ደራሲ፣ ዲፕሎማት፣ አርበኛ፣ መምህር የክብር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ ከነኀስ የተሠራ ኃውልት ቆመላቸው

ለክብር ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (1902 ዓ.ም. -1996 ዓ.ም.) መታሰቢያ የቆመ ከነኀስ የተሠራ ኃውልት፤ ቅዳምን ገበያ - ደብረ ማርቆስ፤ ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 28/2009 ዓ.ም.

ለክብር ዶ/ር ሀዲስ ዓለማየሁ (1902 ዓ.ም. -1996 ዓ.ም.) መታሰቢያ የቆመ ከነኀስ የተሠራ ኃውልት፤ ቅዳምን ገበያ – ደብረ ማርቆስ፤ ቅዳሜ፣ ሚያዝያ 28/2009 ዓ.ም.

 

ደራሲ፣ ዲፕሎማት፣ አርበኛ፣ መምህር የክብር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ ከነኀስ የተሠራ ኃውልት ቆመላቸው፡፡

ጥቅምት 5/1902 ዓ.ም. ተወልደው ኅዳር 26/1996 ዓ.ም. ላረፉት ለሀዲስ ዓለማየሁ ደብረ ማርቆስ ከተማ ላይ የቆመውን ከነኀስ የተቀረፀ ኃውልት መርቀው የገለጡት የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሂሩት ወልደማርያም ናቸው፡፡

ዶ/ር ሂሩት ወልደማርያም፤ የኢትዮጵያ የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ለሀዲስ ዓለማየሁ የቆመውን ኃውልት ሲመርቁ

ዶ/ር ሂሩት ወልደማርያም፤ የኢትዮጵያ የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ለሀዲስ ዓለማየሁ የቆመውን ኃውልት ሲመርቁ

ደብረ ማርቆስ ከተማ ቅዳምን ገበያ ላይ ዛሬ በተከናወነው ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ባሠራው የክብር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ ኃውልት ምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ ቁጥሩ የበዛ የከተማዪቱ ነዋሪና ከሌሎችም አካባቢዎች የተሰባሰበ ሰው ተገኝቷል፡፡

የክብር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ በሕይወት ሳሉ ያላሣተሟቸው ግጥሞቻቸውን የያዘ በዶ/ር ታየ አሰፋ የተዘጋጀና በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሀዲስ ዓለማየሁ ጥናት ተቋም ዓመታዊ ጉባዔ ታትሞ እንዲወጣ የተደረገ መፅሐፍም ዛሬ ይፋ ተደርጓል፡፡

ለክብር ዶክተር ሀዲስ ዓለማየሁ የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ያዘጋጀው የፖስታ ቴምብር በኢትዮጵያ የፖስታ ድርጅት በ2002 ዓ.ም. ታትሞ ተሠራጭቷል፡፡

«የአበሻና የወደኋላ ጋብቻ፣ ተረት ተረት የመሠረት፣ ፍቅር እስከ መቃብር፣ ወንጀለኛ ዳኛ፣ የልም ዣት፣ ትዝታ» የሀዲስ ዓለማየሁ አዕምሮ ውልዶች ናቸው፡፡

ለተጨማሪ ከቅዳምን ገበያ፣ ደብረማርቆስ የተጠናቀረውን የተያያዘውን የመለስካቸው አምሃን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

ቤተክርስቲያን ደጅ ላይ ለልመና ላስቲክ አንጥፈው በሚያገኙት ትርፍራፊ ምግብ – ከጎዳና ወደ ትምሕርት ቤት

 ቤተክርስቲያን ደጅ ላይ ለልመና ላስቲክ አንጥፈው በሚያገኙት ትርፍራፊ ምግብ ለሚያሳድጓት ማየት የተሳናቸው ወላጆቿ በቶሎ ለመድረስ ጠንክራ ከምትማር የ10ኛ ክፍል የደረጃ ተማሪ ጀምሮ፤ ቤተሰቦቻቸውን ከነመፈጠራቸው የማያውቁ በልጅነት ጊዜያቸው ብዙ መከራን የገፉ ተማሪዎች ሕይወት በዚህ ዘገባ ውስጥ ተካቷል።

ከጎዳና ላይ የተሰባሰቡት ተማሪዎች

ከመናገሻዋ አዲስ አበባ በስተምስራቅ 515 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሐረር ከተማ ቀበሌ 10 እና 16 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ሁለት የተለያዩ የመኖሪያ ግቢዎች ይገኛሉ። ግቢዎቹ 25 ወንድና 15 ሴት ተማሪዎችን በአንድነት ይዟል። ተማሪዎቹ ከጎዳና ላይ የተሰበሰቡ ናቸው። አሰባሳቢው ደግሞ ከስምንት ዓመቱ ጀምሮ ብቸኝነትና የጎዳና ሕይወትን የቀመሰው የዛሬው መምሕር ተስፋ አለባቸው ነው። በሁለቱ መኖሪያ ግቢ ውስጥ ያሉት ተማሪዎች ሁሉም አሳዛኝ የልጅነት ታሪክ አላቸው። በሕፃንነት ዕድሜያቸው በድሕነትና በቤተሰብ እጦት መከራን የገፉ ለነገ ግን ብዙ ተስፋን የሰነቁ ናቸው። አንዳንዶቹ ደግሞ ተስፋ የመቁረጥ ስሜት የሚደመጥባቸውም ናቸው።

የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ለአንድ ዓመት/2008 ዓ.ም/ በዚህ ሁኔታ ጎዳና ላይ እየኖሩ ነው ትምሕርታቸውን የተከታተሉት

የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ለአንድ ዓመት/2008 ዓ.ም/ በዚህ ሁኔታ ጎዳና ላይ እየኖሩ ነው ትምሕርታቸውን የተከታተሉት

