በአዲስ አበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ አንድ ሺህ 573 መኖሪያ ቤቶች እየፈረሱ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አንድ ሺህ 573 መኖሪያ ቤቶችን እያፈረሰ መሆኑ ታወቀ፡፡ በክፍለ ከተማው ከአፍሪካ ህብረት ጀርባ እየተካሔደ ባለው የማፍረስ ዘመቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህ ቀደም በክፍለ ከተማው ‹‹ፈለገ ዮርዳኖስ›› በተባለው በዚሁ ስፍራ፣ በርካታ ቤቶች ፈርሰው በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው ይታወሳል፡፡ አሁን እየተካሔደ ያለው የማፍረስ ዘመቻም የዛኛው ተከታይ ክፍል መሆኑን መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተጠቀሰው ክፍለ ከተማ እና ሰፈር 17 ሔክታር መሬት ከነዋሪዎች ለማጽዳት እየሰራ ሲሆን፣ ቦታውም ለቻይና መንግስት ጨምሮ ለሌሎች የውጭ ሀገር ባለሃብቶች እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ በተለይ አሁን ላይ በፍጥነት እየተካሔደ ያለውን አንድ ሺህ 573 ቤቶችን የማፍረስ ዘመቻ ተከትሎ፣ ቦታው የቻይና መንግስት ለሚገነባው ህንጻ መስሪያነት ይውላል፡፡ የቻይና መንግስት ‹‹ቻይና አፍሪካን ሚሽን›› ብሎ ለሰየመው አህጉር ዓቀፍ ፕሮጀክት ማከናወኛ የሚሆን ቢሮ በአዲስ አበባ ለመገንባት ያቀደ ሲሆን፣ ግዙፉን ህንጻ የሚገነባውም ነዋሪዎች እየተፈናቀሉ ባሉበት በዚሁ ቦታ ላይ ነው፡፡

አንድ ሺህ 573 መኖሪያ ቤቶች እየፈረሱበት ባለው የአፍሪካ ህብረት ጀርባ አካባቢ ከቻይና መንግስት በተጨማሪ አንድ የኳታር ባለሃብት ድርሻ እንዳለውም ተጠቁሟል፡፡ በአካባቢው ከነዋሪዎች እየጸዳ ካለው 17 ሔክታር መሬት ውስጥ የቻይና መንግስት አራት ሔክታር መሬት የተፈቀደለት ሲሆን፣ ስድስት ሔክታር የሚሆነው መሬት ደግሞ ለኳታር ንጉሣዊ ቤተሰቦች ተሰጥቷል፡፡ የኳታር ንጉሳዊ ቤተሰብ ንብረት የሆነው ኢዝዲን ሆልዲንግ ግሩፕ በዚህ ቦታ ላይ ሆቴልን ጨምሮ ሪል ስቴት እና የገበያ ማዕከል ለመገንባት ፈቃድ አግኝቷል፡፡ የተቀረው ሰባት ሔክታር መሬት በቀጣይ ለምን አገልግሎት እንደሚውል እስካሁን የተገለጸ ነገር የለም፡፡

ከነዋሪዎች እየጸዳ በሚገኘው በዚሁ 17 ሔክታር መሬት ላይ 1,573 ቤቶች የሚገኙ ሲሆን፣ እስካሁን ድረስም 1,271 ቤቶች ፈርሰው ማለቃቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የማፍረስ ዘመቻው በፍጥነት እየተከናወነ መሆኑ፣ ነዋሪዎችን ለእንግልት እና ላልተፈለገ ውጣ ውረድ እየዳረገ ይገኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በዚሁ አካባቢ በተካሔደው መሰል የማፍረስ ዘመቻ፣ በርካታ ነዋሪዎች ቅሬታ ሲያቀርቡ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ከቦታቸው ተነስተው ተተኪ መኖሪያ ቤት ተሰጣቸው የተባሉ ነዋሪዎች፣ በምትክነት ተሰጣቸው የተባለው ኮንዶሚንየም መብራት፣ ውሃ እና ሰመል መሰረታዎ ነገሮች ያልተሟሉበት መሆኑን ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ የቻይና መንግስት አፍሪካን በቁጥጥሩ ስር ለማዋል የነደፈውን ‹‹ቻይና አፍሪካን ሚሽን›› ፕሮጀክት፣ ዋና መቀመጫውን አዲስ አበባ በማድረግ ለማስፈጸም ተዘጋጅቷል፡፡

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s