ህወሀት መራሹ መንግስት በሀገሪቱ ህዝባዊ ተቃውሞ ሲነሳበት ወደ ውጪ ገንዘብ እንደሚያሸሽ ተገለጸ

ህወሀት መራሹ መንግስት በሀገሪቱ ህዝባዊ ተቃውሞ ሲገጥመው ከሀገሪቱ ካዝና እየመዘበረ ወደ ውጪ ሀገር በከፍተኛ ሁኔታ ገንዘብ እንደሚያሸሽ ባገኘነው መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ አዳማ (ናዝሬት) በመንግስት ስራ ላይ የሚገኝ አንድ ግለሰብ ለቢቢኤን በሰጠው አስተያየት ከአዲስ አበባ በመቀጠል በሀገሪቱ ከፍተኛ ግብር የሚከፈልበት ከተማ አዳማ ናት፡፡

በሆኑም በግብር ጫና ምክንያት ተቃውሞ ይነሳል በሚል ከፍተኛ የሆነ ስጋት ውስጥ እንዳለ ገልጿል፡፡ ህዝቡም ተቃውሞ እስኪነሳ እርስ በርሱ እየተጠባበቀ እንደሆነ ያስረዳል፡፡ ኢህአዲግ ተቃውሞ እንዳይነሳ በጣም የሚፈራው አዲስ አበባን ሳይሆን አደማን ነው፡፡ ከፍተኛውም ሀብታቸው ያከማቹት እዚህ ነው፡፡ የአዳማ ህዝብ ደግሞ አንዴ ከተነሳ መቆሚያ አይኖረውም ሲል አብራርቷል፡፡ አክሎም በሀገሪቱም ተቃውሞ በተነሳ ቁጥር በቦንድ እና በተለያዩ ጉዳዮች እያሳበቡ የሀገሪቱን ገንዘብ እያሸሹ ይገኛሉ፡፡ ህዝቡ ደግሞ ይሄን ነገር ትኩረት አይሰጥም በማለት ገልጿል፡፡

በተለያዩ ጊዜያት በወጡ ጥናቶች እንደሚያመክተው ካለለፈው አስር አመት ወደ ከሀገሪቱ በህገ ወጥ መንገድ እየሸሸ ያለው የገንዘብ መጠን ከ30 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሆነ ነው፡፡ በተለይም ከሁለት አመታት ወዲህ እየተመዘበሩ የሚወጡት የገንዝብ መጠን ማሻቀቡን ተገልጿል፡፡

በህዝብ የሚወደዱ ሰላማዊ የሕዝብ መሪ እጆቻቸው በወያኔዎች ታስሮ #ግርማ_ካሳ

 

የአዉሮፓ ሕብረት ስብሰባ ያደርጋል። በስብሰባው የተለያዩ እንግዶች ይጋበዛሉ። ዶር ብርሃኑ ነጋ እና ዶር መራራ ጉዲና ከተጋባዦች መካከል ነበሩ። እንዳጋጣሚ ሆኖ ሁለቱም ለተጋባዦች በተዘጋጀ ቦታ ጎን ለጎን ይቀመጣሉ። ስብሰባው አለቀ፤ ስምንታት አለፉ። ዶር መራራ ወደ አገርራቸው ይመለሳሉ። “ከዶር ብርሃኑ ነጋ ጎን ተቀምጠሃል፤ በሽብርትኝነት ተግባር ተሰማርተሃል” በሚል አስቂኝ ክስ ወደ ወህኒ ይወሰዳሉ።
ሕወሃቶች እጅግ በጣም ሲበዛ ቂመኞችና በቀለኞች ናቸው። በዶር መራራ ላይ ቂም ከቋጠሩ አመታት አልፏቸዋል። ዶር መራራ ሳይፈሩ ለፍትህ፣ ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነት ድምጻቸውን የሚያሰሙ በመሆናቸው ህወሃቶች ደስተኛ አልነበሩም። ሰበብ ነበር የሚፈልጉት፣ የአዉሮፓዉን ስብሰባ እንደ ሰበብ ቆጥረው እኝህን ታላቅ ሰው ይኸው በበቀል እያሰቃዩውቸው ነው።

ዶር መራራ በደርግ ጊዜ ወደ ስምንት አመት ታስረው የተፈቱ ናቸው። ለኦሮሞ ማህበረሰብ ብቻ ሳይሆን ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የሰሩና የደከሙ ፣ ትልቅ አስተዋጾ ያደረጉ ታጋይ ናቸው። በአገር ዉስጥ ሆነው፣ እስር፣ እንግልት፣ ግድያን ሳይፈሩ፣ በድፍረትና በወኔ የሕዝብን ብሶት የሚናገሩ፣ የሕዝብን ጥያቄ የሚያነሱና ለፍርሃት እጃቸውን ያልሰጡ፣ ቀና ብለው የሚኖሩ ሰዉ ናቸው።

