የችካጎ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ፖለቲካዊ ውጥረት ከገዥው መንግስት ገጠማት

ዘጋቢ ዘላለም ገብሬ ከቺጋጎ

ላለፉት ኣንድ ኣመታት በፖለቲካ ውዝግብ ውስጥ በመሆን የቤተክርስቲያን ኣገልግሎቷን በትክክል መስጠት ያልቻለችው የደብረ ገነት ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስትያን ፣ ኣስተዳደራዊ መድሎ መጥቶብኛል በማለት ጥሪ ለማህበረሰብ ብታደርግም በጥሪው መሰረት ሊደርስላት የቻለ ኣንድም ኣካል ኣልነበረም:: ሆኖም ግን በኣሁን ሰኣት የከፋ ውድቀት ላይ ደርሳለች::

በቤተክህነቴ ውስጥ ምንም ዓይነት የፖለቲካ ሂደት ሊንቀሳቀስ ኣይገባም ማንኛውም ማህበረሰብ ፖለቲካውን በውጭ ማንጸባረቅ ይችላል ፤ ሆኖም ግን ይህ የእምነት ቤት ነው እናም የእምነት ስርአታችን ይከበር ብለው ድምጽ ቢያሰሙ ተቀባይነት ሊያገኝ ኣልቻለም።

በችካጎ ነዋሪ ማህበረሰብ የተመሰረተችው ይህችው ቤተክርስትያን በወያኔ ኣባላት አና ተላላኪ ፓትርያሪኮች ውጥረት ውስጥ በመግባትዋ ህዝብ ከጎኔ ሆኖ ይዳኘኝ ስትል ጥሪ ማቅረቡዋን የደረሰን መረጃ ያመለክታል:: የቤተክህነት አባላቶች እንደጠቆሙት ከሆነ በኦሃዮ ቤተክርስቲያናትን በማፍረስ የሚታወቁት ሊቀካህን በችካጎም ለማፍረስ ግንባር ቀደሙን ስፍራ ይዘዋል ይህንን ህዝባዊ የሆነ ንብረታችንን እና የአንድነት የምነት ጽናታችንን በጋራ እንታገላለን ሲሉ በአጽኖት ጥሪ ያቀረቡት ምእመናኖች እና የቤተክርስቲያኒቱ አባላቶች፣ ህዝብ በላቡ ኣንጠፍጥፎ የሰራትን ቤተመቅደስ በኣንድ አና ሁለት ግልሰብ መፍረስ የለባትም ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል ፣ በኒው ዮርክ የሚገኙት እና የወያኔ ደህንነት ናቸው ተብለው የሚጠሩት ብጹአ ኣቡነ ዘካርያስ የማስፈራርያ እና በቤተክርስቲያናቱ የሚያገለግሉ ካህናትን የመገደብ የመገዘት ሂደት እምነታዊ ስርአት ሳይሆን ስርአት አልበኝነት ነው ፤ ህግ በግል ስልጣናቸው ያወጡ ሲሆን ፣ባለፉት ወራት ለሽምግልና ብለው ከኒውዮርክ ቢመጡም በራሳቸው ስልጣን ፣ከህዝቡ ፈቃድ ውጭ የነበሩትን የቤተክርስቲያን ኣባት ከስልጣን በማውረድ በተተኪው ከኢትዮጵያ ሌላ መንፈሳዊ ኣባት ለማምጣት በመጣራቸው ብጥብጡ ሊነሳ የቻለ መሆኑን ጠቁመው ፣ከኢትዮጵያ ለሚመጡት መነኩሴ ኣባት የደመወዝ ክፍያቸውን የችካጎ ነዋሪዎች አንደሚሸፍኑ አክለው ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ማህበረሰቡ ለዚህም ጉዳይ የመነኩሴውን ክፍያም ሆነ ለሚደረጉት ማናቸውም ነገሮች ሃላፊነትን የማንወስድ ሲሆን ቤተክርስቲያኒቱ ሃላፊነትን ልትወስድ አይገባም ሲሉ ተናግረዋል በተጨማሪም ማህበረሰቡም ዕዳ የለበትም ሲሉ ገልጸዋል።

በኣሁን ሰኣት ከኦሃዮ ቤተክርስቲያንን ኣፈረሱ የተባሉት ሊቀ ካህን የቤተክርቲያኒቱን ቁልፍ በመቀየር በግላቸው ስልጣን ቁልፍ መያዛቸው እና ምዕመናንን ማባረራቸው ተገልጾኣል:: በዚህም መሰረት ቁጣውን የገለጽው የችካጎ የቅድስት ድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ኣባላት እና ኣገልጋይ ካህናት ወደ ክስ ኣቅጣጫ የሚያመራቸውን ኣጀንዳ መጀመር አንደሚፈልጉ አና የህግ ጥብቅና ኣገልግሎት ሊሰጣቸው የሚችል የህግ ባለሙያ ጥሪ እያደረጉ ይገኛሉ። በዚህም ጥሪ መሰረት የነገው እሁድ ቀን ሰኔ ፲፩ ፪፲፻፱ (June 18/2017) በሚደረገው የቅዳሴ መረሃ ግብር ላይ ማንኛውም ህዝበ ክርስቲያን ተነስቶ የላቡን እና የእምነቱን ዋጋ ማግኘት ለበት ሲሉ የጠቆሙ ሲሆን ቤተ ክርስቲያናችን በፖለቲከኞች አንጃ እና የጥቅመኞች ጎራ ተሰልፋ መቆም የለባትም ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል ።

