ለሁሉ ኢትዮጵያዊያን የቀረበ ሕዝባዊ ጥሪ – የጎንደርን ታሪካዊ ሰልፍ አስቦ ስለመዋልና ለኢትዮጵያን የነጻነት ትግል ድጋፍ ስለመስጠት

gondarprotest200

የጎንደር ህዝብ ባለፈዉ ዓመት (ወርሃ ሃምሌ 5 ቀን 2008 ዓ/ም) ወያኔ ያጠመደዉን መትረየስ ተረማምዶ የ25 ዓመታታት የግፍ የዘረኛ ሥርዓት ለመገርሰስ በጎንደር ከተማ የአምባሻ ባንዲራ አሽቀንጥሮ ጥሎ ለዘመናት የነፃነቱ ምሳሌ የሆነችውን ሰንደቅ አላማዉን እያዉለበለ፤ “የኦሮ ደም ደማችን ነው፤ ቅማንት እና አማራ አንድ ነው፤ አንክፋፈልም” በማለት የፍርሃት ኬላን ሰብሮ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ብሔራዊ መልክቱን ማስተላለፉ ይታወቃል። በሚሊዮን የተቆጠረ ሰልፈኛ ጎዳናዎችን አጨናንቆ የጎንደር ሕዝብ በዚያች ቀን ያስተላለፈዉ የትግል ጥሪ ወያኔን በእጅጉ ያብረከረከ የኦሮሞና አማራን ወንድማማችነት ያስመሰከረ፤ የትግል ማዕል ሁኖ ዓለምን ያስደመመ፤ አስደናቂ እና የማይረሳ ታሪካዊ ቀን ነዉ። ይህ ቀን የትዉልድ ጀግናዎቻችን እነ ኮኔሬል ደመቀን የፈጠረ፤ እነ በቀለ ገርባን በጎንደር አደባባይ የትግል መሪ አድርጎ የተቀበለ ታሪካዊ ሰልፍ በመሆኑ በዓለም ዙሪያ የምንኖር የጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት አባላት ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ሀምሌ 16 ቀን 2017 ዓ. ም. በተለያየ መልኩ አሥበነዉ እንዉላለን። ይህንን ታሪካዊ በአል ስናስብ ዛሬም የጎንደር ህዝብ ለወያኔ እስከመጨረሻዉ በቃኝ አልገዛም! ብሎ በአንድነት ተማምሎ የገባዉን የጸና የትግል ቃል ኪዳን ከግቡ ለማድረስ አጠናክሮ ለቀጠለዉ እልህ አስጨራሽ ትግል አጋር መሆናችንንም ለማስመስከር ነዉ።

ጎንደር ላይ የአመጽ እሳት ተለኩሶ፤ ባህርዳር ተቀጣጥሎ መላ ጎጃምን ያጥለቀለቀዉ ታሪካዊው ሰላማዊ ሰልፍ የነጻነት የእሳት ሰደድ ሁኖ የወያኔን የዘረኝነት ጎጆ በማቃጠሉና ሕዝባዊ ድጋፍ ጨርሶ እንደሌለው የተረዳው አዉሬ ሥራዓት የቻለውን ያክል በማርሻል ህግ ጨፍልቆ ለመግዛት ዛሬም እየተፍጨረጨረ ይገኛል። የሐምሌ አምስትን ታሪካዊ በዓል ኢትዮጵያዉያን ሁሉ በዉስጥም ሆነ በዉጭም አሥበን ስንዉል የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር በአሁኑ ሰዓት ያለዉን የጦር ኃይል ሁሉ አከማችቶ የዘር ማጥፋት ዘመቻዉን በአዲስ የኮማድ ፖስት ሥር አጠናክሮ በሁሉም የጎንደር አዉራጃወች እያንቀሳቀሰ ይገኛል።

ይህንን ፋሽሽታዊ ጭፍጨፋ ለመቃወምና መተኪያ የማይገኝላት ህይወታቸውን አሳልፈው ለመስጠት መስዋት እየከፈሉ ያሉ ጀግኖቻችንን በዚህ ታሪካዊ ቀን አስበን ለመዋል እሁድ አምሌ 16, 2017 ሁሉም ኢትዮያዊ በሚኖርበት ከተማ፤ በአዳራሽም ይሁን በእምነት ቦታወች በመሰባሰብ በጸሎት፤ ሻማ በማራት፤ ዉይይት በማድረግ፤ ግጥምና ጽሁፎችን በመገናኛ ብዙኃን በማሰራጨት ለትግሉ የድጋፍ ድምጻችን በመስጠት፤ ትብብራችን እንድናሳይ የጎንደር ህብረት ለኢትዮጵያ አንድነት በአክብሮት ጥሪዉን ያስተላልፋል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ
ጎንደር ሕብረት ለኢትዮጵያ አንድነት

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s