ከጥቂት ቀናት በፊት ዶር መራራ ወደ ፍርድ ቤት ሲሄዱ የሚያሳይ ፎቶ ተመለከትኩ። ከፊትና ከኋላ በታጠቁ ሰዎች ተከበዋል። እጃቸው ወደ ኋላ በሰንሰለት ታስሯል። ነፍሰ ገዳይ፣ ተደባዳቢና አስቸጋሪ የሆኑ ይመስል።

ወያኔዎች ይሄን ሁሉ እንግዲህ የሚደርጉት በዋናነት የዶር መራራ ጉዲናን ስነ-ልቦና ለማዳሸቅና እርሳቸውን በመንፈስ ለመሰባበር ነው። ሆኖም ግን እንኳን ዶር መራራን ሊሰባብሩ በሺሆች የሚቆጠሩ መራራዎች እንዲነሱ ነው የሚያደርጉት። ሌላው ምክንያታቸው ለተቀረነዉን መልእክት ለማስተላለፍ ነው። “ እያንዳንድህ አርፈህ የማትቀመጥ ከሆነ ፣ ልክ ነው የምናገባህ። እንኳን አንተን ባለም ደረጃ የታወቁት ዶር መራራን አስረናል“ የሚል መልእክት። ነገር ግን የዘመኑ ወጣት ከጊዜ ወደ ጊዜ ፍርሃትን እያወለቀ የመጣበት ዘመን ነው። ከዝዚህ በኋላ የግፍ ቀንበር ለመሸከም ትከሻ ያለው አይመስለኝም።

ዶር መራራ እጅግ በጣም በሕዝብ የተወደዱ ሰው ናቸው። እርሳቸው መጡ ከተባለ፣ በተለይም በምእራብ ሸዋ ሕዝብ እንደ ማእበል ነው የሚሰበሰበው። እንግዲህ አስቡት በሕዝብ የተወደደን ሰው ነው ወያኔዎች በማሰር ለሕዝብ ያላቸውን ትልቅ ንቀትም እየገለጹ ያሉት። ሰዎቹ በባህሪያቸው ከሕዝብ ፍላጎት በተቃራኒው የሚሰሩ፣ ከሕዝብ ጋር ካልተጣሉ፣ ህዝብን ካላናደዱ፣ የሕዝብን ደም ካልመጠጡ እረፍት የማያገኙ መሆናቸው ነው እያሳዩ ያሉት።

ወያኔዎች ዶር መራራን በማሰርና በማሰቃየት የተጠቀሙ ይመስላቸው ይሆናል። ያሸነፉ ሊመስላቸው ይችላል። ዶር መራራ “ከጫካ ወጡ እንጅ ጫቃ ከነርሱ አልወጣም” እንዳሏችው፣ ሌላውን በማሰር፣ በመግደል፣ በመርገጥ አሽናፊ ለመሆን መሞከራቸው የጫካ ባህሪያቸውን፣ ትንሽነታቸውን ፣ በራሳቸው የማይተማመኑና የበታችነት ስሜት የተሞሉ insecured መሆናቸውን ከማሳየት ውጭ በዘለቂነት የሚያገኙት ምንም ትርፍ አይኖሩም።

ለዶር መራራ እግዚአብሄር ባሉበት ብርታትና ጥንካሬ እንዲሰጣቸው እጸልይላቸዋለሁ። እኝህ የሕዝብ መሪ (የኦሮሞው ብቻ ሳይሆን የሁሉም ኢትዮጵያዊ) ህዝብ እያለ አንድ ቀን በወህኒ መቆየት የለባቸውም። ዶር መራራን እና በሺሆች የሚቆጠሩ አገራቸው በመዉደዳቸው ብቻ በግፍ የታሰሩ ወገኖቻችን ለማስፈታት ሁላችንም በአዲስ መልክ መንቀስቀስ ይኖርብናል። ከንፈር መጣጮችና ጠረቤዛ ደብዳቤዎች ብቻ ሳይሆን፣ በስትራቴጂና በአንድነት መንቀሳቀስ መጀመር አለብን።

የሕዝብ ማእበል ለዶር መራራ ፍቅሩን ሲገለጽና ዶክተሩ ለሕዝብ ንቀት ባላቸው ወያኔዎች እጆቻቸው እንደ ወንበዴ ታስረው የሚያሳዩ ፎቶዎች ይመልከቱ።

