ያለ ፍትሕ 550 ቀናት የታሰሩት ወጣቶች

ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ፍሬው ተክሌ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቴዎድሮስ አስፋው፡፡ አራቱም ወጣቶች በቂሊንጦ እስር ቤት ይገኛሉ፡፡ ወጣቶቹ እስር የመጀመሪያቸው አይደለም፡፡ በአንድ ወቅት ታስረው ለፍርድ የቀረቡት እነ ዳንኤል ተስፋዬ ‹‹ማቅለያ አቅርቡ›› ተባሉ፡፡ አቀረቡ፡፡ ግን አንድ ሰው ጥፋተኛ ነኝና ፍርዱ ይቅለልልኝ ብሎ በተለምዶ የሚያቀርበውን አይነት ማቅለያ አላቀረቡም፡፡ እነ ዳንኤል ያቀረቡት ማቅለያ፡-

‹‹…..በወጣትነት ዕድሜዬ ይህን አምባገነን መንግስት እየታገልኩ እገኛለሁ፡፡ ….በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ይህን አምባገነን መንግስት በመታገል ለሀገሬና ለህዝቤ የማደርገውን አስተዋፅኦ ከግምት ውስጥ እንዲያስገባልኝ እፈልጋለሁ›› የሚል ነበር፡፡ ወጣቶቹ ይህን ማቅለያ ሲያቀርቡ ፍርድ ቤቱ እውነትም እነሱ ባሉት መንገድ ይረዳዋል ብለው አይደለም፡፡ አቋቸውን አሳውቀው ፍርድ ቤቱ የፈለገውን እንዲያደርግ ነው ፍርድ ቤቱን መቀስቀሻ መድረክ ያደረጉት፡፡

በአሁነኛው እስርም ኢ ፍትሃዊነትን ፊት ለፊት እየተጋፈጡ ይገኛሉ፡፡ ቂሊንጦ እስር ቤት ጥቁር ለብሰው ፍርድ ቤት የሚሄዱትን በካቴና አስሮ ያሳድር ነበር፡ አንድ ቀን ጥቁር ለብሰዋል በሚል በርካታ ወጣቶች በካቴና ታሰሩ፣ አዳራቸውም እንደዛው ሊሆን ነው፡፡ እነ ቴዎድሮስ አልታሰሩም፡፡ ግን የታሰሩት ወጣቶች ካልተፈቱ ወደ ቤት ገብተን አናድርም ብለው አሻፈረኝ አሉ፡፡ ፖሊሶቹ የታሰሩትን ወጣቶች ሊፈቱ ግድ አላቸው፡፡ በነጋታው ግን እነ ቴዎድሮስ፣ እነ ኤርሚያስ መዳረሻቸው ጨለማ ቤት ሆነ፡፡ ይህን ቀድመው ያውቁታል፡፡

ማዕከላዊ እስር ቤት አንድ ላይ የታሰሩ ወጣቶቹ መካከል አንዱን አንዱ ላይ ለማስመሰከር የማያደርገው ጥረት የለም፡፡ ፍሬው ተክሌን በቀሪ ወንድሞቹ ላይ መስክር ብለው ቁም ስቅሉን አሳዩት፡፡ ደብድበውትና ዝተውበት ‹‹አሁንስ ምን ይሻልሃል?›› አሉት፡፡ የእሱ መልስ ‹‹ከወንድሞቼ ጋር ክሰሱኝ ነበር›› ክስን የማይፈሩ ወጣቶች፡፡
አራቱ ወጣቶች የቀረበባቸው የዘመኑ የሀሰት ክስ ነው፡፡ ‹‹ሽብር››! ወጣቱን እግሩ ስር ማድረግ ለሚፈልግ አገዛዝ እንዲህ አይነት አሻፈረኝ ባይ ወጣቶች ለእሱ ‹‹አሸባሪዎች›› ናቸው፡፡ ወጣቶችን በማስጎብደድ ለመግዛት የነበረው አላማ ያከሽፉበታልና ሌላውም እንደነሱ ይሆንብኛል ብሎ ይሰጋል፣ ይፈራል፣ ይሸበራልም፡፡ ትውልዱን አንገቱን ደፍቶ እንዲሄድ ፖሊሲ ነድፎ ለሚሰራ ራዕይ አልባ ገዥ እነዚህ እስር የማይፈሩ ደፋሮች ባዶ እጃቸውን ሽብር ይነዙበታል፡፡

አራቱ ወጣቶች ታህሳስ 15/2008 ዓ.ም ነው ታፍሰው እስር ቤት የገቡት፡፡ ባለፉት 18 ወራት ጨለማ ቤት ገብተዋል፡፡ ባዶ እግራቸውን እንዲሄዱ ተደርገዋል፡፡ ባዶ ወለል ላይ ተኝተዋል፡፡ እጃቸውን በካቴና ታስረው ለቀናት ቆይተዋል፡፡ በአጠቃላይ የዚህን ሀገር የእስር ቤት ሰቆቃ አይተዋል፡፡ ለ550 ቀናት፡፡ እነሆ ወጣቶቹ ከታሰሩ ዛሬ 550 ቀናት ሆናቸው፡፡ ያለ ፍትህ!

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s