ኢትዮጵያ ለዓለም ዓቀፍ አበዳሪ ሀገራት እና ተቋማት ሥጋት መሆኗ ተገለጸ

 

(BBN NEWS) ኢትዮጵያ ለዓለም ዓቀፍ አበዳሪ ተቋማት እና ሀገራት ሥጋት እየሆነች መምጣቷን አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ገለጹ፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር አብርሃም ተከስተ እንደገለጹት ከሆነ፣ ሀገሪቱ ያለባትን የውጭ ሀገራት ብድር መመለስ እያቃታት በመሆኑ፣ በአበዳሪ ተቋማት እና ሀገራት ዘንድ እንደ ስጋት እየታየች ትገኛለች፡፡ ይህም ሀገሪቱ በዓለም ዓቀፍ አበዳሪ ተቋማት እና ሀገራት ዘንድ ‹‹ታማኝ ተበዳሪ›› እንዳትሆን እንዳደረጋት ሚኒሰትሩ ገልጸዋል፡፡

‹‹የኤክስፖርት ገቢው አነስተኛ ስለሆነ፣ አገሪቱ የምትወስዳቸውን ብድሮች መልሶ ለመክፈል የማያስችላት በመሆኑ በአበዳሪ አገራትና በዓለም የገንዘብ ተቋማት ግምገማ አገሪቱ ያለባትን የሥጋት ደረጃ ከፍ እንዲል አድርጓል፡፡›› ያሉት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር አብርሃም ተከስተ፣ አክለውም ‹‹የኤክስፖርት ገቢው አፈፃፀም ተሻሽሎ አገሪቱ በአበዳሪ አገራት ያለባት የሥጋት መጠን እስከሚቀንስ ድረስ የኮሜርሻል ብድር መውሰድ ለተወሰነ ጊዜ መገደብ ይኖርበታል፡፡›› ሲሉ አሳስበዋል፡፡

መንግስት ከተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት እና ሀገራት በውጭ ምንዛሪ መልክ የወሰዳቸውን በቢሊዬን የሚቆጠሩ ብድሮች፣ በወቅቱ መክፈል አለመቻሉ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወደቀ እንደመጣ እንደሚያመላክት የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ በየዓመቱ ‹‹አስራ አንድ በመቶ አደገ›› እየተባለ ከበሮ የሚመታለት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ፣ ብድር ለመክፈል እንኳን የሚያበቃ ተክለ ሰውነት እንደሌለው የሚናገሩት ባለሙያዎቹ፣ በተለይ ከወጪ ንግድ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ከጊዜ ወደ ጊዜ ማሽቆልቆል፣ በኢኮኖሚው ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ በዚህኛው በጀት ዓመት ዘጠኝ ወራት ወደ ውጪ ከተላኩ ዕቃዎች የተገኘው የኤክስፖርት ገቢ፣ ለኢምፖርት የተከፈለውን የውጪ ምንዛሬ መሸፈን የቻለው 17 በመቶ ያህሉን ብቻ ነው፡፡

‹‹በኤክስፖርት ገቢው ላይ የሚታየው ማሽቆልቆል አሳሳቢ ነው፡፡›› ያሉት ዶ/ር አብርሃም፣ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ወራት ከኤክስፖርት የተገኘው 1.95 ቢሊዮን ዶላር ብቻ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ይህም ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ጊዜ ከተገኘው የ2.9 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር ‹‹ከፍተኛ ውድቀት›› ሊባል የሚችል ማሽቆልቆል አሳይቷል፡፡ ሚኒስትሩ፣ የመጪውን የ2010 ዓመት በጀት አስመልክቶ ለፓርላማ ባቀረቡት ማብራሪያ ላይ፣ ‹‹የተከሰተውን የወጪ ገቢ ንግድ በማሳደግ፣ በዓለም ዓቀፍ አበዳሪ ተቋማት ዘንድ ያለንን የስጋት መጠን መቀነስ አለብን፡፡›› በማለት በተደጋጋሚ ተናግረዋል፡፡

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s