አስቸኳይ ግዜ አዋጁ ሲወጣ የፀረ-ሽብር ሕጉ መጣ

ስዩም ተሾመ

ላለፉት አስር ወራት በሀገሪቱ ላይ ተጥሎ የነበረው የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ በዛሬው ዕለት ተነስቷል። በእርግጥ መንግስት አዋጁ የተቀመጠለትን ዓላማ እንዳሳካ ገልጿል። ይሄን የተለመደ ፕሮፓጋንዳ ወደ ጎን በመተው የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ በተጨባጭ ያመጣው ለውጥ ከወደፊቱ የሀገሪቱ ፖለቲካዊ ሁኔታ አንፃር እንዴት ይታያል? በዚህ ፅሁፍ ከአስቸኳይ ግዜ አዋጁ መነሳት ጋር ተያይዞ ያሉትን አንዳንድ ሁኔታዎች በአጭሩ እንዳስሳለን።

መነሻ ይሆነን ዘንድ በመጀመሪያ የራሱን የግል ገጠመኝ ላካፍላችሁ። አንዳንዶቻችሁ እንደምታውቁት የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ከመታወጁ በፊት ታስሬ ነበር፡፡ የታሰርኩበት ዕለት መስከረም 20/2009 ዓ.ም ሲሆን የተከሰስኩበት ወንጀል “ሕዝብን ለአመፅ የሚያነሳሱ ፅሁፎችን ፅፈሃል፣ የጦር መሳሪያ በመኖሪያ ቤትህ ውስጥ ይገኛል” በሚል ወንጀል ነበር። በወሊሶ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እያለሁ መስከረም 28/2009 ዓ.ም የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ታወጀ። በማግስቱ ፖሊስ ጣቢያ ሊጠይቁኝ ከመጡ የስራ ባልደረቦቼ አንዱ የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መታወጁን ነገረኝ። እኔም እንደ ልማዴ በብጣሽ ወረቀት ላይ ማስታወሻ ያዝኩኝ። የማስታወሻው ጭብጥ የሚከተለው ነበር፡-

“ከስሙ መረዳት እንደሚቻለው “የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ” የአጭር ግዜ መፍትሄ ነው። ሕዝቡ እያነሳ ላለው የመብት፥ ነፃነትና ተጠቃሚነት ጥያቄ ዘላቂ ምላሽ ለመስጠት አያስችልም። ሆኖም ግን፣ አዋጁ ትግባራዊ በሚሆንባቸው ቀጣይ ወራት ለችግሮቹ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችል ዘዴ ለመቀየስ በቂ ግዜ ነው። በመሆኑም፣ የኢህአዴግ መንግስት የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ሕዝቡ ለሚያነሳቸው ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ጥረት ማድረግ አለበት።”

መስከረም 30/2009 ዓ.ም የወሊሶ ከተማ ፖሊሶች በታሰርንበት ክፍል ውስጥ ድንገተኛ ፍተሻ በማድረግ ከላይ የተጠቀሰውን ማስታወሻ ከኪሴ ውስጥ ወሰዱ። ከተወሰኑ ቀናት በኋላ ይህን ፅሁፍ እንደ ማስረጃ በመጥቀስ “የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን በመጣስ አመፅ ቀስቃሽ ፅሁፎችን በመፃፍና ለማሰራጨት ሲሞክር እጅ-ከፍንጅ ተይዟል” በሚል ተከሰስኩ። በዚህ ምክንያት ጉዳዩ በአስቸኳይ ግዜ አዋጁ በተቋቋመው ኮምንድ ፖስት መታየት አለበት በሚል ጥቅምት 17/2009 ዓ.ም ወደ ጦላይ ተወሰድኩ። ከዚህ ገጠመኝ በመነሳት ብዙ ነገር ማለት ይቻላል። ከእነዚህ ውስጥ እስኪ የተወሰኑትን ነጥቦች በማንሳት እንመልከት።

በመጀመሪያ ደረጃ እኔ የታሰርኩት በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 29 መሰረት ሃሳብና አመለካከቴን በነፃነት ስለገለፅኩ ሲሆን የተከሰስኩት አንቀፅ ደግሞ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ነው። በእርግጥ የፀረ-ሽብር አዋጁ በወጣ የመጀመሪያ አመስት አመታት ውስጥ ብቻ 10 ጋዜጠኞች ሲታሰሩ 57ቱ ደግሞ ለስደት ተዳርገዋል። የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ከወጣ በኋላ ደግሞ ይሄው አፈና ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠሉ ይታወቃል። የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ከተነሳ በኋላ ደግሞ የፀረ-ሽብር አዋጁ የቀድሞ አገልግሎቱን መስጠት ይጀምራል። በመሆኑም፣ የዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብትና ነፃነት እንደ ቀድሞ ይታፈናል። ዛሬ ላይ አስቸኳይ ግዜ አዋጁ ተነስቷል፡፣ አምባገነንነት ግን ይቀጥላል።

