የኢትዮጵያ መንግሥት የፖለቲካ መብት ተሟጋቾችና ተቃዋሚ አካላት ላይ ስለላ እያደረገ እንደሆነ ተከሰሰ

internetcensorship-300x188

የኢትዮጵያ መንግሥት የገዛ ዜጎቹ ላያ የበይነ መረብ (ኢንተርኔት) ስለላ እያደረገ ነው ሲል ሂዩማን ራይትስ ዎች የተሰኘው የመብት ተሟጋች ድርጅት ወቀሰ።

የፖለቲካ መብት ተሟጋቾች እና ነፃ ድምፆች ላይ የሚያደርገውን ስለላም እንዲያቆም ድርጅቱ አሳስቧል።

ኅዳር 27/2010 የወጣው ሪፖርት እንደሚያሳየው የኢትዮጵያ መንግሥት የፖለቲካ መብት ተሟጋቾችና ተቃዋሚ አካላት ላይ ስለላ እያደረገ እንደሆነ መቀመጫውን ቶሮንቶ ያደረገ ‘ሲትዝን ላብ’ የተሰኘ የቴክኖሎጂ ተቋምን ጠቅሶ ድርጅቱ ዘግቧል።

የኢትዮጵያ መንግሥት መሰል ትችቶች ሲቀርቡበት የመጀመሪያው ባይሆንም አሁን ላይ ግን ስለላውን እጅግ አጠናክሮ ቀጥሏል ይላል ሪፖርቱ።

“የኢትዮጵያ መንግሥት ሃሳቡን የሚተቹ ዜጎች ላይ በየትኛውም የዓለም ክፍል ይሁኑ ስለላ ከማድረግ አልተቆጠበም” ሲሉ የሂዩማን ራይትስ ዎች ከፍተኛ አጥኚ ሲንቲያ ዎንግ ይናገራሉ።

“መሰል ስለላዎች የሰዎችን ሃሳብ የመግልፅ ነፃነት፣ ግላዊነት እንዲሁም የዲጂታል ደህንነት ይፈታተናሉ” ሲሉ ያክላሉ አጥኚዋ።

ከ2016 ጀምሮ ሲደረግ የነበረው ጥናት እንደሚጠቁመው ስለላው በርካታ የፖለቲካ መብት ተከራካሪዎችን ዒላማ ያደረገ ሲሆን በተለይ ደግሞ የኦሮሞ መብት ተሟጋቾች የስለላው ትልቅ አካል መሆናቸውን ድርጅቱ ያስታውቃል።

ከእነዚህም መካከል መቀመጫውን አሜሪካ ያደረገው የኦሮሚያ ሚድያ ኔትዎርክ ኃላፊ ጃዋር መሐመድ አንዱ መሆኑ ታውቋል።

የኦሮሚያ ሚድያ ኔትዎርክን ለማገድ ብዙ ሙከራዎችን ማድረጉን ያወሳው ሪፖርት የኢትዮጵያ መንግሥት ዜጎቹ መረጃ እንዳያገኙ እገዳ እያደረገ ነው ሲል ይወቅሳል።

የስለላው ተጠቂዎች በኤሌክትሮኒክ የመልዕክት መላላኪያ አድራሻቸው (ኢሜይል) በኮምፒውተራቸው ላይ የሚጫን ሶፍትዌር በመላክ የሰዎቹን የግል መልዕክት ማየት የሚያስችል ቫይረስ ተልኮላቸዋል።

ሶፍትዌሩን ኮምፒዩተራቸው ላይ የጫኑ ግለሰቦች የቫይረሱ ተጠቂ ሆነው የተገኙ ሲሆን፤ እነዚህም አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ኤርትራ፣ ካናዳና ጀርመንን ጨምሮ በሃያ ሃገራት ያሉ ኢትዮጰያውያን መሆናቸውም ታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ስለላውን ያከናወነው ከሃገር ቤትና መሠረቱን እስራኤል ካደረገ የሳይበር ደህንነት ኩባንያ ጋር በትብብር በመሆን እንደሆነም ታውቋል። ‘ሳይበርቢት’ የተሰኘው የእስራኤል ኩባንያው ‘ኤልቢት ሲስተምስ’ የተባለ ድርጅት አካል መሆኑም ተዘግቧል።

