በደቡብ ጎንደር ንፋስ መውጫ ከተማ የክልሉ ልዩ ሃይል አድማ በታኝ እና የአጋዚ ወታደሮች ተጣሉ

ከሰሞኑ ንብረትነታቸው የመሰቦ ስሚንቶ ፉብሪካ የሆነ ሁለት ተሳቢ ሙሉ ሲሚንቶ የጫኑ በወልድያ አድርገው በንፋስ መውጫ ከተማ አልፈው ወደ ደብረታቦር ሲያቀኑ ከከተማ መውጫው ካለው ማደያ አካባቢ ከዛፍ ላይ በተተኮሰ ጥይት የለበሱት ሸራ በመጠኑ ተቃጥሏል።

(በሰዓቱ ዝናብ ነበር) ከዚህ ጋር ተያይዞ የማደያው ጠባቂ ነው በሚል ቢመረመር እኔ አይደለሁ በማለቱ በቦታው የደረሱት የክልሉ ልዩ ሃይል አድማ በታኝ እና መከላከያ ወታደሮች በከፍተኛ ሁኔታ መዘላለፉቸው ተሰምቷል።

ልዩ ሃይሎች ወታደሮችን እናተ ሀገር ለመጠበቅ አልመጣችሁም ህዝብ ላይ ለመተኮስ እንጂ ገና ከመምጣታችሁ በየመጠጥ ቤቱ እና ጭፈራ ቤቱ ከነትጥቃችሁ ነው የገባችሁ በማለታቸው ከፍተኛ የሆነ ውዝግብ ተነስቶ መሳሪያ እስከመማዘዝ በመድረሳቸው በአለቆቻቸው አማካኝነት እንዲለያዩ ተደርገዋል። ይህ ወሬ በየቦታው ባሉ አባሎቻቸው በመድረሱ እርስ በርስ ጥርስ እየተነካከሰ ይገኛል።

በደብረታቦር ከተማ ከፍተኛ ውጥረት ያለ ሲሆን በከተማው ልዩ ሃይል አድማ በታኝ ብቻ እንዲቀሳቀስ ተደርጓል። በደብረታቦር መውጫና መግቢው ከፍተኛ ቁጥጥር እየተደረገ ሲሆን በጉና ተራራ ስር ከጉና ውሃ ፍብሪካ ፊት ለፊት የአጋዚ ወታደሮች ሰፍረዋል።

በአካባቢው ውጥረቱ ከሰሞኑ ጨምሯል።


የወያኔን ሰራዊት እሳትና ጭድ ያድርጋቸው ፀሎታችን ብቻ ሳይሆን ስራችንም ነው!

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s