በድጋሜ ከላይ ወደተጠቀሰችው ፅሁፍ ስንመለስ፣ አንዲት ብጣሽ ወረቀት ለከፋ ስቃይና እንግልት ዳርጋኛለች። ከሁሉም በላይ የሚቆጨኝ ግን በስጋቴ እውን መሆኑ ነው። ከፅሁፉ ጭብጥ መረዳት እንደሚቻለው፣ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን እንደ ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ሀገሪቱ ላጋጠማት ፖለቲካዊ ችግር ዘላቂ መፍትሄ መፈለግ ይቻል ነበር። በእርግጥ ከአስቸኳይ ግዜ አዋጁ በስተጀርባ ያለው ምክንያት የኢህአዴግ መንግስት አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ያለበት ችግር ነው። አዋጁ ተግባር ላይ በዋለባቸው አስር ወራት የኢህአዴግ መንግስት እነዚህን ችግሮች በዘላቂነት ለመቅረፍ በሚያስችል መልኩ ሥር-ነቀል ለውጥና መሻሻል ለማምጣት ያደረገው ጥረት እዚህ ግባ የሚባል አይደለም።

በመሆኑም፣ ¨Crisis is the best opportunity to miss” እንደሚባለው፣ የኢህአዴግ መንግስት ከፀጥታና አለመረጋጋት ችግሩ መንስዔ የሆኑትን ችግሮች በመለየት ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት የሚችልበትን ምቹ አጋጣሚን ሳይጠቀምበት ቀርቷል። ለዚህ ደግሞ ዋናው ምክንያት የገዢው ፓርቲ አመራሮችና ደጋፊዎች ዘንድ የሚስተዋለው የተዛባ አመለካከት ነው። አብዛኞቹ የመንግስት አመራሮችና ደጋፊዎች በተለያዩ የሀገራችን አከባቢዎች የታየው አመፅና ተቃውሞ፣ እንዲሁም ይህን ተከትሎ የተከሰተው የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር በፀረ-ሰላም ኃይሎች እና አፍራሽ አጀንዳ ባላቸው ሚዲያዎች፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ መሪዎች፥ ጋዜጠኞችና የመብት ተሟጋቾች፣ እንዲሁም በገዢው ፓርቲ ውስጥ ባለው የኪራይ ሰብሳቢነት፥ ጠባብ ብሔርተኝነት እና የትምክህት አመለካከት ምክንያት እንደሆነ ሲጠቅሱ ይሰማል። የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን ግን ዜጎች ለአመፅና ተቃውሞ አደባባይ የሚወጡት “በሚያገኙት እና ማግኘት በሚገባቸው” መካከል ያለው ልዩነት ይበልጥ እየሰፋ በመሄዱ ምክንያት እንደሆነ ይገልፃሉ።

ህዝባዊ አመፅና ተቃውሞ ወደ ሁከትና ብጥብጥ፣ ብሎ ወደ ግጭትና አለመረጋጋት ሊያመራ የሚችልበት ምክንያት ግን የመንግስት አፀፋ እርምጃ ነው። የሕዝብ ጥያቄ ከፖለቲካዊ መብትና ነፃነት፣ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ጋር የተያያዘ ነው። ሕዝቡ የሚያነሳውን ጥያቄ መንግስት በአግባቡ ተቀብሎ ተገቢ ምላሽ የሚሰጥ ከሆኑ የአደባባይ አመፅና ተቃውሞ ወደ ሁከትና ብጥብጥ አያመራም፡፡ በተቃራኒው፣ የሕዝቡን ጥያቄ በኃይል ለማፈን ጥረት የሚያደርግ ከሆነ ግን የህዝቡ ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ ወደ ግጭትና አለመረጋጋት ያመራል።

