ፒያሳ አራዳ ህንፃ ፊት ለፉት የተሰራብኝ ድርጊት “ግዳጅ” ተብሎ የሚጠራው የስርቆት አይነት

ግዳጅ   በኔ ላይ ሐምሌ 23/09 ዓ.ም እሁድ ፒያሳ አራዳ ህንፃ ፊት ለፉት የተሰራብኝ ድርጊት “ግዳጅ” ተብሎ የሚጠራው የስርቆት አይነት ነው። ይህም ድርጊት የተለያዩ አይነት መሳሪያዎችን በመጠቀም የሚከናወን የአዘራረፍ ሁኔታ ነው። እዚህ ፌስቡክ ላይ የሆነብኝ በመፃፌ ብዙዎች መትረፌ እንዳስደሰታቸውና ድርጊቱን በተመለከተ የሚሰማቸውንና የሚያሳስባቸውን ነገር አስታየት መስጫው ላይ አስፍረዋለ። አንዳንዶችም ሀሳብና ስድብ መሰል ነገር ፅፈዋል። (ሁላቹህንም አመሰግናለሁ)። 

ሁኔታውን ሳየው ብዙዎች ድርጊቱ እንዳስደነገጣቸውና በቀን በአደባባይ መፈፀሙ ግራ እንደገባቸው እንደተጠራጠሩ ተረድቻለሁ። ድርጊቱ ግን ምንም ይህል የሚያስደነግጥ ግራ የሚያጋባና የሚያጠራጥር ቢሆንም እኔ ላይ ግን ተፈፅሞብኛል። “ግዳጁን” የፈፀሙብኝ ወጣቶች ይህን ይመስላሉ አንደኛው መጀመሪያ ገጀራ የሰነዘረብኝ ሌዘር ጥቁር ካፖርት ያደረገ ፀጉሩን በአጭሩ የተቆረጠ በተለምዶ ቶርሽን የሚባሉትን ጫማ ያደረግ እረዘም ያለ ሰውነቱ የስፖርተኛ የሆነ ፊቱ የሞላ ቀላ ያለ ሁለተኛው ስልኩን የነጠቀኝ ቀጭን እረዥም ፊቱ ከሳ ያለ ፁጉሩ በትንሹ የተንጨባረረ አመደማ ሹራብ የለበሰ ሸራ ጫማ ያደረገ ጠይም፣ ሦስተኛው ቡርተካናማ ኮፍያ ያለው ቱታ የደረገ ገጀራ ይዞ የመጣ መካከለኛ ቁመት ያለው ሰውነቱ ሞላ ያለ ጠይም አራተኛው አረንጓዴ ከነቴራ የለበሰ አረዘም ያለ በገጀራ መንገድ እያስከፈተ የሄደ ጥቁር ልጅ ነው።

በእለቱ ለፖሊስ ጉዳዩን ሳመለከት በአካባቢው ላይ ከነበሩት ሰዎች መካከል 8 መስክሮች ቢገኙም ፖሊስ የበቃኛል ያለውን የሶስት ምስክሮች ቃል ተቀብሏል። እኔም ትላንት ሐምሌ 24/09ዓ.ም ህክምና ቦታ ሄጄ ህክምና ያገኘው ስሆን የህክምና ማስረጃውን ለፖሊስ ሰጥቻለሁ።  

ይህን የፃፍኩት ነገሩ በትክክል መከናወኑን አስረግጮ ማሳወቅ ስለፈለኩና ጉዳዩ ሀይ ባይ ካላገኘ ነገም ዛሬም በባሰ ሁኔታ በያንዳንዳችን ላይ “ግዳጅ” መሰራቱ እንደማይቀር ለማሳወቅ እና እኔም ነገሩን መከታተል እስከምችልበት መንገድ እንደምሄድ ግልፅ ለማድረግ ነው።

    ሐምሌ 25/09ዓ.ም

ታሪኩ ደሳለኝ

Advertisements

Author: mr☻n Ta Αβραάμ

Long live Ethiopia “When dictatorship is a fact, revolution becomes a right." victor Hugo

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Google+ photo

You are commenting using your Google+ account. Log Out /  Change )

Twitter picture

You are commenting using your Twitter account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

w

Connecting to %s