በስለላው ተጠቂ የሆኑ ግለሰቦች በኮምፒውተራቸው የሚያከናውኗቸውን ማንኛውም ዓይነት ተግባራትን የኢትዮጵያ መንግሥት መከታተል የሚችል ሲሆን ከዚህ አልፎም የኮምፒውተሩን ካሜራ በመጠቀም ቀጥታ ስለላ እንደሚያደርግም ድርጅቱ አጋልጧል።

ቴክኖሎጂው ወንጀልን በተለይ ደግሞ ሽብርተኝነት ለመከላከል ተብሎ የተፈበረከ እንደሆነ ታውቋል።

ከአውሮፓውያኑ 2013 ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት መሰል ስለላዎችን ሲያከናውን ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑን ደርጅቱ አስታውሷል።

ከዚህ በፊት ሂዩማን ራይትስ ዎችና ‘ሲትዝን ላብ’ የኢትዮጵያ መንግሥት ከጣልያን፣ እንግሊዝና ጀርመን ድርጅቶች ጋር በመተባበር ስለላዎችን ማከናወኑን ገልጿል።

ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ካዛኪስታን፣ ናይጄሪያ፣ ፊሊፒንስ፣ ሩዋንዳ ቬትናምና ዛምቢያም መሰል ስለላዎችን በማከናወን ድርጊት ተኮንነዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት በዚህ ብቻ ሳይወሰን የተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቃሚዎችንም እየሰለለ እንዳለ ያወሳው ሪፖርቱ ድርጊቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው ሲል ይኮንናል።

የፖለቲካ መብት ተሟጋቾች የሚያደርጉትን የስልክ ንግግር በመቅረፅና በምርመራ ወቅት በመጠቀም እንደ አፍ ማዘጊያ እየተጠቀመው ነው ሲልም ይወቅሳል።

ምንም እንኳ መሰል ቴክኖሎጂ የሚያመርቱ ድርጅቶች ከመንግሥታት ጋር ሽብርተኝተን ለመዋጋት እንደሚሰሩ ቢታወቅም የኢትዮጵያ መንግሥት ግን መሣሪያውን ተቃዋሚዎችን ለመስለል እየተጠቀመበት ነው፤ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪዎችን፣ እንዲሁም ተሟጋቾችን እያስፈራራበት ነው ባይ ነው ሪፖርቱ።

መንግሥት የግል ጋዜጦችን ከገበያው ገሸሽ ማድረጉን ተከትሎ ከ2010 ጀምሮ ቢያንስ 85 ጋዜጠኞች ሃገራቸውን ጥለው እንደተሰደዱ ድርጅቱ ያትታል።

ሂዩማን ራይትስ ዎች የሲትዝን ላብን ጥናት አጣቅሶ ሳይበርቢት የተሰኘው ድርጅት በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥና መሰል ድርጊቶች ሲፈፀሙ ቀጣዩ እርምጃ ምን እንደሆነ እንዲያሳውቅ መጠየቁን ዘግቧል።

ሳይበርቢት ቴክኖሎጂውን ለመንግሥታት ብቻ የሚሸጥ ሲሆን ሽያጩን ሲፈፀም ከሚመለከተው ከፍተኛ የመንግሥት አካል ፊርማ እንደሚጠይቅም አስታውቋል።