ከአስቸኳይ ግዜ አዋጁ መታወጅ በፊት በነበሩት አመታት ዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸውን በአመፅና ተቃውሞ ካልሆነ በስተቀር በመደበኛ የፖለቲካ አካሄድ እንዳይጠይቁ ተደርገዋል። መደበኛ የተባሉት መንገዶች በሕገ-መንግስቱ ላይ በግልፅ የተቀመጡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ፤ አንቀፅ 29፡- “የአመለካከትና ሃሳብን በነፃ የመያዝና የመግለፅ መብት”፣ አንቀፅ 30፡- “የመሰብሰብ፥ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ ነፃነትና አቤቱታ የማቅረብ መብት”፣ እንዲሁም አንቀፅ 31፡- “የመደራጀት መብት” በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ናቸው።

ሆኖም ግን፣ ከላይ የተጠቀሱት ዴሞክራሲያዊ መንገዶች ከሞላ-ጎደል በፀረ-ሽብር ህጉ ተገድበዋል። ስለዚህ፣ በአመፅና ተቃውሞ ካልሆነ በስተቀር ዜጎች ሃሳብና አመለካከታቸውን፣ ቅሬታና አቤቱታቸውን ሊገልፁ የሚችሉበት መንገድ የለም። ባለፈው አመት በኦሮሚያ፥ አማራና በደቡብ ክልሎች የታየው ሕዝባዊ አመፅና ተቃውሞ ዋና ምክንያቱ የፀረ-ሽብር አዋጁ ነው። በዚህ ምክንያት ዜጎች “የተሻለ መብትና ነፃነት፣ እንዲሁም ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ይገባናል” የሚል ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ ለማንሳት የሚችሉበት መተንፈሻ ቀዳዳ ሲያጡ በአመፅና ተቃውሞ አደባባይ ወጡ። በእነዚህ ዜጎች ላይ የተወሰደው የኃይል እርምጃ ሁኔታውን እያባባሰው በመሄዱ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ታወጀ።

በዛሬው ዕለት የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ሲነሳ ለአመፅና ተቃውሞ መነሻ የነበረው የፀረ-ሽብር አዋጁ ወደ ቀድሞ ተግባሩ ይመለሳል። ይህ ደግሞ በተራው ለሌላ አመፅና ተቃውሞ ይወልዳል። “ይህን አመፅና ተቃውሞ ዳግም በአስቸኳይ ግዜ አዋጅ መቆጣጠር ይቻላል ወይ”? የሚለውን ወደፊት አብረን እናያለን። ለአሁኑ ግን የቀድ-አውጣ ኑሮ ይቀጥላል፡፡ የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ ሲወጣ የፀረ-ሽብር ሕጉ መጣ፣ ነገደ ቀንድ-አውጣ ከቤት እንዳትወጣ!

የህወሓት መፈርከስ የኢትዮጵያን ትንሳኤ ያቀርባል !

በህወሓት/ኢህአዴግ ውስጥ የዓላማ ሳይሆን የጥቅም ግጭት ተፈጠረ። ” ጅብ ሲሰርቅ ይስማማል ሲካፈል ነው የሚጣላው ” እንደ ሚባለው ሰሞኑን የህወኃት/ኢህአዴግ ሰዎች በማን አለበኝነት ለ26 ዓመት እነሱ እና መሰሎቻቸው የዚችን ምስኪን አገር ሀብትና ንብረቷን በመዝረፍ እነሱ እንደሚሉት በእድገት ጎዳና ያለች አገር ሳትሆን እጅግ ኃላ ቀር ከሚባሉ አገሮች የአገር ጭራ አድርገዋት ትገኛለች።

በመሆኑም ይህ ስርዓት በከፍተኛ ደረጃ በሙስና የተዘፈቀና አገሪቱን ለከፋ ድህነት ከመዳረጉም በላይ ለዕዳ ዳርገዋት ይገኛሉ። ይህን አገራዊ ችግር የተናገሩ ሙሁራን፣የፖለቲካ ሰዎች፣የራሳቸው አባል የሆኑ ሳይቀር ተገድለዋል ፣ታስረዋል፣ከአገር በግፍ ተሰደዋል።

ከዚያም ጉዳዩ ይህ ስርዓት በስልጣን ላይ ካለ ሙስናን መከላከልም ሆነ ዘራፌዎችን በህግ ለመጠየቅ የማይቻል በመሆኑ በሁሉም መልኩ የተዘጉትን መንገዶች ማለትም የዴሞክራሲ( የፖለቲካ)፣የኢኮኖሚ፣የማህበራዊ መብቶችን ማስፈን የሚቻለው በኃይል እንጅ በሰላማዊ ወይም በልመና እንዳልሆነ ያመኑ የትጥቅ ትግልን በአማራጭነት በመያዝ በአሁኑ ሰዓት ስርዓቱን ለከፋ ችግር እንዲወድቅና በርካታዎቹን ከጎናቸው በማሰለፍ ለህዝብ አሊንታና መኩሪያ ለጠላት ደግሞ ድንጋጤና ፍርሃትን ለቆበት ይገኛል።