​የተማሪዎቹ የሕይወት ታሪክ የሚጀምረው ከድሕነትና ከቤተሰብ ማጣት ነው። አንዳንዶቹ በወላጆቻቸው የማሳደግ አቅም እጦት ምክንያት ለጎዳና ተዳርገው የነበሩ ናቸው። የአንዳንዶቹ ወላጆች ደግሞ ገና በልጅነት ዕድሜያቸው በሞት ተለይተዋቸዋል። የጥቂቶቹ እናቶች በሴተኛ አዳሪነት ንግድ ላይ የተሰማሩ በመሆናቸው ልጆቻቸውን ማሳደግ ሲያቅታቸው ወደ ጎዳና አውጥተዋቸዋል።አንዳንዶቹ ተማሪዎች እዛው ሐረር ከተማ የተወለዱ ናቸው። አንዳንዶቹ ደግሞ ከተለያየ ከተማ ነው ወደዛ የሄዱት። መብራቱ ታደሰ ከእነዚህ ተማሪዎች አንዱ ነው። በጉራጌ ዞን በቡታጅራ ከተማ የሚገኙ ቤተሰቦቹ በማሳደጊያ ማጣት ምክንያት ሐረር ለሚገኙ ዘመዶቻቸው ሰጡት።

መብራቱ ታደሰ 17 ዓመቱ ነው። 10ኛ ክፍል ጎበዝ ተማሪ ነው። ጎዳ

መብራቱ ታደሰ 17 ዓመቱ ነው። 10ኛ ክፍል ጎበዝ ተማሪ ነው። ጎዳ

“እንደ ልጆቻቸው ስለማያዩኝ እነሱን ጥዬ ወደ ጎዳና ወጣሁ” ይላል። መብራቱ ጎዳና ከወጣ ትምሕርቱን አላቋረጠም ቦቴ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ለሴተኛ አዳሪዎች ከሩቅ ቦታ ውሃ እየቀዳ ስለሚያመጣላቸው በሚሰጡት ገንዘብ እየታገዘ ትምሕርቱን ቀጠለ።

“በጎዳና ሕይወት ላይ ከፍተኛ ችግር ነበር። ምግብና ልብስ በጣም ቢቸግረንም እየተረዳዳን ኑሮን ገፍተነዋል” ይላል። እንደ መብራቱ ኹሉ ከሕፃንነት ጀምሮ እስከ አፍላው የወጣትነት ዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችም ነበሩ። ገና በስምንት ዓመት ዕድሜው የጎዳና ሕይወትን የቀመሰው ተስፋ አለባቸው እነዚህ ልጆች ለመርዳት ወስኖ ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት ወደእነሱ ሄደ።ተስፋ አለባቸው የ26 ዓመት ወጣት ነው። ተወልዶ ያደገው ሐረር ከተማ ነው። በልጅነት ዕድሜው አባቱን አያውቀውም። እናቱ ከእርሱ አባት ልጅ መውለዷ ስላልተወደደላት ከቤተሰቦቿ ተነጥላ ብቻዋን ነበር ያሳደገችው።

ተስፋ አለባቸው ይባላል። በልጅነቱ ነው እናቱን የተነጠቀው። ለሰዎች በመላላክ ውሃ እየቀዳና ቆሻሻ እየደፋ ትምህርቱን ተምሮ አሁን 40 የጎዳና ልጆችን በአንድ ላይ አሰባስቦ ያስተምራል።

ተስፋ አለባቸው ይባላል። በልጅነቱ ነው እናቱን የተነጠቀው። ለሰዎች በመላላክ ውሃ እየቀዳና ቆሻሻ እየደፋ ትምህርቱን ተምሮ አሁን 40 የጎዳና ልጆችን በአንድ ላይ አሰባስቦ ያስተምራል።

“ለሊት ላይ ወደ ጅቡቲ ለሚጓጓዙ ተሽከርካሪዎች መንገድ ላይ ቆማ ለውዝ ትሸጥ ነበር። በዚህ ምክንያት በመጣ ቅዝቃዜ ሦስት ወር ታማ ሕይወቷ አለፈ። ያን ግዜ እኔ የአራተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ።” የሚለው ተስፋ እናቱ የሞተችው እርሱ የስምንት ዓመት ልጅ እያለ ነበር። እናቱ ከሞተች በኋላ ማንም የሚያስጠጋው ዘመድ ስላለገኘ ቀደም ሲል ይኖሩበት በነበረው “አራተኛ” እየተባለ በሚጠራው ሰፈር መኖር ጀመረ።

የአካባቢው ነዋሪዎችና የገብርኤል ቤተክርስቲያን ሰንበት ትምሕርት ቤት ተማሪዎች እንዲሁም የሰፈር ጓደኖቹ ጭምር የሚሰጡትን ምግብ እየተመገበ እስከ ዐስራ ሦስት ዓመቱ ዘለቀ። ከዚህ ዕድሜ በኋላ ረዳት ማግኘት አስቸጋሪ ስለሆነበት ሥራ መሥራት እንደጀመረ ይናገራል። ምግብ ሳይበላ የሚውልበትና የሚያድርበት ቀን በርካታ እንደነበሩም ያስታውሳል።

“ጠዋት ትምሕርት ቤት ከመሄዴ በፊት ውሃ ቀድቼ እሄዳለሁ ስመለስ ደግሞ ቁሻሻ እደፋና ማታ መጥቼ አጠና ነበር።” የሚለው ተስፋ ከፍተኛ ጥረቶችን አድርጎ ዐስረኛ ክፍል ሲደርስ ወደ መምሕራን ማሰልጠኛ ገብቶ ትምሕርቱን ጨረሰ። በዚህ ሁሉ ጉዞ ውስጥ ዓላማ እንደነበረው ይናገራል።

