አዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር ኦባንግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን ተናገሩ

 

 

nሳዑዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውንና እየደረሰ ያለውን ፈር የለቀቀ አስነዋሪ ግፍ ዓለምአቀፍ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ከሰብዓዊ መብት ተሟጋች እና ሌሎች ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ጋር እየሠሩ መሆናቸውን አቶ ኦባንግ ሜቶ በተለይ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ተናገሩ፡፡ የሳዑዲ ልዑል ሰብዓዊነት የረገፈበትንና በግፍ የተሞላ የወሮበላ ተግባር የሚፈጸምበትን አሰቃቂ ተግባር የሚከናውኑትን አንጋቾች አሞካሹ፡፡

ያለ አንዳች ልዩነት ኢትዮጵያውያን በኅብረት ድምጻቸውን በማሰማት እየተቃወሙት ያለውን ኢሰብዓዊ ተግባር አስመልክቶ በተለያዩ መንገዶች ይፋ ከሆኑት በተጨማሪ ድብቅ መረጃዎች እየተሰበሰቡ መሆናቸውን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ኦባንግ ሜቶ የጋራ ንቅናቄው ከዓለምአቀፍ የመብት ተቋማት ጋር በቅርበት እየተሰራ ስላለው ዝርዝር ጉዳይ ግን ከሁኔታው ምስጢራዊነት አኳያ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበዋል፡፡

“አልዘገዩም” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም “አኢጋን ችግር በተከሰተ ቁጥር የሚቋቋምና የሚፈርስ የዕቁብ ይዘት ያለው ድርጅት አይደለም፡፡ ወይም እሣት ሲነሳ ድምጽ እያሰማ እንደሚከንፍ የእሣት አደጋ መኪና የሚመሰል ድርጅት አይደለም” በማለት የጋራ ንቅናቄውን የተጠና አካሄድ በመጠቆም የመለሱት አቶ ኦባንግ ይህ ችግር እንደሚከሰት አስቀድሞ ማስጠንቀቂያ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡

ችግሩ አስቀድሞ እንደሚከሰት ቢታወቅም ምላሽ የሚሰጥ ብቃት ያለው አካል ባለመኖሩ አንገት የሚያስደፋና ኃፍረት የሚላብስ፤ “አገር አለኝ ወይ?” የሚል ጥያቄ የሚያስነሳ በኢትዮጵያ ታሪክ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቅ ኃፍረት ሊደርስብን ችሏል፡፡ “ይሁን እንጂ” አሉ ኦባንግ “ይህ መራር ዜና ከተሰማበት ሰዓት ጀምሮ የጋራ ንቅናቄው የበኩሉን” ሲያደርግ መቆየቱን አመልክተዋል፡፡

“ከተለያዩ ዓለምአቀፋዊ ተቋማት፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች፣ አግባብ ካላቸው መንግሥታዊ አካላትና በተለያየ ደረጃ ላይ ከሚገኙ የሳዑዲ ባለስልጣናት ጋር ተነጋግረናል” በማለት አቶ ኦባንግ ተናግረዋል፡፡ ለዓብነት ያህልም የሳዑዲ ም/ጠ/ሚ/ር እና የመከላከያ ሚ/ር፣ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚ/ር፣ የፍትሕ ሚ/ር እና ሌሎች ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን የመንግሥት መ/ቤቶችን ጨምሮ በአውሮጳና በሰሜን አሜሪካ የሚገኙትን የሳዑዲ ኤምባሲዎችን እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽነርን፣ የአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ACHPR)፣ ወዘተ ማነጋገራቸውንና በየደረጃውም ምላሽ ማግኘታቸውን አመልክተዋል፡፡

