ብአዴን እንደ ድርጅት አማራን እንደማይወክል የታወቀው ዛሬ ነውን? (አያሌው መንበር)

ይህ የታወቀው ድሮ፤ ተፈትኖ ሙሉ በሙሉ የወደቀውም የወልቃይትን ጉዳይ አይመለከተኝም ያለ እለት ይመስለኛል። ሰሞኑን ፌስቡክ ተጠቃሚ ሁሉ ታድያ ከብአዴን ምን ጠብቆ ነው ብአዴን ይውደም የሚለው? ከስብሰውባ መሪዎች እነ ካሳ ተ/ብርሃን ይልቅ ከበላይ ጠባቂዎችእነ በረከት ይልቅ ገዱ ላይ ዘመቻስ ምን ይሆን ምክንያቱ?

ብአዴንን ለትግል መጠቀም (ልክ ኦሮሞዎች ኦህዳድን እንደተጠቀሙበት) እና ብአዴንን እንደ ድርጅት መውደድ ፍፁም የተለያዩ ይመስለኛል።አንዳንዱ ሰው ምን እንደሚፅፍና ለምን እንደሚፅፍም የሚያውቀው አይመስለንም።ብአዴን የአማራ ህዝብ ወኪል ከሆነ እኛ መታገል ለምን አስፈለገን? የሚለውን ቀላል ጥያቄ መመለስ አቅቶት “እንዴት ብአዴን መቀሌ ይሄዳል?፣ እንዴት የብአዴን ም/ሊ/ር እና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር መቀሌ ይሄዳሉ? ብሎ ሲፅፍ እመለከታለው።
ለምን ሆነ ውጤቱስ ምን ሊሆን ይችላል? የሚለውን ግን በደንብ ያጤነው አልመሰለኝም።አንዳንዱ ጀማሪ “ፖለቲከኛ” ደግሞ ፅሁፉን የሚፅፈው ለግለሰቦች ሁሉ ይመስላል።gonder-before-and-after-1991

አንዳንዱ ደግሞ የውስጡን ፍላጎት በራሱ ስም እንዳይፅፍ ገፅታውን ለመገንባት ስለፈለገ በሚቀርባቸው ሰዎቻ በመጠቀም እርሱ ነፃ እየመሰለ ዘመቻውን ያጧጡፈዋል። እነርሱም ፖለቲካዊ ስልትን ሳይሄን የስድብ መርህን ተከትለው ያው አቅጣጫ በማሳት ሌላ አጀንዳ ይከፍታሉ።ቁረጠው ፍለጠው በቃ ምኑ ቅጡ።

እንደዚህ አይነቱ ሸርና ብጣብልጥነት አካሄድ ግን እንኳን ለአማራው ለግለሰቦችም አይጠቅም።ምክያቱምን የአማራው ትግል እውነት ላይ የቆመ ማንም ቢገፋው የማይወድቅ ነውና።ለገዜው ግን ተስፋ አስቆራጭ ይመስላል።ሞቅ ሲል ብልህ አማራና ፖለቲከኛ ቀዝቀዝ ሲል ሸርን መጎንጎንና የቂላቂል አካሄድ መሄድ ፍፃሜው ራስን ጠልፎ መጣል ነው።

የአንዳንዱ እንደዚህ አይነት ሰው የፖለቲካ ብስለት ማጣቱ ብቻ ሳይሆን የትግሉን ዓላማና መዳረሻ በደንብ አለማወቁም ጭምር ከሚፅፈው ይታወቅበታል።ራስን ለመከላከል ግሪሳ ማዘጋጀት ደግሞ ሌላኛው ነው።እንደ ቁራ መጮህ ብቻ መፍትሄ አይደለም።በአንድ ወቅት ዶ/ር አክሎግ “የአማራው ትግል ብልሃት ያንሰዋል” በማለት የተናገሩት ነገርን መዘንጋት ያለብን አይመስለኝም።

የሆነው ሆኖ ብአዴን ቀድሞውን አማራውን ቢወክል እኮ እኔ ነኝ አማራን ልወክለው የምችል የሚል ብዙ ከብአዴን ተቃራኒ የአማራ ድርጅት ባልተመሰረተ ነበር።ህዝቡም በእኛ ተስፋ ከማድረግ ይልቅ ብአዴንን የእኔ ብሎ በያዘው ነበር።የእነ ካሳ ተ/ብርሃን፣ የእነ አዲሱ ለገሰ፣በረከት ወዘተ ብአዴን እኮ የወልቃይት ቁስል እንደማያመው ከወራት በፊት በመፅሄቶች መግለጫ ሲያወጣ፣የአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ማሸነፍ ሳይችል ሲቀር ራሱን በራሱ ነው የገደለ።በእርግጥ ይህ ወቅት ብአዴን እንደ ድርጅት በእነዚህ ጉዳዮች “አያገባኝም” ማለቱ ከህዝብ እስከ ወዲያኛው እንዲለያይ አደረገው እንጅ ህዝብን እንደማይወክልማ የታወቀው ቀደም ብሎ ነው።

ይህ ማለት ግን ብአዴን ውስጥ ለህዝብ የሚያስብ የአማራ ህዝብ ግድያና ስቃይ፡ የአማራ ህዝብ ጥያቄ የወልቃይትም ይሁን የአ.አ ጉዳይ የሚያመው የለም ማለት አይደለም።ሶስት ሚሊዮን አማራ ሁሉ ደደብ፣መሃይም፣ባንዳ፡ጨፍፊፉ…ነው ማለት ግን ፍፁም ስህተት ነው።እኔና ብዙዎቻችችን የምንለያየው በዚህ መሰረታዊ ነጥብ ነው።

ስለዚህ ብአዴንን የአማራ ህዝብ ምርጥ ወኪል ነው የሚሉትን ርሷቸው።እነዚህ ልክ በህወሃት መርፌ የተወጉ ማለት ናቸው።በተቃራኒው ደግሞ ብአዴንን ለትግል ስልት እንጠቀብበት እዛ ውስጥም ብዙ እምቅ የሰው እና የገንዘብ ሀብት አለ የሚለውን በደንብ ልንገነዘብ ይገባል።ይህ የእኔ የማይናወጥ ፖለቲካዊ አቋሜ ነው።ማለትም ብአዴን የአማራ ህዝብ ወኪል ካልሆነ ቢያንስ የህወሃትን ያህል ባይሆን እንኳን የአማራ ህዝብ እንዲበደል እያደረገ ነው” የሚለው ላይም እንግባባለን ማለት ነው።

የብአዴን ሰዎች ለአማራ ህዝብ እንዲሰሩ የምናደርጋቸው ልክ እንደ እስከአሁኑ ስራቸውን እየሰሩ (ፖለቲካዊ ሀላፊነታችወንም ጭምር) እንጅ ስራቸውን አቁመው መሆንም የለበትም።

እንግዲህ ብአዴን የአማራን ህዝብ አይወክልም፤ብአዴን ውስጥ ያሉ ሰዎች ግን ሁሉም ባይሆኑም አማራው እንዲበደል አይፈልጉም (ከላይ ያሉትን አብዛኛዎችን ሳይጨምር) ካልኩ ዘንድ ታድያ እንዴት እንጠቀምባቸው? እንዴትስ እንለያቸዋለን? የሚል በውስጥ ለውስጥ ሊሰራ የሚችልን ነገር ቢኖር መልካም ነው።

ክፍል ሁለት ሊቀጥል ይችላል።

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s