“መጀመሪያ የምንኖረው ሥላሴ ቤተክርስቲያን ደጅ ነበር። ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ ምግብ ይሰጡናል። እሱን እየበላን እኔና ወንድሜ ትምሕርት ቤት እንማር ነበር።”

“እኔ ባለፍኩበት መንገድ ሌሎች ማለፍ የለባቸውም የሚል ዓላማ ስለነበረኝ ጠንክሬ መሥራትና። መጀመሪያ አንድ ልጅ ከዛም ጠንከር ብዬ ሁለት ልጅ መጨመር እፈልግ ነበር” ተስፋ ያሰበውን አደረገ። እዛው ሐረር ከተማ ውስጥ መጀመሪያ አንዲት ልጅ ማስተማር ጀመረ። ጠንክሮ ሠርቶ ከግለሰብ እስከ ድርጅት በሐረር ከተማ ያገኘውን ሁሉ አስተባብሮ ጎዳና ላይ የሚገኙ ተማሪዎችን መርዳት ጀመረ። ሲጀምረው አንድ ጊዜ ብቻ ለመርዳት ነበር ነገር ግን ጠጋ ብሎ የሁሉንም ታሪክ ሲያዳምጥ እዛው ባሉበት ሆነው ትምሕርታቸውን እንዲቀጥሉ ማድረግ ጀመረ።

መብራቱ ከእነዚህ ተማሪዎች አንዱ ነው። ቢማር ውጤት ሊያመጣ እንደሚችል የገባው ከተስፋ ጋር ከተገናኘ በኋላ እንደሆነ ይናገራል። ተስፋ ተማሪዎቹ መጀመሪያ እዛው ባሉበት ትምህርት እንዲጀምሩ ነበር ያደረገው። ምግባቸውን በተመለከተ ደግሞ በሐረር ከተማ የሚገኙ ሆቴል ቤቶችን አነጋግሮ የተራረፉ ምግቦች በየተራ እንዲሰጧቸው ጠየቀ። ፈቃደኛ ሆኑላቸው።

“የተወሰኑ ሆቴሎች ንፁህ ምግብ ፈቅደው ለአንዳንድ ተማሪዎች የሚሰጡ አሉ። እኛ ደግሞ ዱሮ ቡሌ ከምናመጣበት ቦታ ሄደን እናመጣለን። የከሰዓት ተማሪ የኾኑት ለጠዋቶቹ ተማሪዎች ምሳ አምጥተው ይጠብቋቸዋል። የጠዋቶቹ ደግሞ ለከሰዓቶቹ ያመጣሉ።”.

መብራቱ ምግቡን በተመለከተ በየተራ ተረዳድተው እያመጡ መማር መቀጠላቸውን ይናገራል። “የተወሰኑ ሆቴሎች ንፁህ ምግብ ፈቅደው ለአንዳንድ ተማሪዎች የሚሰጡ አሉ። እኛ ደግሞ ዱሮ ቡሌ ከምናመጣበት ቦታ ሄደን እናመጣለን። የከሰዓት ተማሪ የኾኑት ለጠዋቶቹ ተማሪዎች ምሳ አምጥተው ይጠብቋቸዋል። የጠዋቶቹ ደግሞ ለከሰዓቶቹ ያመጣሉ።” ተስፋ በወቅቱ ከጎዳና ላይ ለሰበሰባቸው 89 ተማሪዎች የራሱን የሕይወት ታሪክ ስለነገራቸው በሐሳቡ ተስማምተው ጎዳና ላይ ዩኒፎርማቸውን እየለበሱ ደብተራቸውን አንጠልጥለው ወደ ትምህርት ቤት ሄዱ። ተስፋ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ሲናገር “መጀመሪያ 89 ልጆችን ሰብስቤ ከሆቴል የተራረፈ ምግብ ተራ በተራ እያመጡ እሱን እየተመገቡ እንዲማሩ አደረኩ። ከእነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ በተለያየ ምክንያት ትምሕርታቸውን አቋረጡ። አንዳንዶቹ በሴተኛ አዳሪነት ላይ የተሰማሩ ስለነበሩ በደረሰባቸው ከፍተኛ ችግር ምክንያት ትምሕርታቸውን መቀጠል አልቻሉም”

አርባዎቹ 25 ወንድና 15 ሴት ተማሪዎች ግን ጠንካራ ኾኑ። በዚህ ውስጥ ዕድሜያቸው ከስድስት እስከ 17 ዓመት የሆኑ ልጆች ይገኛሉ። ከክፍሏ አንደኛ ከአጠቃላይ ትምሕርት ቤቱ ሁለተኛ የወጣች የ11ኛ ክፍል ተማሪን ጨመሮ በትምሕርታቸው ጠንካራ የሆኑ ተማሪዎች አሉ።

እነዚህን ተማሪዎች ቆይታ የተቀላቀለችው የትነበርሽ አያሌው 16 ዓመቷ ነው። በሐረር ከተማ ነው ተወልዳ ያደገችው። የየትነበርሽ የልጅነት ታሪክ ለአንድ ልጅ ዕድገት የሚያስፈልገው በጣም ጥቂት ነገር እንኳን የተሟላበት አልነበረም። እናትና አባቷ ማየት የተሳናቸው ናቸው። ሁለቱም ሥላሴ በተባለ ቤተክርስቲያን ደጅ ላይ የላስቲክ ሸራ ወጥረው በልመና የሚያገኙትን ምግብ እየመገቡ ነው እሷንና ወንድሟን ያሳደጓቸው።

የትነበርሽ አያሌው 16 ዓመቷ ነው። እናቷም አባቷም ማየት የተሳናቸው ናቸው። ቤተክርስቲታ ደጅ ተቀምጠው እየለመኑ በሚያመጡት ምግብ ነው ያስተማሯት። ትምሕርት ቤት ከገባች ጀምሮ የ10ኛ ክፍል እስከደረሰች ድረስ የደረጃ ተማሪ ነች