በሌላ በኩል የራሱ የስርዓቱ ሰዎችም ቢሆኑ ሙስናን፣ስልጣንን ያላግባብ መጠቀምን፣ በተለያዩ ፕርጀክቶች ስም የተመደበን ገንዘብ መዝረፍ ይቁም ማለትና መጠየቅ በራስ ላይ እንደመፍረድ የተቆጠረ ሆነ ፣ ከዚያም ዝርፊያውን በጋራ ተያያዙት ከዚህ ላይ ግን ግጭቶች ብቅ አሉ እሱም ቁልፍ እና በርካታ ገንዘብ የሚዘረፍባቸውን ቦታዎች እኔ ልያዝ እኔ ልያዝ በሚል፣ከዚያም ህወኃት ያለውን ጡንቻ በመጠቀም ቦታዎችን ጠቅልሎ ያዘ ከዚያም ከፍተኛ ገንዘብ የሚመደብላቸው ድርጅቶችን መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ ሜቴክን መሰረቱ በዚህ ድርጅት አማካኝነት አገሪቱ እንዴት በዘራፊዎች እየተቦጠቦጠች እንደሆነ ሁላችንም እያየን ነው።

ከዚያም ህዝቦች ኧረ ባካቹህ ሙስና የስርዓቱ መገለጫ ሆነ፣ህዝብ ድህነት አጠቃው፣ ጥቂቶች እጅግ በለፀጉ ብሎ ሲጠይቅ ለተወሰነ መልስ ወይም ማስታገሻ ይሆን ዘንድ ምስኪኑን የበታች ሰራተኛ ሰብስቦ በማሰር በራሱ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ” ሙሰኞችን በቁጥጥር ስር አዋልናቸው” እያለ ይለፈልፋል ይህን የሰሙ አንድ አዛውንት አንድ የአገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣን በሚመሩት የህዝብ መድረክ ላይ የሚከተለውን ቃል ተናገሩ
” አንድ ሰው መንገድ ወጥቶ እየሄደ ሳለ ይመሽበትና ከእንድ ቤት አሳድሩኝ ብሎ ይገባል ሰዎችም እሽ ብለው የመሸበትን እንግዳ ተቀብለው ወደ ቤት አስገቡት በቤቱ ባል ሚስትና አንድ ልጅ ብቻ ይኖራሉ፣ ከዚያም ራት እየተበላ በጫወታ ላይ ድንገት ሚስት ያመልጣቸዋል ከዚያም ደንገጥ አሉ እና አንተ ልጅ ብለው ከእንግዳ ፊት እንዴት እንዴህ ታደርጋለህ ብለው ልጅን በኩርኩም ይመቱቷል፣ ከዚያም ትንሽ ይቆይና ባል ድንገት ያመልጣቸዋል እሳቸውም ደንገጥ በማለት አሁንም ልጃቸውን አንተ ባለጊ በማለት በኩርኩም ይመቱታል ከዚያም ጫወታው ያልቅና እንግዳው ከመቀመጫቸው ሲነሱ እሳቸውም ያመልጣቸዋል ሰውየው ደንገጥ ብለው የት አለ ያነ የፈረደበት ልጅ በሉ አምጡትና እኔም በኩርኩም ልበለው አሉ” በማለት ተረቱባቸው የናንተም የሙስናው ትግል እንዲህ ነው አሏቸው።

እንግዲህ በአገሪቱ ያለው የሙስና ሁኔታ ከህዝብ የተደበቀ እንዳልሆነና ሙሰኞች እነማን እንደሆኑ ጠንቅቆ ያውቃል ስለሆነም ይህን ህዝብ ማታለል የማይቻልበት ደረጃ ተደርሷል ህወሓት/ ኢህአዴግ በሚከተሉት ነገሮች አጣብቅኝ ውስጥ ገብቷል።
1ኛ፣ ጂቲፒ እያለ በየ አምስት ዓመት የሚያቅዳቸው እቅዶች ከወረቀት አልፈው ጠብ የሚል ነገር አላሳዩም ይባስብለው ህዝብን በማፈናቀል እና አገሪቱን ለዕዳ ከመዳረግ ያለፈ የፈየዱት አለመኖሩ
2ኛ፣ስርዓቱ ከዓመት ዓመት እየወረደና በተለይ በአሁኑ ሰዓት በነፃነት ታጋዬች በሁሉም ዘርፍ ( በትጥቅም ትግል፣በዲፕሎማሲ) መወጠሩ በስርዓቱ አገልጋዬች ላይ ለፍተኛ ስጋት በመደቀኑ እነዚህም ህዝቡ ቃል የገባንለት ነገር ባለማሳካታችን በጥያቄ እያስጨነቀን ነው የሚሉና እኛ ምንም ሀብት ሳንይዝ ሊሎች በዘረፉት የነሱ አገልጋይ ሁነን ነገ ልንጠየቅ ነው ስለዚህ ከአለንበት ከክልል ኃላፊነት ወደ ላይ አውጡን ወይም አባሳደር አድርጋቹሁ ሹሙን የሚል ጥያቄ በብዛት መምጣት ጀምራል።