በመላው የመካከለኛው ምስራቅ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ዕረፍት የሚሰጥ እንዳልሆነ የጠቆሙት “ጥቁሩ ሰው” ሳዑዲ ካላትና ከምትከተለው “የበርህን ዝጋ ፖሊሲ” አንጻር በአካል በቦታው ላይ ከመገኘት ይልቅ አቅም ካላቸው ዓለምአቀፋዊ አካላት ጋር በአፋጣኝና በቅርበት መሥራቱ ድርጅታቸው የወሰደው አማራጭ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ የሎጂስቲክሱ ጉዳይ መስመር ሲይዝም የጋራ ንቅናቄው ከዚህ በፊት በየአገራቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ ሲያስፈጽምበት የነበረውንና በውጤታማነቱ የሚታወቀውን አማራጭእንደሚተገብር ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ኢህአዴግ አገርን እንደሚያስተዳድር ድርጅት በዜጎቹ ላይ እየደረሰ ያለውን አስነዋሪ ተግባር ትኩረት ሰጥቶ አለመመከቱ ተቃውሞ አስነስቷል፡፡ ይህንኑ አስመልክቶ አቶ ኦባንግ ሜቶ “ወገኖቻችንን ድንበር በማሻገርና ኤጀንሲ ከፍተው ወደ አረብ አገራት ሲልኩ የነበሩት ሁሉ ሕግ ፊት ቀርበው ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ የተለያዩ ተግባራት” እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ሼክ መሐመድ አላሙዲ የሠራተኛ ኃይል ወደ ሳዑዲ እንዲላክ ከኢህአዴግ ጋር በይፋ ስምምነት ማድረጋቸው የሚታወስ ነው፡፡ ኢንቨስትመንትን በተመለከተ ከሚፈልጉበት ክልል መሬት ለመውሰድ፣ ከሚፈልጉበት ባንክ ኮሪደር ገንዘብ ለመበደር ገደብ የሌላቸውና በሞቀበት ሁሉ ባለመጥፋት በጀት መድበው በሚያስተዳድሯቸው ሚዲያዎች እንዲሁም አንደበታቸውን በሙስና ላሰሯቸው ባለሥልጣናት “ኢትዮጵያዊ ነኝ” እያሉ በተገኙበት ቦታ ሁሉ ለሚዲያ ፍጆታ የሚደሰኩሩትና ግጥም የሚያስደረድሩት ሼክ መሐመድ አላሙዲ፣ “ወገኔ” የሚሉት ሕዝብ በአባታቸው አገር ወሮበሎች ሲያልቅና ሲጨፈጨፍ ዝም ማለታቸው ኢንቨስትመንቶቻቸውን ጥያቄ ውስጥ ከትቷል፡፡

አንዳንዶች እንደሚሉት ይህ አሰቃቂ ድርጊት መስመር ለቅቆ ከመውጣቱ በፊት የሳዑዲ አረቢያ ዜጎችን ከርስ እንዲሞላ በኢትዮጵያ የተቋቋመው ሳዑዲ ስታር ኩባንያ በገንዘብ እጥረት ሊዘጋ እንደሚችል መዘገቡ የሚታወስ ነው፡፡ በወቅቱ ሪፖርተር ባወጣው ዘገባ ሳዑዲ ስታር በኪሣራ ወደ መዘጋት መድረሱ የኩባንያው “ባለቤት የሆኑትን ሼክ ሙሐመድ አል አሙዲንና የሳዑዲ ዓረቢያን ስም የሚያጎድፍ ከመሆኑም ባሻገር፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እስኪታክት የተወራለት ይህ ፕሮጀክት መና መቅረቱ ሁለቱን አካላት በሕዝቡ ዘንድ ለከፍተኛ ትችትና ወቀሳ እንደሚያጋልጣቸውም” ጠቁሞ ነበር፡፡

በአሁኑ ጊዜ “ሕገወጥ ናችሁ” በሚል ሰብዓዊነት የጎደው እርምጃ እየተወሰደባቸው ያለው የበርካታ አገራት ዜጎች በተለይም ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመውን ሰቅጣጭ ተግባር ሕገወጦችን የማባረር “ዘመቻ” በማለት ያቃለሉት የሳዑዲው አገር ውስጥ ሚ/ር ልዑል ሞሐመድ ቢን ናይፍ ወንጀለኛ ሬንጀር ለባሾችን፣ ፖሊሶችንና ወሮበሎቹን ሸባቦች አደፋፍረዋል፡፡ “ዘመቻው ይቀጥላል … በተወሰነ ጊዜ የተገደበ አይደለም” በማለት “እስክንጨርስ እንጨርሳችኋለን” የሚመስል የማፊያ መሪ መሰል መልዕክት ለአንጋቾቻቸው አስተላልፈዋል፡፡

