የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በድጋሚ ሊራዘም ነው

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በድጋሚ ሊራዘም ነው
BBN news August 1, 2017

በመስከረም ወር መጨረሻ ይፋ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሁለተኛ ጊዜ ሊራዘም መሆኑ ታወቀ፡፡ አዋጁ ለስድስት ወር ከቆየ በኋላ ባለፈው መጋቢት ወር ላይ ለአራት ወራት መራዘሙ የሚታወስ ሲሆን፣ ለተጨማሪ አራት ወራት የተሰጠው ጊዜ በመገባደዱ በድጋሚ ሊራዘም እንደሚችል ታውቋል፡፡ በህወሓት የሚመራው መንግስት፣ አዋጁን በዚህ ሰዓት የማንሳት ፍላጎት እንደሌለው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ይፋ ተደርጎ ግድያ መፈጸም ከተጀመረ በኋላ፣ የተለያዩ ዓለም ዓቀፍ ተቋማት በህወሓት መንግስት ላይ ውግዘት ሲያስከትሉ እንደነበር ይታወሳል፡፡

አዋጁን ለማራዘም እረፍት ላይ የነበሩት የገዥው ፓርቲ ፓርላማ አባላት አስቸኳይ ስብሰባ የተጠሩ ሲሆን፣ እንደተለመደውም በጭብጨባ እና በሆታ በህወሓት ትዕዛዝ መሰረት አዋጁን ያራዝሙታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ወቅቱ ከግብር ጫና ጋር በተያያዘ በሀገሪቱ ከፍተኛ ተቃውሞ የተነሳበት በመሆኑ፣ በዚህ የጭንቅ ሰዓት ህወሓት አዋጁን ሊያነሳ እንደማይችል የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራ፡፡ በተለያዩ አካባቢዎች ባለው ህዝባዊ ተቃውሞ ህወሓት ዳግም አጣብቂን ውስጥ የገባበት ጊዜ መሆኑን የገለጹት ተንታኞች፣ እንኳን በእንዲህ ያለው የጭንቅ ጊዜ ቀርቶ፣ በደህናውም ጊዜ ቢሆን፣ ሕወሓት ገዳይ ወታደሮቹን ማሰማራት መለያው እንደሆነ ተንታኞቹ አክለው ገልጸዋል፡፡

የዛሬ ዓመት በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ፣ ህወሓትን የሚሸሸግበት አሳጥቶት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ በወቅቱ የነበረው የህዝብ ማዕበል ከፍተኛ ድንጋጤ ላይ የጣለው ህወሓት፣ ነገሮች ሁሉ ከአቅሙ በላይ በሆኑበት ሰዓት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጁ ይታወሳል፡፡ አዋጁ ከታወጀ በኋላ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ንጽኃን ዜጎች በአጋዚ እና በሌሎች ወታደሮች ጥይት እየተመቱ መንገድ ላይ ቀርተዋል፡፡ ከ50 ሺ በላይ የሚሆኑ ዜጎችም ተቃውሞ በማሰማታቸው ወደ እስር ቤት ተግዘዋል፡፡ ስደት የወጡ ዜጎችም ቁጥራቸው በርካታ ነው፡፡ ይሔ ሁሉ ግፍ የተፈጸመበት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በድጋሚ ለራዘም መሆኑ ተሰምቷል፡፡ አዋጁ ምናልባት ለይምሰል ሲባል የተወሰኑ ‹‹ማሻሻያዎች›› ሊደረጉለት ይችል ይሆናል ብለው የሚያምኑት የፖለቲካ ተንታኞች፣ መራዘሙ ግን አይቀሬ መሆኑን ያስረግጣሉ፡፡

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s