የትነበርሽ አያሌው 16 ዓመቷ ነው። እናቷም አባቷም ማየት የተሳናቸው ናቸው። ቤተክርስቲታ ደጅ ተቀምጠው እየለመኑ በሚያመጡት ምግብ ነው ያስተማሯት። ትምሕርት ቤት ከገባች ጀምሮ የ10ኛ ክፍል እስከደረሰች ድረስ የደረጃ ተማሪ ነች

የትነበርሽ ስለ ዕድገቷ ስትናገር፤ “መጀመሪያ የምንኖረው ሥላሴ ቤተክርስቲያን ደጅ ነበር። ሰዎች ወደ ቤተክርስቲያን ሲመጡ ምግብ ይሰጡናል። እሱን እየበላን እኔና ወንድሜ ትምሕርት ቤት እንማር ነበር።” ጥረቷን የተመለከቱ በሐረር ከተማ ቀበሌ 08 ውስጥ “የድሆች ሰፈር” በሚባል ቦታ በትንንሹ የተከፋፈለ መጠለያ ቤት ተሰጠቷቸው ገቡ። “አባቴ ማየት ባይችልም በራሱ መሄድ ግን ይችላል። እናቴን የምመራት ግን እኔ ነበርኩ። ጠዋት እሷን ቤተክርስቲያን አድርሼ ወደ ቤት ተመልሼ እመጣና ልብሴን ቀይሬ ወደ ትምሕርት ቤት እሄዳለሁ። ትምሕርት ቤቱ ግን ራቅ ስለሚል እዛው እውላለሁ እናቴን ጎረቤቶች ያመጡልኛል።” ትላለች።

ትምሕርት ቤቱ ዩኒፎርም ስላለው ልብስና የመሳሰሉት ነገሮች አያስጨንቁኝም የምትለው የትነበርሽ በዚህ ሁኔታ እስከ ዘጠነኛ ክፍል ተማረች። በትምሕርት ቤት ውስጥ ደግሞ ጎበዝና የደረጃ ተማሪ ናት። ይህን የተመለከቱ ሰዎች ተስፋ ጋር አስገብተዋት አሁን እዛ ሆና የ10ኛ ክፍል ትምሕርቷን በመከታተል ላይ ትገኛለች። ስታድግ መሆን የምትፈልገው የሕክምና ባለሞያ ነው። የትነበርሽን ደጋግሜ ምን ቢሟላላት እንደምትፈልግ ጠየኳት መልሷ “ምንም አሁን ሁሉ ነገር ተሟልቶልኛል ነው።”

እሷን የሚያሳስባት ከጀመረችው ትምሕርቷ ሳትፈናቀል በቶሎ ለቤተሰቦቿ መድረስ ነው። የትነበርሽ ስድስተኛ ክፍል የሚማረው ታናሽ ወንድሟ ጠንክሮ እንዲያጠና የምትመክረውም ለዚህ እንደሆነ ነግራኛለች።

መንፈሳቸው ጠናካራ የሆኑ ተማሪዎች እንዳሉት ሁሉ ያለፉበትን መንገድ መናገር የሚከብዳቸው ልባቸው በሐዘን የተሰበሩ ተማሪዎች አሉ። ገሊላ ሰለሞን ከእነዚህ አንዷ ነች። ገሊላ አሁን የኮሌጅ ተማሪ ናት። የምትኖረው ሌላ ቦታ ነው ግን በተስፋ አማካኝነት ጥቂት የትራንስፖርት ርዳታ ታገኛለች። ተስፋ እንደነገረኝ ግቢ ውስጥ አስገብቶ ማስተማር የማይችለውን በውጭ ይረዳቸዋል። ሐረር የሚገኘው የሬፍት ቫሊ ኮሌጅ የነፃ የትምህርት ዕድል ሰጥቷት እየተማረች ነው።

ገሊላ ሰለሞን እናትና አባቷን በልጅነቷ ነው የተነጠቀችው አሁን የአንደኛ ዓመት የኮሌጅ ተማሪ ናት።

ገሊላ ሰለሞን እናትና አባቷን በልጅነቷ ነው የተነጠቀችው አሁን የአንደኛ ዓመት የኮሌጅ ተማሪ ናት።

“እናትና አባቴ በልጅነታችን ነው የሞቱት። እኔና ወንድሜ በየቦታው ተንከራተን ነው ያደግነው። እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ በየሰው ቤት እየተንከራተትኩ ነው ያደኩት። ለሦስት ቀን ሳልበላ ትምሕርት ቤት የምሔድበት ቀን ነበር….” ገሊላ ስሜቷን አምቃ መናገር ያቅታታል።

“ቀኑን ሙሉ ነው የምንማረው ምግብ ስለማላገኝ ምሳ ሰዓት ሲደርስ ጓሮ እቀመጥና ወይም ደግሞ ላይብረሪ እገባና ውዬ እመጣለሁ። ስጨርስ እቤት ገብቼ ምግብ ካገኘሁ እበላለሁ ካጣሁ ደግሞ እተኛለሁ።” ገሊላ ትምሕርቷን የመጨረስ ጠንካራ ፍላጎት እንዳላት ደጋግማ ብትናገርም መከራዋ ጭንቀትን እንደፈጠረባት መሸሸግ ግን ትቸገራለች። በዚህ ላይ የነፃ ትምህርት ዕድሉን የሰጧት ኃላፊ በመቀየራቸው ዕድሏ በእንጥልጥል ላይ ነው። ተስፋ ልጆቹን ለማገዝ የወሰነው ከራሱ ታሪክ በተጨማሪ እንደ ገሊላ ያሉ በችግር እየተፈተኑ ለመማር የሚታትሩ ልጆችን ሲያይ ነው።