አብዛኛዎቹ ኢትዮጵያውያን በሕጋዊነት የሚኖሩትም ጭምር በሳዑዲ ያለው ሁኔታ አሳሳቢነት ወደፊት ችግር ውስጥ ሊከትታቸው እንደሚችል በመገመት ወደ አገራቸው መመለስ ይፈልጋሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ሰቆቃ የተጋለጡት ኢትዮጵያውያን “ቤት አለን ቤታችን መልሱ” እያሉ የሰቆቃና የድረሱልን ጥሪ በሚያስተላልፉበት ወቅት ሰብዓዊነት የጎደላቸው የኢህአዴግ መሪዎች ይህ ነው የሚባል አፋጣኝ ምላሽ መስጠት አለመቻላቸው “በእርግጥ ኢትዮጵያውያን አገር አላቸው?” ብሎ የሚያስጠይቅ እንደሆነ በርካታዎች የሚጋሩት ነው፡፡

አቶ ኦባንግ በበኩላቸውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለአንድ ሳምንት ሥራውን አቋርጦ እንኳን ቢሆን ስደተኞቹን ባፋጣኝ የማመላለስ ተግባር መፈጸም ይገባው ነበር በማለት ቁጭታቸውን ተናግረዋል፡፡ ዜጎች በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ህይወታቸው እየተቀጠፈ “3ሺህ ዛሬ ገቡ … ድምሩ 10ሺህ ሆኗል …” የሚል የሞላ ጎደለ ቁማር ዓይነት ጨዋታ በትዊተር መጫወት የቴድሮስ አድሃኖምን ዘመነኛነት ሳይሆን ለሰውልጅ ህይወት ያላቸውን ደንታቢስነት የሚያሳይ መሆኑን ሁኔታው ያስቆጣቸው አስተያየት ሰጥተዋል፡፡ አቶ ኦባንግም “ቤቴ መልሱኝ” ብሎ ለሚለምን አንድ ዜጋ የተከፈለው ተከፍሎ ትራንፖርት በማቅረብ ክቡር ህይወትን በአስቸኳይ ለመታደግ አለመቻል ለትውልድ የሚተላለፍ የታሪክ ጠባሳ መሆኑን በአጽዕኖት ተናግረዋል፡፡

source. goolgule.com

ሰማያዊ ፓርቲ “የዜጎችን ሰቆቃ እና በደል ችላ ማለት ከግፈኞች ጋር እንደመተባበበር ይቆጠራል” አለ

ሰማያዊ ፓርቲ “የዜጎችን ሰቆቃ እና በደል ችላ ማለት ከግፈኞች ጋር እንደመተባበበር ይቆጠራል” አለ

semayawi-party

“የላንቻ ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊዎች ሳዑዲ ኤምባሲ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተሳተፉና ታስረው በዋስ የተለቀቁ ዜጎችን በስልክ እየደወሉ በመጥራት ማስፈራሪያና ድብደባ እያደረሱ ነው፡፡ሃላፊዎቹ ከ3 ቀናት በፊት ወጣት ዮናስ ከድርን በስልክ በመጥራት በ2 ደህንነቶች የስደበደቡት መሆኑ የሚታወስ ሲሆን በትናንትናው እለትም በእለቱ ታስረው ለነበሩት በሙሉ ስልክ ደውለው የጠሯቸው ሲሆን በጉዳዩ ላይ በመነጋገር ህጋዊ መጥሪያ ካልተሰጠን አንሄድም የሚል ምላሽ ሰጥተው ሳይሄዱ ቀርተዋል፡፡” ሲል በፌስ ቡክ ገጹ የዘገበው ሰማያዊ ፓርቲ ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ “የዜጎችን ሰቆቃ እና በደል ችላ ማለት ከግፈኞች ጋር እንደመተባበበር ይቆጠራል” አለ። ሙሉ መግለጫው የሚከተለው ነው፦