ሳይበርቢት በጉዳዩ ዙሪያ እንዲሰጥ ለተጠቀው አስተያየት ምላሽ ሲሰጥ ድርጊቱ መፈፀም አለመፈፀሙን አለማረጋገጡን አስታውቆ አስፈላጊውን ምርመራና እርምጃ ለመውሰድ ግን ዝግጁ መሆኑን ተናግሯል። እርምጃው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ውሉን እስከሟቋረጥና ድርጊቱ ከተፈፀመ ደግሞ በይፋ ለሕዝብ ማሳወቅን ሊያካትት እንደሚችል ጠቁሟል።

ሂዩማን ራይትስ ዎች እስራኤልን የመሰሉ ሃገራት ድርጅቶቻቸው መሰል ቴክኖሎጂዎችን ለሃገራት ሲሸጥ አስፈላጊው ምርመራ እንዲካሄድ በተለይ ደግሞ የሰብዓዊ መበት ጥሰት አለመፈፀሙን ማረጋገጥ እንዳለባቸው ይጠቁማል።

“የእስራኤል መንግሥት እያወቀ ሳይበርቢት የተሰኘው ኩባንያ ኢትዮጵያን ለመሰሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለሚያከናውኑ ሃገራት ቴክኖሎጂውን ሲሸጥ ዝም ካለ እጅግ አደገኛ ነው” ሲሉ ሲንቲያ ዎንግ ይደመድማሉ።

Advertisements

ትምህርት እድሜን እንደሚያስረዝም በጥናት ተረጋገጠ

ሰዎች በትምህርት ላይ የሚያሳልፉት እያንዳንዱ ዓመት በእድሜያቸው ላይ በአማካይ 11 ወራትን እንደሚጨምር ሳይንቲስቶች አረጋገጡ።

እድሜን ከሚያራዝሙ ነገሮች በተጨማሪ የሚያሳጥሩ በርካታ ምክንያቶች እንዳሉም አመልክተዋል።

አጥኚዎቹ እንደሚሉት አንድ ሰው ከልክ በላይ በሚጨምረው በእያንዳንዱ ኪሎ ግራም ከእድሜው ላይ ሁለት ወርን ሲቀንስ በቀን አንድ ፓኮ ሲጋራ የሚያጨስ ሰው ደግሞ ከዕድሜው ላይ ሰባት ዓመታትን ያሳጥራል።

የኤደንብራ ዩኒቨርሲቲ የጥናት ቡድን እዚህ ውጤት ላይ የደረሰው ባልተለመደ ሁኔታ የሰዎችን የዘረ-መላዊ መለያዎችንና የዘር ቅንጣቶችን ልዩነት በመተንተን ነው።

ተመራማሪዎቹ እንደሚያስቡት ውጤቱ ሰዎች ረጅም ዕድሜን እንዲኖሩ የሚያስችል አዲስ መንገድን ለማወቅ ያስችላል ብለዋል።

የአጥኚዎቹ ቡድን ግዙፍ በሆነው ተፈጥሯዊ የጥናት ሙከራ ላይ የተሳተፉ ከ600 ሺህ የሚበልጡ ሰዎችን ዘረ-መላዊ መለያዎችን ተጠቅመዋል።

አንድ ሰው በተመሳሳይ የሚያጨስ፣ የሚጠጣ፣ ትምህርቱን ያቋረጠ ከሆነና ከልክ ያለፈ ክብደት ካለው፤ ጤናማ ያልሆነውን የአንዱን ነገር ተፅዕኖ ለይቶ ለማወቅ አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።

ከዚህ ይልቅ አጥኚዎቹ ተፈጥሯዊ ወደሆነው ሙከራ ፊታቸውን መልሰዋል።

አንዳንድ ሰዎች በዘር ቅንጣታቸው ውስጥ ምግብን አብዝተው እንዲመገቡ የሚያደርግ ወይም ለውፍረት የሚያጋልጥ ተፈጥሮ ሊኖራቸው ይችላል።