በተለይ ለዛሬ መነሻ የሆነን በአገሪቱ የስኳር አቅርቦትን ይፈታሉ የተባሉ ፉብሪካዎች በልዩ መልኩ አደረጃጀትና አመራር ተመድቦላቸው የነበሩ ፉብሪካዎች የውሃ ሽታ መሆናቸውና የተበላው ገንዘብ ደግሞ የትየለሌ መሆኑ ከፍተኛ መነጋገሪያ ከሆነ ውሎ አድራል ወያኔም ለጥያቄው ቅድም አንድ አባት እዳሉት ዋናዎቹ መሪዎች እነ አባይ ፀሀዪ ተቀምጠው ታችኞችን ማሰሩ መፍቴሄ አለመሆኑ እውነታው እየተገለፀ መጥቶ በአሁኑ ሳዓት የነአባይ ፀሀዪ ቡድን እና የሌሎቹ ቡድኖች ትንቅንቅ ውስጥ ገብተዋል።

በመሆኑም ይህ የበሰበሰ ስርዓት አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል በተለይ ሙስና መገለጫ የሆነበት” በሙስና የተጨማለቀ ስርዓት በሁለት ጎን ይወጠራል ይህም ሙስናን ልዋጋው ቢል ስርዓቱ ይፈርሳል፣ሙስናን ዝም ብሎ ቢመለከትም ይፈርሳል” ስለዚህ ይህ ስርዓት ፈራሽ መሆኑን አውቀን ግብዓተ መሪቱን የማፉጠን ስራ ከሚሰሩት የነፃነት ታጋዬች ጎን እድንሰለፍ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

 

የወልቃይት ማንነት ጥያቄ ያነሱ 12 ግለሰቦች በሽብር ወንጀል ተከሰሱ

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በክሱ ላይ የሽብር ቡድን አመራር መባላቸውን ጠበቆች ተቃውመዋል ተከሳሾቹ ከጎቤ መልኬና ከኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጋር በመገናኘት ወልቃይት ውስጥ የሚገኙትን የመንግስት ደጋፊዎችና የትግራይ ተወላጆችን የሰፈራ ቦታ በመለየት ጥቃት ለመፈፀም ተንቀሳቅሰዋል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

የወልቃይት አማራ ማንነት ጥያቄን ያነሱ 12ቱ ግለሰቦች ‹‹የወልቃይት አማራ ማንነት ጥያቄን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ከዞን እስከ ክልል ከዚያም አልፎ እስከ ፌዴሬሽን ጥረት ሲያደርጉ ነበር።

አሁን ግን ጥያቄያቸው ተግልብጦ በሽብር ወንጀል ተከሰዋል። ተከሳሾቹ የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባል በመሆን በመደራጀትና የጦር መሳሪያ በመታጠቅ በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት አድርሰዋል፥ የአካባቢው ነዋሪ ላይም ከባድ ስጋት ፈጥረዋል›› በሚል ተወንጅለዋል፡፡

ተከሳሾቹ ከጎቤ መልኬና ከኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጋር በመገናኘት ወልቃይት ውስጥ የሚገኙትን የመንግስት ደጋፊዎችና የትግራይ ተወላጆችን የሰፈራ ቦታ በመለየት ጥቃት ለመፈፀም ተንቀሳቅሰዋል የሚል ክስም ቀርቦባቸዋል፡፡ ተከሳሾቹ በተለይ ከኮሌኔል ደመቀ ዘውዱ ጋር በመገናኘት የወልቃይት አማራ የማንነት ጥያቄን ለመመለስ የመንግስት ደጋፊዎች ላይ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው ተልዕኮ ወስደዋል በሚልም ተፈርጀዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በአርማጭሆና ወልቃይት ከሚገኙ የግንቦት ሰባት ታጣቂዎች፣ እንዲሁም በክሱ የግንቦት 7 አመራር ነበር ከተባለው ጎቤ መልኬ ከሚመራቸው 80 ያህል ታጣዊዎች ጋር ጫካ ገብተዋል ይላል በሕወሀት ኣአቃቤ ሕግ የቀረበባቸው የክስ ሰነድ። ወልቃይት ውስጥ በነበረ የመንግስት ጦር ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የትግራይ ተወላጆችና ባለሀብቶች የሰፈራ መኖሪያ ካምፖች ላይ ጥቃት አድርሰዋልም ነው የተባሉት፡፡