በተለይም ቁልፉን በመቀየር እና ቤተክርስቲያንን በማፍረስ የሚታወቁት የተባሉትን ሊቀ ካህን (የዚህን ግለሰብ) ውሳኔ የተመለከቱ ማህበረሰቦች በሙሉ ቁጣቸው ከፍያለ ከመሆኑም በላይ የዘሃበሻ እና ማለዳ ታይምስ ዘጋቢ ከስፍራው እንደገለጸው ከሆነ ካህኑ ቁልፉን በመቀየሩ ብቻ ይህዝብ ንብረት የሆነውን ይህንን ትልቅ ድርጅት አንደ ግላቸው በራሳቸው ፈቃድ ሁከትን በመፍጠራቸው እና የፖለቲካ ኣንጃቸውን በማንጸባረቃቸው ፣ በመካፈልን በመፍጠር አና ዲያቆናትን በማባረር ኀር ሲተበትቡ አንደነበር ጥናት በማካሂያድ ቆይቶ የህግ ባለሙያ ኣናግሮ ፣የህግ ባለሙያዎች አንደገለጹለት ከሆነ ከአስር አመት አስከ አስራ አምስት አመታት ቅጣት ሊጠብቃቸው እንደሚችል እና የቤተ ክህነት አገልግሎት ፈቃዳቸው ሊነጠቅ አንደሚችል ጭምር አክሎ ገልጧል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ ቤተክርስቲያኒቱ በችካጎ ለሚገኙት ህዝበ ምእመናን አና በሌሎች ሰሜን የሚገኙ ህዝበ ክርስቲያንን ድረሱልኝ ሸምግሉኝ ፣እነዚህን ፖለቲከኞች ከስሬ አስወጡልኝ ስትል ጥሪዋን አቅርባለች ። ይህ የችካጎ ህዝብ ገንዘብ እና ንብረት አንጂ በፖለቲካ የተመሰረቱ ግለሰቦች መጠቀሚያ ኣይደለሁም ስትል ትገልጻለች ቤተክርስቲያኒቱ። ዘሃበሻ ከዚህ በፊት አንደዘገበው የዲያቆን በረከት ገብሬ መባረር ዋነኛ ኣጀንዳ ከመሆኑም በላይ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቤተክርስቲያኒቱን ኀርኅሮ የመጣው ፖለቲካዊ ኣጀንዳ ክፉኛ ኣወዳደቅ ላይ ደርሶኣል።

የዲያቆን በረከት መባረር ምክንያት በእሪቻ በአል ላይ በመንግስት ግፍአዊ አገዛዝ ለተጨፈጨፉ ዜጎቻችን የህሊና ጸሎት በማድረጉ አና ምእመናን ለሃገራችን ጸሎት ያስፈልጋታል፣ የሃይማኖት አባቶቻችን እጃችሁን ወደ እግዚአብሂአር ዘርጉ ብሎ በአደባባይ መናገሩ እንደ ሃጢአት ተቆጥሮ ነው ክስ የተጀመረበት ፣ከዚያን ጊዜ በሁዋላ ከአገልግሎት እንዲታገድ ተደርጉል ይህንንም ዘሃበሻ እና ማለዳ ታይምስ መዘገባቸው የቅርብ ጊዜ ትውስታችን ነው ይህም በመከሰቱ እና የዜና ሪፖርቱ በመታወጁ እነዚህኑ የስለላ ስራ የሚሰሩትን የቤተክርስቲያን አቀንጭራዎች እንደአስቆጣቸው፣ መዕመናን ገልጸዋል።

በዚህች ቤተክርስቲያን ውስጥ ለአንድ አመት ያላሰለሰ ጥረት ተደርጎ በሰላም ለመፍታት ጥረት ቢደረግም በጉልበታቸው ቁልፉን የቀየሩትን እኝህን የሃይማኖት አገልጋይ የተባሉትን እና የቤተክርስቲያን ጠላት ለመክሰስ ዝግጅታችንን አጠናቀናል ሲሉ፣ ከአሁን በኋላም ከኒው ዮርክ መጥቼ ስለቤተክርስቲያኗ ያገባኛል የሚሉትም ብጹእ ኣቡነ ዘካርያስ ወደ ቤተክርስቲያኗ ጥግ እንዳይደርሱ የፍትህ ደብዳቤ አያይዘን ለመላክ ዝግጅታችንን አጠናቀናል ሆኖም ግን አሁን ህዝበ ክርስቲያኑ ከጎናችን ይሆን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s