ግዮን ሽባባው በዚህ ግቢ ውስጥ የሚገኝ ሌላው ጎበዝ ተማሪ እንደሆነ ተነግሮናል። 17 ዓመቱ ነው 8ኛ ክፍል ነው።

ግዮን ሽባባው በዚህ ግቢ ውስጥ የሚገኝ ሌላው ጎበዝ ተማሪ እንደሆነ ተነግሮናል። 17 ዓመቱ ነው 8ኛ ክፍል ነው።

ግዮን ሽባባው በዚህ ግቢ ውስጥ የሚገኝ ሌላው ጎበዝ ተማሪ እንደሆነ ተነግሮናል። 17 ዓመቱ ነው 8ኛ ክፍል ነው። የተወለደው ቢሾፍቱ ከተማ ነው። እናቱ በልጅነቱ ነው የሞተችው። አባቱ ድሬደዋ ይገኛል ስለተባለ ወደዚያው አቀና። አልተሳካለትም። ወደ ሐረር ከተማ አቅንቶ ለጎዳና ሕይወት ተዳረገ።

“ግን እግዚያብሔር ይመስገን ጥሩ ጥሩ ሰዎች ያጋጥሙኛል። ትምህርት መማር አስጠልቶኝ ነበር ገፋፍተው ትምሕርት ቤት አስገቡኝ መጀመሪያ በትምሕርቴ ጠንካራ አልነበርኩም በኋላ ግን እየጠነከርኩ መጣሁ” ይላል አሁን በትምህርት ቤቱ የደረጃ ተማሪ ነው። በከተማው የሚገኙ የተለያዩ ሆቴሎች ተከፋፍለው ምግብ ይሰጧቸዋል። “ጠዋት ቁርሳችንን ዳቦ እንበላለን ምሳና እራታችንን ደግሞ ተራ በተራ ከየተመደብንበት ሆቴል እያመጣን እንበላለን።” የሚለው ግዮን ወደፊት ፖለቲካ ውስጥ ተሳትፎ አሻራውን ማስቀመጥ ወይም ደግሞ ታሪክ ማጥናት ያስደስተዋል።

ተማሪዎቹ ካለመብላት ወደ መብላት ከጎዳና ወደ መኖሪያ ቤት ስለገቡ ድምፃቸው ላይ የጥንካሬ መንፈስ ይሰማል። ተስፋ እንደሚለው ሁሉም ተማሪዎች ከትምሕርታቸው ጎን ለጎን የራሳቸው ተሰጦ አላቸው። መብራቱ ከእነዚህ አንዱ ነው። አሁን 10ኛ ክፍል ነው ከክፍሉ ሰባተኛ እንደሚወጣ ነግሮኛል። ኳስ መጫወት በጣም ስለሚወድ ከትምሕርቱ ጎን ለጎን በሐረር ከተማ በሚገኝ የእግር ኳስ ቡድን ውስጥ ገብቶ ኳስ ይጫወታል። ለዚህ ደግሞ ትልቁ ችግሩ ትጥቅ መሆኑን ይናገራል።

ተስፋ አለባቸው ከሚያስተምራቸው ልጆች ጋር

ተስፋ አለባቸው ከሚያስተምራቸው ልጆች ጋር

ተስፋ ለሁለቱ ግቢዎች በወር ዘጠኝ ሺሕ ብር ይከፍላሉ። ይህን ገንዘብ ከብዙ ሰዎች አሰባስበው እንደሚከፍሉ ነው የነገረን። ልጆቹን ለማሳደግ የማያንኳኳው በር የለም። የእነዚህን ተማሪዎች ትምሕርት ለማስጨረስ የቻለውን ያደርጋል። እቅድ እያወጣ ከምግብ እስከ ፅዳት አገልግሎት ርዳታ ይጠይቃል። ግቢ ውስጥ ያሉትን ተማሪዎች የሚያዩ የጎዳና ላይ ልጆች ደግሞ “እኛንስ መቼ ነው የምታስገባን?” በሚል ጥያቄ ወጥረው ይይዙታል። “በተለይ ዝናብ ሲጥል እዚህ አካባቢ መተው ቁጭ ሲሉ ሳይ መፈጠሬን እጠላለሁ” ይላል።

በዚህ ላይ አሁን መሰረት የያዙት ልጆቹ በተለያየ ምክኒያት እንዳይደናቀፉ ሁሌም ደግሞ ከተረጂነት ወጥተው ሠርተው መማር እንዲችሉ ልብስ ማጠቢያ ማሽን እና እንጀራ መጋገሪያ ቢያገኝ ተረዳድተው እንዲኖሩ ማድረግ እንደሚችል ይናገራል። በተጨማሪ ደግሞ የሚያጠኑበት መጽሐፍት እንዲሁም የግል ንፅህና መጠበቂያ ቁሶች ቢያገኙ ብዙ ነገሮች እንደሚያቃልልላቸው ይናገራል።

የእርሱ የዘወትር ጭንቀት እንዲህ ያሰባሰባቸው ጎበዝ ተማሪዎች ያሰቡበት ሳይደርሱ በአጭር እንዳይቀሩ ነው። “ባለንበት ከተማ ሁሉም የራሱን ኑሮ ለማሸነፍ የሚታገልበት ቢሆንም የቻልነውን ሁሉ ጥረት አድርገን ልጆቹን ትምሕርት ለማስጨረስ ከፍተኛ ጥረት አደርጋለሁ” ብሏል።

ተስፋና ተማሪዎቹ “እስካሁን እዚህ የደረስነው በእነርሱ ድጋፍ ነው “ በማለት ደጋግመው የሐረር ከተማን ሕዝብ ያመሰግናሉ።

በሰዓሊተ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በተደረገው የፕሮቴስታንቶች ርኵሰትተጠያቂ መኾን ያለባቸው ፓትርያርኩ ናቸው፡፡

የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጁ አጥማቂ ፍለጋ ከአባቶቻቸው ይልቅ ወደ ፕሮቴስታንቶች ማዘንበላቸውን በራሳቸው አንደበት ተናገሩ፡፡ በሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንደተከናወነ የተነገረው ቅብዓት አይሉት ጥምቀት በእርሳቸው ብቻ ሳይኾን በፓትርያርኩ ቡራኬ ሰጪነት የተከናወነ መኾኑ አነጋጋሪ ነው፡፡

እኛ እነርሱን ስናጠምቅም ይሁን ስንቀባ ብንገኝ ደግ በኾነ፤ አንድ ፓስተር ብድግ ብሎ አንድን በቁምስና ማዕርግ ያለ የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛው አስተዳደር ውስጥ ተዋናይ የኾነን ሰው ሲቀባም ይሁን ሲያጠምቅ ማየት ከየት እንደመጣ እስካሁን ማንም አልነገረንም፡፡ ለጊዜው የነገሩ ሙሻዙር ወደ ም/ሥ/ አስኪያጁ ያጠንጥን እንጂ ዋናው ተጠያቂ መኾን ያለባቸው ፓትርያርኩ ናቸው፡፡ ሰውየው አድርግ የተባሉትን አድርገው ይኾናል፡፡ ይህም መለካዊነታቸውን ከሚያሳብቅባቸው በቀር ከተጠያቂነት ነፃ ያደርጋቸዋል ማለት አይደለም፡፡

እንኳን በማዕርገ ቁምስና በምእመን ደረጃም እንዲህ ያለ የሚፈጽም በሌለባት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይህን የኃፍረት ካባ ሊያከናንቡን መቁረጣቸው ብርቱ ጽዩፍ አድራጎት ነው፡፡ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ለማን እንዴት መቼ እንደሚፈጸም በጉልህ የምታስተምርን ቤተ ክርስቲያን በቅጽሯ ውስጥ ነውረኛ ሥራ በማድረግ መሠማራት አደጋው ቀላል አይደለም፡፡ “የጥፋት ርኵሰት በማይገባው ስፍራ ቆሞ ብታዩ፥ አንባቢው ያስተውል” ያለውን ልብ እንበል፡፡ ማር ፲፫፥፲፬።

ለመኾኑ እርሳቸው አሉ እንደሚባለው ጉዳዩ የተከናወነው በውኃ ነው ከተባለ፤ ጥምቀቱ ለልጅነት ነው ወይስ ለፈውስ? ቤተ ክርስቲያን የሰጠቻቸውን ልጅነት የት ጥለውት ይኾን? አሞኝ ነው ካሉ ደግሞ ጠበል ቤት እንጂ ኪታ ለባሽ ፓስተር ይዞ ወደ መቅደስ መግባትን ምን አመጣው? ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን በየትኛው አንቀጽ እንደሚወድቅም ሊነግሩን ይገባል፡፡ ኢኩሚኒካል ግንኙነትን ስለማጠናከር ነው ከተባለም በምሥጢር ተካፋይነት የሚፈጸም አይደለም፡፡

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንኳን ለመናፍቅ ትምህርተ ክርስትናን በመከታተል ላይ ያሉ ባለ ተስፋዎችን በቅዳሴ ጊዜ ምሥጢር ለመካፈል የበቁ አይደሉምና (ማለትም አልደረሱምና) ፃዑ ብላ ታሰናብታለች፡፡ እኒህን ጳጳስ አደርጋለሁ ብሎ . . . መነሣት ነገ ደግሞ ማንን አምጥተው በማን እንዲቀቡ ይኾን? ከአባቱ ውጭ ሌላ አባት መፈለግ . . .

በሰውየው ላይ ብዙ ችግር እንዳለ እየታወቀ ብዙ ጊዜ በዝምታ ታለፉ፡፡ አሁን ብለው ብለው በአደባባይ ቤተ ክርስቲያንን የማይመጥኑ መኾናቸውን በይፋ አጋለጡ፡፡ የሰውን ዲዘርቴሽን ግትም አድርገው ገልብጠው ፒኤች ዲ አለኝ ሲሉ ኖሩ፡፡ ዝም ተባሉ፡፡ በሆለታ ገብርኤል አካባቢ ያለባቸውን ብዙ ነውረኛ ሥራ ሲሠሩ ኖሩ ዝም ተባሉ፡፡ አሁን ደግሞ ሌላ . . .

በቅርቡ ቅዳሴ ረዘመ ብለው በሸገር ሬድዮ ሲነዛነዙ የነበሩት ፓትርያርክ አሁን ደግሞ እንዲህ ባለ ተግባር ላይ መሰለፋቸው ሒደቱን በጥሞና የሚያየው አካል ይፈልጋል፡፡ የእናት ቤተ ክርስቲያን ጉዳይ እንዲህ በዋዛ በዋዛ እየታለፈ መቀጠል የለበትም፡፡ የሃይማኖት ጉዳይ ቀስ በቀስ እንዲሸረሸር ብርቱ ጥረት የሚደረግ ይመስላል፡፡ በሰዓሊተ ምሕረት በተደረገው ይህ ኩነትም እንደ ደኅና ነገር ጳጳስ አስከትለው የደብር አለቆችን ጠርተው ታዳሚ ኾኖ መገኘት ምን ይሉታል? ቅዳሴው እንዲያጥር የሚከራከሩት ሰው ቀድሞም ቢኾን ምክሩን ያገኙት ከአንድ የፕሮቴስታንት ፓስተር እንደነበር ነግረውን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ፓስተሮቹን ወደ ቤተ መቅደስ ይዘዋቸው ገቡ፡፡

በአሁኑ የግንቦቱ (፳፻፱) ሲኖዶስ ጉባኤ መካከል አንዱ ተነሥተው “መሠረት ስብሐት ለአብ መናፍቅ አይደለም” ብለው ድምፅ አሰምተዋል መባሉ ሌላው አነጋጋሪ ጉዳይ ነው፡፡ አለማወቅ እንዲህ ካለ ድፍረት ያደርሳል፡፡ ክርስቶስ አማላጅ ነው ብሎ የቅዱሳንን ሥራ ለእግዚአብሔር ሰጥቶ የተናገረን ሰው መናፍቅ አይደለም ብሎ መከራከር ምን ይሉት ጥብቅና ነው፡፡ ሰውየው ሔደው የሙጥኝ ብለው የተጣበቁበት ድርጅት ምን ብሎ የሚያስተምር እንደኾነ በገሃድ እየታወቀ ለክርክር መሰናዳት ምን ይባላል?

የኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያንን አቋም የሚሸራርፉትን በጥብቅ የሚቃወሙት አቡነ ቄርሎስ የሰጡት ምላሽ አንጀት አርስ ነው፡፡ የሚቅበዘበዝ ሀሳብ የሚያመጡትን እዚያው መገሠፁ የተገባ ለመድረኩ የሚመጥን ነውና፡፡ ግን እንዲሁ በቀላሉ መታየት አለበት ተብሎ መወሰድ የለበትም፡፡ ያንን ቃል የተናገሩት ጳጳስ ናቸውና በሀገረ ስብከታቸውም ብዙ ሃይማኖታዊ ውዝግብ እየፈጠሩ የሚገኙ ናቸውና ጉዳያቸው ለብቻ መታየት ይገባዋል፡፡ እኒህን ጳጳስ ሰውየው ራሱ ቢሰማቸው እንዴት በሳቀባቸው፡፡ ጥብቅናውን አይፈልገውም፡፡ ይብላኝ ለእርሳቸው እንጂ በአደባባይ ማንነቱን ደጋግሞ የተናገረ “ምስጉን” መናፍቅ ነው፡፡ ታዲያ ለሞተ ሰው ጥብቅና መቆሙን ምን አመጣው? ነገር ዝም ብሎ አይመዘዝምና ደጋግሞ ማጤኑ ይበጃል፡፡

እነዚህ ሦስት ጉዳዮች በለበጣ የሚታዩ አይደሉም፡፡ ይታሰብባቸው!

Image may contain: 1 person, indoor

ታላቅ አውሮፖ አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ በስዊዘርላድ ጄኔቫ የተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት ፊት ለፊት

ታላቅ አውሮፓ አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ የወያኔ ተወካይ የሆነው ቴውድሮስ አድሀኖም ለ WHO መሪነት የሚያደርገውን ምርጫ በመቃወም ታላቅ: ሰላማዊ ሰልፍ በስዊዘርላንድ ጄኔቫ May 22 ይህን የገዳይ ተወካይ ህዝቡን በቆሻሻ ክምር እሚገድል የአለም: የጤና ድርጅት ተወካይ ሊሆን አይችልም በማለት ድምፃችንን ከፍ አድርገን ለአለም እናሰማለን የአገራችንን ወቅታዊ ሁኔታ Photo በፁፍ፣ መፈክር እናሰማለን፣ TPLF በመቃወም እንጮሀለን የህዝባችንን ስቃይ ሞት ለአለም ሚድያ እናሳያለን። ኑና በጋራ ድምፃችንን እናሰማ ወያኔን በአንድ ነታችን የህዝብ ልጅ መሆናችንን እናሳየው። ሞት ለገዳይ በእለቱ የአለም ሚድያዎች በቦታው ይገኛሉ በጋራ በመሆን ቴውድሮስ ለቦታው ማይመጥን ገዳይ ህዘብን ሚያሰቃይ አረመኔ ነብሰ በላ መሆኑን እንናገር እናስቁመው። ቀን May 22 ከ 13 ሰአት ጀምሮ አድራሻ ጄኔቫ UN ቢሮ ፊት ለፊት አዘጋጅ የኢትዮጲያ ሰብአዊ መብት እና ዴሞክራሲ ታስክ ፎርስ በ ስዊዘርላንድ።

Image may contain: 1 person, text

በመካከለኛው ምሥራቅና በአፍሪካ ከአራት ሕፃናት አንዱ በድኅነት ውስጥ ይኖራል – ዩኒሴፍ


ፎቶ ፋይል

የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ ከትናንት በስቲያ ባወጣው አዲስ ሪፖርት በመካከለኛው ምሥራቅና በሰሜን አፍሪካ ሀገሮች ከአራት ልጆች አንዱ እንደ ንፁህ ውሃና ተገቢ መጠለያ የመሳሰሉ እጅግ መሠረታዊ የሆኑ አቅርቦቶችን አጥተው በድኅነት እንደሚኖሩ አመለከተ።

የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት ዩኒሴፍ ከትናንት በስቲያ ባወጣው አዲስ ሪፖርት በመካከለኛው ምሥራቅና በሰሜን አፍሪካ ሀገሮች ከአራት ልጆች አንዱ እንደ ንፁህ ውሃና ተገቢ መጠለያ የመሳሰሉ እጅግ መሠረታዊ የሆኑ አቅርቦቶችን አጥተው በድኅነት እንደሚኖሩ አመለከተ።

አሥራ አንድ የአረብ ሃገሮችና አካቶ የተካሄደው ጥናት ሃያ ዘጠኝ ሚሊዮን ሕፃናት ሁለት ወይም ከሁለት በላይ በቂ የተመጣጠነ ምግብ፣ መሠረታዊ ትምህርት፣ የንፅህናና የመረጃ አቅርቦት የመሣሳሉ ለሕይወት እጅግ መሠረታዊ ፍላጎቶች በማያገኙበት የድኅነት አረንቋ ይኖራሉ ብሉዋል።

የወጣቶች ደኅነት ዓይነተኛ ምክንያት የትምህርት ዕጥረት መሆኑን ስለአካባቢዎቹ የልጆች ደኅነት የተጠናቀረ የመጀመሪያ የሆነው ይህ መረጃ አመልክቷል።