ስለዚህም አጥኚዎቹ አብዝተውና በልኩ የሚመገቡ ሰዎችን ተጨማሪ የሕይወት ዘይቤዎችን ሳያካትት ለማነፃፀር ችለዋል።

ዶክትር ፒተር ጆሺ እንደሚሉት ”ክብደት መጨመር በቀጥታ በዕድሜ ላይ የሚያስከትለውን ውጤት በተመለከተ ለማወቅ ይቻላል። ይህም ትንተናውን አያፋልሰውም” ብለዋል።

ተመሳሳይ የተፈጥሮ ይዘቶችም ሰዎች በትምህርት ላይ የሚያሳልፉትን ዓመታትና በማጨስ ወይም በመጠጣት ከሚያገኙት እርካታ ጋር እንዲያያዙ ተደርገዋል።

የጥናት ቡድኑ በተጨማሪም በዘር ቅንጣቶች ውስጥ ዕድሜ ላይ ተፅዕኖ ያላቸው የተለዩ ይዘቶችን ማግኘታቸውን ሳይንሳዊ ጥናት በሚቀርብበት መጽሔት ላይ አስፍረዋል።

  • የተፈጥሮ በሽታን የመከላከል አቅማችንን የሚያንቀሳቅሱ በዘር ቅንጣቶች በእድሜያችን ላይ ሰባት ወራት ያህል ሊጨምሩ ይችላሉ።
  • በዘር ቅንጣት ላይ ለጤና ጠንቅ የሆነ ኮሌስትሮል እንዲጨምር የሚያደርጉ ለውጦች ሲኖሩ ደግሞ ከእድሜያችን ላይ ስምንት ወራትን ይቀንሳል።
  • ከእርጅና ጋር የሚመጣ አዕምሯዊና አካላዊ እክልን የሚያስከትለው ብዙም ያልተለመደ የዘር ቅንጣት ለውጥ ከዕድሜ ላይ 11 ወራትን ያሳጥራል።

ዶክተር ጆሺ እንደሚሉት እነዚህ የዘረ-መል ይዘቶች ላይ የሚታዩ ልዩነቶች ”በጣም ትንሽ ጉዳዮች ናቸው” ብለዋል።

በእድሜ ላይ ለውጥን ከሚያስከትሉ ልዩነቶች ውስጥ 20 በመቶ የሚሆኑት በዘር የሚመጡ ሊሆኑ ይችላሉ።

ነገር ግን አስካሁን ተለይተው የታወቁት 1 በመቶው ብቻ ናቸው።

ዶክተሩ እንደሚሉት ዘረ-መል በምንኖረው እድሜ ላይ ተፅዕኖ ያለው ቢሆንም ”እያንዳንዳችን በአኗኗር ዘይቤያችን ላይ በምናደርገው ምርጫ መሰረት የበለጠ ተፅዕኖ የማድረግ አቅም አለን” ብለዋል።

ዶክተር ጆሺ ለቢቢሲ እንደገለፁት ”እድሜ ላይ ተፅዕኖ ያላቸውን ቀዳሚ የዘር ቅንጣቶችን በመለየት ስለእርጅናና መፍትሄው አዳዲስ መረጃዎችን እናገኛለን ብለን ተስፋ እንደርጋለን”ብለዋል።

ረጅም ዕድሜ እንዳንኖር የሚያደርጉ የበሽታ አይነቶችም እንዳሉ ባለሙያዎቹ ጠቁመዋል።

ጣሊያናዊው ‘ረክሰዋል’ ያላቸውን ዘመዶቹን መረዘ

የጣሊያን ፖሊስ ከሃይማኖት አንፃር ‘ረክሰዋል’ ያለቸውን የቤተሰቡን አባላት በአይጥ መርዝ ገድሏል ያለውን ግለሰብ መያዙን አስታወቀ።

የ27 ዓመቱ ማቲያ ዴል ዞቶ መርዛማውን ታሊየም የተባለ ኬሚካል በምግባቸው ላይ በመጨመር በአባቱ በኩል ያሉትን አያቶቹንና አክስቱን ገድሏል ተብሎ ነው የተከሰሰው።

