የተሰረቅነው አገር ነው ።

የተሰረቅነው አገር ነው ።የተሰረቅነው አገር ነው ።

የተሰረቅነው አገር ነው ።
ላለፉት 26 ዓመታት የወያኔን ስርዓት ምን ዓይነት ስርዓት እንደሆነ ለማወቅ ተቸግረን ቆይተናል በተለይ በተለይ እስከቅርብ ጊዜ ድረስ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊው ዘንድ ወያኔን ይጠራበት የነበረው ስሙ ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ በማደናገሪያነት ተጠቅሞበታል ። የወያኔ ስርዓት ኢትዮጵያን ለመውረርና ለመግዛት የተጠቀመበት ኢህአዴግ የሚባለው የውሸት የወያኔ የመደበቂያ ጫካው ከቅርብ ዓመታት ጀምሮ መመንጠር ጀምሮ አሁን አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ኢህአዴግ የሚባል ድርጅት ሳይሆን ወያኔ የሚባል የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር የዘራፊና የወንበዴ ድርጅት እንደሆነ የማያውቅ ኢትዮጵያዊ አለ ብሎ ለማመን ይከብዳል ።
ይህ የዘረኛ አፓርታይድ ስርዓት ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያለማቋረጥ አገሪቷን ሙሉ በሙሉ በመዝረፍ ተግባር ላይ ተሰማርቷል ። የወያኔ ስርዓት በአገሪቷ ላይ ያልተሰማራበት የዘረፋ ተግባር የለም ከትንሹ የቀበሌ ሙስና የጀመረ እስከ የአገርን ድንበር ቆርሶ ለባእድ አገራት እስከመሸጥ ድረስ የደረሰ ወንጀለኛ ብቻ ሳይሆን አገር ከሃዲ የሆነ ድርጅት ነው ።
የወያኔ ስርዓት ኢትዮጵያ ውስጥ መቀጠል ማለት ኢትዮጵያ የምትባል አገር እንዳትኖር ማድረግ ማለት ነው ። ወያኔዎች ይህችን አገር ያላትን ሃብት ብቻ ሳይሆን ሁለመናዋን አርደው ለውጭ ባዕዳን አገሮች በመሸጥ ላይ ናቸው ። ይህ ደግሞ የመጣው ከመሬት ተነስቶ ሳይሆን በእቅድ ተነድፎና ተዘጋጅቶ ውስጥ ውስጡን ለብዙ ጊዜያት የተሰራበት ታላቅ የወያኔ የአገር ክህደት ወንጀል ነው ።
ታዲያ ዛሬ ዛሬ ይህ የወያኔ የአገር ማጥፋት ወንጀል በመላው ኢትዮጵያዊ በመታወቁና ህዝቡ በቃኝ ብሎ በመነሳቱ ወያኔ እንደከዚህ ቀደሙ የኢትዮጵያን ህዝብ አታሎ ለማለፍ አንዳንድ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ በዚህም መሰረት ባለፉት ሰሞናት በጥቂት ሰዎች ላይ የእስራት ዘመቻ በመውሰድ የአገሪቱን ሃብት የዘረፉ በማለት ለማወናበድ ቢሞክርም ሰሚ በማጣቱ ምክንያት ወደ ሌላ አቅጣጫ በመዞር አንዳንድ የወያኔ አመራሮችን በሙስና ስም ለማሰርና ድርጅቱ ሌብነትን ለመዋጋት ቁርጠኝነትን ይዞ ተነስቷል ለማለት በእንቅስቃሴ ላይ እንዳለ አንዳንድ ፍንጮች ከወዲሁ እየታዩ ነው ። 
ወያኔ ልክ እንደከዚህ ቀደሙ የማጭበርበሪያ መንገዶች እየሄደ የኢትዮጵያን ህዝብ ዘላለም ዓለሙን እያታለለ ለመኖር ማሰቡ ቢያናድድም ነገር ግን አሁንም ቢሆን የወያኔ ተስፋው ጥቂት የሆኑትን የወያኔ ሰዎችን አስረው ስልጣናቸውን ለማቆየት በመሞከር ላይ ይገኛሉ ። 
እኛ ኢትዮጵያውያኖች የተዘረፍነው ገንዘብ እና ንብረት ሳይሆን የተዘረፍነውና የተነጠቅነው አገራችንን ነው ይህንንም ለማስመለስ የምንችለው ይህንን የአገር ከሃዲ የሆነውን የወያኔ አፓርታይድ ስርዓት ከኢትዮጵያ ምድረ ገፅ ላይ ስናጠፋ ብቻ ነው ። ይህንንም ለማድረግ በአሁኑ ሰዓት መላው ኢትዮጵያዊው በየአቅጣጫው እየተነሳ ይገኛል እናም እንደከዚህ ቀደሙ ይህ ትግል አቦይ ፀሃዬን አልያም ደግሞ ስብሃት ነጋን ወይም ደግሞ የሙስና ቁንጮ የሆነችውን አዜብ መስፍንን በማሰር ሳይሆን ሊቆም የሚችለው ሙሉ በሙሉ ወያኔ የሚባለውን ስርዓት ከኢትዮጵያ ምድረገፅ ላይ በማጥፋት ብቻ መሆኑን የሁሉም ኢትዮጵያዊ እምነት ነው ። ስለሆነም ትግሉ እስከ ነፃነት ድረስ መስወአትነት እየከፈለ የሚሄድ ስርነቀል ትግል ነው እንጂ እንደከዚህ ቀደሙ እየተጭበረበረና እየተወናበደ የሚቆም ትግል አይደለም ።
ወያኔ ኢትዮጵያን የሰረቀ ሌባ ድርጅት ነው ። ኢትዮጵያ ነፃ የምትወጣው ወያኔ ከኢትዮጵያ ምድረገፅ ሲጠፋ ብቻ ነው ።
ዘነበ ዘ ቂርቆስ

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s