የትምህርት ዕድል ባላገኙ የቤተሰብ አባላት የሚመሩ ቤተሰቦች ውስጥ የሚኖሩ ልጆች በድኅነት የመኖር ዕድላቸው ዕጥፍ መሆኑን ያመለክታል። በዚህ ዓይነት ከሚኖሩ ዕድሜአቸው ከአምስት እስከ አስራ ሰባት ዓመት ከሆኑ ልጆች ውስጥ አንድ አራተኛው ትምህርት ቤት ያልገቡ ወይም ከዕኩዮቻቸው በሁለት ክፍል ወደኋላ የቀሩ ናቸው ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የመካከለኛ ምሥራቅ እና የሰሜን አፍሪካ አካባቢ ድሬክተር ገርት ካፔሌሬ ሲናገሩ የልጆች ድኅነት አመዛኙ ምክንያት የቤተሰብ ገቢ ማነስ ሳይሆን ጥራት ያለው ትምህርት የጤና ጥበቃ መኖሪያና ንፁህ ውሃ ዕጦቱ ነው ብለዋል።

አርበኞች የተጠና ስልታዊ ጥቃት ፈፀመ ፡፡

በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ(ሰሜን ጎንደር ) ጠረፋማው ከተማ ነጋዴ ባህር አካባቢ ከሱዳን ነዳጅ ጭነው ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዙ የነበሩ ሁለት የህወሀት ወያኔ ንብረት የሆኑ ቦቲዎች እስከተሳቢው፤ እስከጫኑት ነዳጅ ሙሉ በሙሉ በአርበኞች መብረቃዊ ጥቃት ዶግ አመድ ሆኑ፡፡ የወያኔ ሰራዊት ከቦታ ቦታ ለመንቀሳቀሻ የሚውል መሆኑ ቀድሞ መረጃ የጀረሳቸው የነፃነት ጎዶች፤ ደፍጠው በመጣባበግ የልባቸውን አድርገዋል፡፡

ለጥቃቱ ድርጅታችን አርበኞች ግንቦት ሰባት ለፍትህ ለአንድነት እና ለነጻነት ለዲሞክራሲ ኃላፊነቱን ወስዷል፡፡ የተለመደውን ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ በአካባቢው የሚገኙ የወያኔ ሰራዊት አባላት ከካምፓቸው ተነስተው የሚያደርጉትን ጠፍቷቸው ጥምብ እንዳየ አሞራ በየቦታው ሰራወጡ ነበር፡፡

የነፃነት ኃይሎች በሚያደርጉት የተጠና ተደጋጋሚ ጥቃት በመተማ በኩል የሚቀርበውን ነዳቸጅ ማስተጓጎል መቻሉ ይታወሳል፡፡ በዚህም ምክነያት በሀገር ውስጥ የነዳጅ እጥረት መኖሩ ይታወቃል ነገር ግን ይህ ነዳጁ የተጫነው ለህዝብ አገልግሎት ሳይሆን ለወያኔ ቅጥረኞች ነው፡፡

ይህ ጥቃት የወያኔዎችን የነዳጅ ምንጭ ለማድረቅ የሚደረገው ሳልታዊ የወታደራዊ የዘመቻ አካል ነው፡፡

በተያያዘ ዜና አርበኞች ግንቦት 7/2009 ዓ/ም ለሊት 8፡55 ሲሆን በደቡብ ጎንደር ዞን ሊቦከምከም ወረዳ በጣራገዳም መሽጎ በነበረ የህወሃት መከላከያ ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈፀሙ።

ዘላለማዊ ክብር ለነፃነት ለተሰው አርበኞቻችን!!

በማኅበራዊ ሚዲያ ለተሠራጨባቸው በጴንጤ የ”መቀባባት” አቤቱታን አባ ኃይለ ማርያም መለሰ(ዶ/ር)አስተባበሉ

Image may contain: 4 people, text

ከ16ቱ ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት አንዱ ኾነው በዕጣ የተመረጡት የጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ፣ አባ ኃይለ ማርያም መለሰ(ዶ/ር)፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ለተሠራጨባቸውና ምልአተ ጉባኤው እንዲጣራ ባዘዘው የ”መቀባባት” አቤቱታ፤ ዛሬ፣ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቴሌቭዥን(EOTC-Tv) ማስተባበያ መስጠታቸው ተሰማ፡፡

በቃለ ምልልስ መልክ በተሰጠው ማስተባበያቸው፦ የካቲት 22 ቀን 2009 ዓ.ም.፣ በደብረ ምጥማቅ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የተከናወነው፣ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት “የጸሎት ሥነ ሥርዓት” በጋራ ጉዳዮች ላይ ያተኮረና በግልጽ የተካሔደ እንጅ የቡራኬ እንዳልነበረ፤ እርሳቸውም ቤተ ክርስቲያኒቱን ወክለው እንዲያስተባብሩ በታዘዙት መሠረት መርሐ ግብሩን መምራታቸውን፤ ውኃና እምነት ተበጥብጦ እንደቀረበና እርሱን በጣታቸው ጠቅሰው በትእምርተ መስቀል መቀባታቸውንና እርሳቸው ግን በፍጹም እንዳልተቀቡ፤ ቅብዓ ቅዱስ እና ሜሮን እንዳልነበረ፤ ለተሿሚነትም የተመረጡት በፈቃደ እግዚአብሔር እንደኾነ፤ ማስረጃው በወቅቱ ቢቀርብ ማብራሪያ ሊሰጡበት ይችሉ እንደነበርና የኤጲስ ቆጶስ ምርጫና ሢመት ወቅት ተጠብቆ መሠራጨቱ ተገቢ እንዳልኾነ በመጥቀስ ቅሬታቸውን መግለጻቸው ተመልክቷል፡፡