በቋራ አላጥሽ በረሃ የወያኔ ወታደር ከባድ ጉዳት ደረሰባቸው ተባለ

የወያኔ ወታደር በዚህ ወደ 267 ሺ ሄክታር በሚሰፋ የጀግኖቹ መናህሪያ የ3 እና የ4 ቀን ሬሽን ይዞ በዘመቻ ቢገባ ብዙወች በውሃ ጥም እና መንገድ ጠፍቷቸው መውጫው መንገዱ ሲጨልምባቸው ሲዞርባቸው እራሳቸውን ሱዳን በረሃ ውስጥ ያገኙታል።

የቀየው ባላባት የአራዊቱ ጓድ ታጋይ አርበኛ ግን የዛፍን ፣የሳሩን አይነት የአራዊቱን ዝማሬ ሳይቀር ለይቶ ያውቃል። ለዚህም ነው የሚገባውን የጠላት ወያኔ ጦር ገና እርምጃ ሳይጀምር በአጭር የሚቀጨው።

እስከዛሬ ከሻውራ ቋራ እየተወረወረ ፣ ከሱዳን ዳንዲር ፣ ከጃዊ ከብተሌ እየከበበ ወደ አላጥሽ በረሃ ገብቶ የተመለሰ አንድም የወያኔ ጦር የለም። ለዚህ የአርበኛው እርሳስ አፎቱ ምስክር ነው ። ለዚህ አላጥሽ በረሃን ሰንጥቆ ሱዳን የሚገባው “የአልጣሽ ወንዝ”፣ ተራራው ገደሉ ምስክር ነው ። ለዚህ የጠዋት ሲሳይ ሁኗቸው የወያኔን ወታደር ቅርጥፍ አድርገው የበሉ የዱር አራዊቶች ምስክር ናቸው። 


ለዚህ ጃንሆይ ቀዳማዊ ኋይለስላሴን ከስደት መልስ የተቀበላቸው ሰንደቃችን በክብር የተሰቀለበት የኦሜድላ ምድር ትልልቅ ዛፋ ፣እረጃጂም ሳር ምስክር ነው ።
ለዚህ በአርበኝነት ለሚኖረው ገቢውን እንጂ ወጭውን ለማያየው በትዝብት ለኖረው የመይሳው የቋራ ህዝብ ምስክር ነው።


ከሰሞኑ በጎንደር እና በጎጃም እስከ ሱዳን ማዶ ወያኔ አለኝ የሚለውን የአጋዚ ጦር አሰልፎ ቢገባ እንዳሰበው አልሆነም ያልጠበቀው በወገራ እንቃሽ የጀመረው አስደንጋጭ የመልስ ምት በጆሮው ግርጌ አፉጨበት ፤ ከማይታገለው ቋጥኝ ጋር ተላትሞ ከፊሉ ሲደመሰስ ከፊሉ መፈግፈጉ አልቀረም።

የጀግናውን የአማራ ገበሬ ትጥቅ ለማስፈታት የማሰነው ወታደር እግሩ ሳይራመድ ከተሰቀለበት ሳይወርድ እንደቅጠል እየረገፈ ነው። ብዙወች ተደምስሰዋል ከፊሎችም መሳሪያቸውን ተገፈዋል። በቀጣይስ ? 

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s