ከተከሳሾቹ መካከል አብዛኛዎቹ ወልቃይት ውስጥ የሚኖሩ ሲሆኑ መኖሪያቸው ሰ/ጎንደር ጠገዴ ወረዳ የሆኑ ሁለት ተከሳሾች ‹‹እኛንም የወልቃይት ጥያቄ ይመለከተናል›› ብለው አብረው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር በክሱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

በሌላ በኩል የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ጠበቃ የደንበኛቸው ጉዳይ በሌላ ፍርድ ቤት እየታየ ባለበት ሁኔታ በዚህ ክስ ‹‹የሽብር ቡድን አመራር›› ተብለው መጠቀሳቸው የኮሎኔሉን በህግ ፊት ንፁህ ሆኖ የመታየት መብት የነፈገ መሆኑን በመግለፅ ተቃውሞ አቅርበዋል፡፡ በሌሎች ክሶች ላይም ኮሎኔሉ በተመሳሳይ ሁኔታ የተጠቀሱ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ጠበቆቹ አቤቱታቸውን በክስ መቃወሚያ ማቅረብ እንደሚችሉ አሳውቋል፡፡

 

የአረበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጲያ ዕዝ ታጋዬች በወያኔ ወታደራዊ ቃኝዎች ላይ ጥቃት ፈፀሙ

በሰሜን ጎንደር ዞን በበለሳ ወረዳ ዞዛ አለፋ ቀበሌ ከደቡብ ጎንደር ዞን እብናት ወረዳ ካለው የወያኔ ማዘዣ ቀጠና ለቅኝት የተንቀሳቀሱ ወታደሮች ሀምሌ 21 ቀን 2009ዓ/ም ምሽት ላይ በተጠቀሰው ቦታ የአግ7 ታጋዬች በደፈጣ በወሰዱት የማጥቃት እርምጃ 1 ወታደር ወዲያውኑ ሲሞት 1 ደግሞ ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሶበት ለህክምና ወደ ባህርዳር ተወስዳል፣ የቀሩት እግሪን አውጭኝ ብለው በመሮጥ ወደ መጡበት ተመልሰዋል።

ሟቹ ዛሬ ንጋት ላይ አስከሪኑን አንስተው ወደ እብናት ከተማ ያመጡት ሲሆን ከዚህ ይቀበር ወይስ ወደ ቤተሰቦቹ ይወሰድ በሚለው ክርክር ላይ ነበሩ።

በመሆኑም የአረበኞች ግንቦት ፯ የሰሜን ኢትዮጵያ እዝ ተደጋጋሚ እንደገለፀው ወታደሮችን የመግደል አላማ የለውም ትግሉ እነሱንና የኢትዮጲያን ህዝብ እየረገጠና እየጨቆነ ካለው ስርዓት ጋር በመሆኑ ይህን አውቃቹሁ ስርዓቱን በመክዳት ከነፃነት ታጋዬች ጋር እድትቀላቀሉ በድጋሜ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን ።

የአረበኞች ግንቦት 7 የሰሜን ኢትዮጵያ እዝ

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬች የፖሊስ ጽ/ቤት ላይ ጥቃት ፈፀሙ

dr-berhanu-1

ሀመሌ 30 ቀን 2009ዓ/ም ከምሽቱ 4:20 ሲሆን በደቡብ ጎንደር ዞን በእብናት ወረዳ የወረዳውን ፖሊስ ጽ/ቤ/ት በቦንብ ጥቃት ደረሰበት ::

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀጠናው የአርበኞች ግንቦት 7 ታጋዬች ተደጋጋሚ ጥቃት በመፈፀማቸው የወረዳው ፖሊስ አዛዥን ጨምሮ ሊሎች የፀጥታ አመራሮች እንደማዘዣ ጣቢያ የሚጠቀሙት ይህን ፖሊስ ጽ/ቤት ነው።

በመሆኑም በጥናት በተመሰረተ መልኩ በትናንትናው ምሽት ይህ ጥቃት ተፈፅማል ፣የደረሰውን ጉዳት በተመለከተ ዝርዝሩ እደደረሰን እንገልፃለን።