጡ የተደረገበት ጥቃት በማን እንደተፈጸመ በመጣራት ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡

 

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s