በተጨማሪም ሌሎች አምስት ዘመዶቹ በመርዙ ምክንያት ሆስፒታል ገብተው ህክምና እየተደረገላቸው ነው።

ፖሊስ ግለሰቡ ኮምፒውተር ውስጥ መርዙን የገዛበት ደረሰኝን ካገኘ በኋላ ነበር ዴል ዞቶን ሚላን አቅራቢያ በምትገኘው ሞንዛ ስፍራ በቁጥጥር ስር ያዋለው። ከተያዘ በኋላም በሰጠው የዕምነት ቃል ረክሰዋል ያላቸውን የቤተሰቡን አባላት ”ለመቅጣት” የፈፀመው ድርጊት እንደሆነ መናገሩን አቃቤ ህግ ገልጿል።

እናቱ ለመርማሪዎች እንደተናገሩት ዴል ዞቶ በቅርቡ ብዙም የማይታወቅ የዕምነት ቡድንን መቀላቀሉን የጣሊያን መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

ታሊየም በውሃ ውስጥ በቀላሉ የሚዋሃድ ሲሆን ሽታና ጣዕም አልባ መርዝ ነው።

German tourist shot dead in Ethiopia

A German tourist has been shot dead and a guide injured during a visit to a volcano in north-eastern Ethiopia.

They were part of a group which had travelled to the Erta Ale volcano.

It is not known who carried out the attack, but the Ethiopian government has launched an investigation, the BBC’s Emmanuel Igunza reports.

The Afar region, which straddles the border between Eritrea and Ethiopia, is known as an operating ground for several separatist groups.

Five years ago, the Afar Revolutionary Democratic Front – the most prominent of the groups – claimed responsibility for the deaths of five tourists and the abduction of four others in the Afar region.

The group seeks the creation of an independent Afar homeland, which would include areas of Ethiopia, Eritrea and Djibouti.

Despite the risks, tourists continue to visit the volcano – found in the heart of the Danakil Depression, which sits at 410ft (125m) below sea level.

By some measures the Danakil Depression is considered to be one of the hottest places on earth, with an average reported temperature of 34.4C, but only 100 to 200mm of rainfall per year.

Added to this heat is the volcano, with its lava lake – one of only six in the world, according to this report from the BBC, making it one of the most inhospitable places on the planet.

Afar police standing guard on the slopes of the Erta Ale volcano in the Afar region of East Africa in 2005

አራት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች(ቃና፣ ኢቢኤስ፣ ኤልቲቪና ናሁ) ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነው

Image may contain: text
Image may contain: text
No automatic alt text available.
Image may contain: text

 
ፈቃድ ሳያወጡ በሳተላይት አማካይነት በሀገር ውስጥ ቋንቋ ፕሮግራማቸውን በሚያሰራጩ አራት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ላይ እርምጃ ለመውሰድ የህዝብንና የፓርላማውን እገዛ እንደሚፈልግ የብሮድ ካስት ባለሥልጣን ተናገረ፡፡

ቃና፣ ኢቢኤስ፣ ኤልቲቪና ናሁ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ፈቃድ ተሰጥቷቸው ስርጭታቸውን የጀመሩት በውጭ ሀገር የተቋቋሙና በተቋቋሙበት ሀገርም ፈቃድ ያላቸው ናቸው በሚል ኃሣብ እንደነበርም ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡

ባደረኩት ማጣራት ግን አራቱም የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የሚሰሩትም ሆነ ገቢ የሚያገኙት በኢትዮጵያ መሆኑን ደርሼበታለሁ ብሏል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ቋንቋ የሚሰራጭ የቴሌቪዥን ጣቢያ የውጭ ሀገር ዜጋና ትውልደ ኢትዮጵያዊ በባለቤትነት ሊያስተዳድረው እንደማይችል የብሮድካስት አዋጅ ይደነግጋል፡፡

