የሁለት ኦስካሮች ወግ በጀርመን የሂትለር Nazi ወቅት

– ታደሰ ብሩ ከርሲሞ

ኦስካር ግሮኒንግ (Oskar Groening) ከሕይወት ያለ የዘጠና ስድስት ዓመት ሽማግሌ ጀርመናዊ ነው። በጀርመን የሂትለር አገዛዝ ወቅት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ንፁሃን የተፈጁበት አሽዊትስ ካምፕ ውስጥ የሂሳብና ጽህፈት ሠራተኛ ነበር። ኦስካር ግሮኒንግ አንድም ሰው አልገደለም፤ አንድም ሰው አልገረፈም። እሱ ሂሳብ ነው የሠራው። ሂሳብ ሠራተኝነቱ በፋሽስት ሥርዓት ተባባሪነት ያስከስሰኝ ይሆናል ብሎ አልገመተም ነበር ይሆናል። ሆኖም ከብዙ ዓመታት በኋላ አሽዊትስ ሲሠራ እንደነበር የደረሱበት ሰዎች ከሰሱት። እሱም ሂሳብ ከመሥራት ያለፈ በማንም ሰው ላይ እጁን እንዳላነሳ ተከራከረ። መከራከሩ ዜናው በስፋት እንዲወራና በ 90+ ዓመት እድሜው እንዲዋወድ አደረገው እንጂ አልጠቀመውም። በደል ሲፈፀም አይቶ “ምናገባኝ” ብሎ አልፏልና July 15 2015 የ4 ዓመታት እስር ተፈርዶበት በሁለት እግሮቹ መቆም በማይችልበት በመጦሪያው ዘመን ቤተሰቦቹና ጓደኞቹ ፊት ተዋርዶ እስር ቤት ወርደ።unnamed

በአንፃሩ ኦስካር ሽንድለር (Oskar Schindler) በጀርመን ናዚ ወቅት ሂትለር ይመራው የነበረው የናዚ ፓርቲ አባልና ሰላይ ነበር። ሆኖም ግን የሥርዓቱን ኢሰብዓዊነት ሲረዳ እዚያው የናዚ ፓርቲ ውስጥ ሆኖ አለቆቹ ያዘዙትን ሳይሆን ቅን ህሊናው ያዘዘውን በምስጢር መሥራት ጀመረ፤ በዚህም የ 1200 ሰዎችን ሕይወት ታደገ። የናዚ ፓርቲ ምስጢሮችን ለነፃነት ኃይሎች እየሰጠ የውስጥ አርበኛ ሆነ። ከጦርነቱ በኋላ ኦስካር ሽንድለር ተከብሮ የኖረ በርካታ የክብር ስሞችና ሽልማቶች የተሰጠው በመልካም አርዓያነቱ የሚጠቀስ ሰው ሆነ።
ሁለቱም ሰዎች – ኦስካር ግሮኒንግና ኦስካር ሽንድለር – የጀርመን ዜጎች ናቸው፤ የሂትለር መንግሥትም ወራሪ የውጭ ኃይል ሳይሆን የጀርመን መንግሥት ነበር፤ ሆኖም ልክ እንደ ህወሓት አገዛዝ አፋኝና ፀረ-ሕዝብ አገዛዝ ነበር። አንዱ የአገዛዙ ተባባሪ መስሎ ውስጥ ውስጡን ሥርዓቱን በማዳከሙ ተሸለመ፤ ሌላው በምን አገባኝ በመተባበሩ ተዋረደ፣ ተቀጣ።
በህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴድ፣ ደኢህዴግ እንዲሁም አብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊና ኢሶዴፓ ያላችሁ ወገኞች ኦስካር ግሮኒንግን ወይንስ ኦስካር ሽንድለርን መምሰል ትፈልጋላችሁ? በህወሓት ፋሽስታዊ አገዛዝ የጦርና የፓሊስ ሠራዊት ውስጥ ያላችሁ ወገኖቻችን ነገ የምትዋረዱበትን ሥራ መሥራት ነው የሚበጃችሁ ወይስ ዛሬ ከህሊናችሁ ጋር ታርቃችሁ እየኖራችሁ ነገ ደግሞ ልጆቻችሁና የልጅ ልጆቻችሁ የሚኮሩበትን ተግባር መፈፀም ትፈልጋላችሁ? በአገዛዙ የስለላ ድርጅቶች ውስጥ ያላችሁ ወገኖች ስማችሁን በመልካም ማስጠራት አትሹምን?
የህወሓት፣ ብአዴን፣ ኦህዴግ፣ ደህዴግ እንዲሁም አብዴፓ፣ ቤጉህዴፓ፣ ጋህአዴን፣ ሀብሊና ኢሶዴፓ አባላት የሆናችሁ ወገኖቻችን ኦስካር ግሮኒንግን ወይንስ ኦስካር ሽንድለርን መምሰል ትፈልጋላችሁ? በአገዛዙ የፓለቲካ፣ የጦርና የፓሊስ ተቋማት፤ በስለላም ይሁን በሌላ የሲቪል ሙያ የተሰማራችሁ ወገኖቻችን የታዘዛችሁትን ሳይሆን ቅን ህሊናችሁ የሚጠይቃችሁን በመሥራት የህወሓት አገዛዝን ማዳከም ትችላላችሁ። ይህንን ስታደርጉ በጠላት መዋቅር ውስጥ ሆናችሁም የመልካም ዜግነት አርዓያዎች ትሆናላችሁ።
በአገዛዙ ውስጥ ሆናችሁ እያለም የምትሠሩት ለሀገርና ለትውልድ የሚጠቅም በርካታ ሥራ አለ። የአገዛዙን ምስጢራዊ ሰነዶች ለአርበኞች ግንቦት 7 እንዲደርስ አድርጉ፤ አሊያም በማኅበራዊ ሚዲያዎች (ለምሳሌ ፌስ ቡክና ቱተር) አሰራጩ። የህወሓት ፀረ-አገር እና ፀረ-ሕዝብ ፕሮጀክቶችን አሰናክሉ። በነፃነት ታጋዮች ላይ የሚደረጉ ዱለታዎችን አክሽፉ። ኢሕአዴግ ውስጥ ሆናችሁ ኢሕአዴግን አዳክሙ። የኢህአዴግ አባላት ሆይ! ድርጅታችሁ ለኢትዮጵያ ጥፋት የቆመ ነውና እውስጡ ሁናችሁ አዳክሙት፤ ግደሉት።
መልካም ዜጋ “ያባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ”፤ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶም አይብቀል”፤ “እያለህ ካልሆነ ከሌለህ የለህም” እና በርካታ መሰል ምሳሌዎችን አይከተልም። መልካም ዜጋ “እኔ ተቀጣሪ ባለሙያ ነኝ” በማለት የቀጣሪውን ባህርይ እግምት ውስጥ ሳያስገባ ኢፍትሀዊ ሥርዓትን በታማኝነት አያገለግልም።
Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s