የአራቱ የቴሌቪዥን ጣቢያ ባለቤቶች ግን ትውልደ ኢትዮጵያዊና የውጭ ሀገር ዜጎች እንደሚገኙባቸው አውቄያለሁ ብሏል ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ፡፡

ወሬውን የሰማነው የባህል ቱሪዝምና መገናኛ ብዙሃን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱን የ2010 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ከመሥሪያ ቤቱ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ሲመክር ነው፡፡

የባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዘርአይ አስገዶም እንዳሉት ካለፈው ዓመት ጀምሮ ቃና፣ ኢቢኤስ፣ ኤል ቲቪና ናሁ የተሰኙ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ሕጋዊ ፈቃድ እንዲያወጡ እያነጋገርናቸው ነው ብለዋል፡፡

ፈቃዱን ለመስጠትም ከመካከላቸው በውጭ ሀገር ዜጋና በትውልደ ኢትዮጵያዊ በባለቤትነት የሚተዳደሩትም ባለቤትነቱን ለኢትዮጵያዊ እንዲያስተላልፉ ስንጠይቃቸው ቆይተናል ያሉት አቶ ዘርአይ እስካሁን ግን ተግባራዊ አላደረጉም ብለዋል፡፡

የቴሌቭዥን ጣቢያዎቹ ፈቃድ የማያወጡ ከሆነ ሕጉ በሚፈቅደው መልኩ እርምጃ እንወስዳለን፤ ለዚህም የህዝብንና የፓርላማውን ድጋፍ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ በ2010 ሩብ ዓመት የከወናቸው ሥራዎች ላይም ከሥራ ኃላፊዎቹ ጋር ውይይት እያደረገ ነው፡፡

SHEGER FM 102.1 RADIO

Kritik der UN-Migrationsagentur Facebook & Co – Plattform für Schlepper

Die Migrationsagentur der Vereinten Nationen hat Facebook und andere soziale Medien dazu aufgerufen, schärfer gegen Schlepper und Kriminelle vorzugehen. Die UN-Organisation kritisierte den aus ihrer Sicht nachlässigen Umgang mit Inhalten von Menschenschmugglern. Boote in einem Hafen in Libyen

Die sozialen Medien böten Schmugglern und Folterern Plattformen und täten zu wenig, um deren schmutziges Geschäft zu unterbinden, sagte der Kommunikationschef der Internationalen Organisation für Migration (IOM), Leonard Doyle, in Genf in einem ungewöhnlich emotionalen Appell.

“Soziale Medien geben Gangstern, Schmugglern, Schleppern und Ausbeutern eine Kommunikationsplattform mit Turbomotor”, sagte Doyle. “Die Menschen sind nur einen Klick von den Schleppern und ihren Lügen entfernt.”

“Facebook selbst muss tätig werden”

Die IOM versuche ständig, Facebook und anderen Plattformen zum Einschreiten zu bewegen, aber ohne Erfolg. “Sie sagen uns: ‘Zeigt uns die zu beanstanden Seiten und wir nehmen sie runter.’ Aber es ist nicht unsere Aufgabe, die Seiten auf Facebook zu überwachen, das muss das Unternehmen selbst tun”, sagte Doyle.

Wer pornografische Seiten aufrufe, bekomme oft ein Fenster eingeblendet mit einer Warnung vor Gefahren und kriminellen Aktivitäten. So etwas sei bei perfiden Angeboten von Schleppern auch möglich, sagte Doyle. Soziale Medien hätten die Verantwortung, die Menschen über die Risiken der Flucht mit einem Schlepper aufzuklären.

Folter in libyschen Lagern

Die Organisation hat nach Angaben Doyles in diesem Jahr gut 14.000 Migranten, die in Folterlager in Libyen gerieten, bei der Rückkehr in ihre Heimatländer unterstützt. Menschenhändler foltern dort Migration.

Icon facebook