ሰማያዊ ፓርቲ በሳውዲ አረቢያ የሚገኙ ዜጎቻችን ላይ የሳውዲ መንግስት እያደረሰ ያለውን እስራት፣ ስቃይ እና ግድያ በመቃወም እና ህይወታቸው ላለፈ፣ ለተደበደቡ እንዲሁም የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ህዝቡ ሃዘኑን እንዲገልጽ በመጪው እሁድ በሚደረገው ታላቁ ሩጫ ላይ የሚሮጡ ተሳታፊዎች ጥቁር ሪቫን አድርገው እንዲሮጡ ጥሪ ማስተላለፉ የሚታወቅ ነው፡፡
ይሁን እንጂ የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች ይህንን ጥሪ እንደሚቃወሙት እና በፕሮግራሙም ላይ ጥቁር ሪቫን ያሰረ ተሳታፊን እንደተሳታፊ እንደማይቆጥሩ መናገራቸው ፓርቲያችንን እጅግ አሳዝኖታል፡፡ ፓርቲያችን ይህንን ጥሪ ሲያስተላልፍ አላማው ፍጹም ፖለቲካዊ አንድምታ የሌለው ሲሆን ጥያቄውም በዜጎች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት እና ግድያ እንዲቆም እና ፍትሃዊ እርምጃም እንዲወሰድ ለመጠየቅ ብቻ እና ብቻ እንጂ ሌላ አላማ እንደሌለው እየታወቀ የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች ግን ጉዳዩ ከፖለቲካ ጋር ለማያያዝ መሞከራቸው የሚያስተዛዝብ እና ህዝባዊ ወገንተኝነታቸውን ጥያቄ ውስጥ የሚከት ነው፡፡
ስፖርት ሰላማዊ ነገር የሚሰበክበት እንዲሁም እኩይ ተግባራት የሚወገዙበት መድረክ ነው፡፡ በአለማችን ላይ በተለያዩ ጊዜያት በተከሰቱ አሰቃቂ ሰው ሰራሽ አደጋዎች በተለያዩ ስፖርታዊ ዝግጅቶች ላይ ሲወገዙ እንዲሁም ለሰለባዎች ሃዘን የመግለጽ ስነ ስርዓትና የህሊና ጸሎት ሲደረግ መመልከት የተለመደ ነው፡፡ ታዲያ በጠራራ ፀሀይ በአደባባይ እናት ልጆችዋ ፊት እንዲሁም ሴት ልጅ ቤተሰቦችዋ ፊት ስትደፈር ከማየት የዘለለ ምን እኩይ ተግባርስ ሊኖር ነው? ታዲያ ስፖርት ይህንን ካላወገዘ ምንን ሊያወግዝ ነው?
በመጨረሻም የታላቁ ሩጫ አስተባባሪዎች የፓርቲውን ጥሪ መቃወማቸው ፓርቲያችንን ያሳዘነ እና ያስቆጣ መሆኑን እየገለጽን አሁንም ፓርቲያችን በድጋሜ በዝግጅቱ ላይ ተሳታፊዎች ጥቁር ሪቫን አድርገው እንዲሮጡ እየጠየቀ ጥቁር ሪቫኖችን ማግኘት ለማትችሉ በሰማያዊ ፓርቲ ጽህፈት ቤት ተገኝታችሁ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
ክብር ለዜጎቻችን ይሁን!!

Source http://www.zehabesha.com

የአፍሪካ ጋዜጠኞች የወያኔን ልማታዊ ጋዜጠኝነት አስተሳሰብ ተቹ :: በአለማችን ጋዜጠኞች ከሚሰደዱባት አገራት በሶስተኛ ደረጃ የምትገኝ አገር ናት ተብሏል።

የአፍሪካ ጋዜጠኞች የወያኔን ልማታዊ ጋዜጠኝነት አስተሳሰብ ተቹ 
 
አዲስ አበባ ዉስጥ በተካሄደዉ ያለዉ 6ኛው የአፍሪካ ሚዲያ አመራሮች ፎረም 
የወያኔ  ዋልጌ  ምሁራን  የፈጠራ  ዉጤት  የሆነዉንና  ወያኔ  ሌሎቹም  የአፍሪካ 
አገሮች እንዲከተሉለት በማቀንቀን ላያ ያለዉን  “የልማታዊ ጋዜጠኝነት” ጽንሰ­
ሀሳብ አላስፈላጊና ትርጉም የለሽ የሆነ ጽንሰ ሀሳብ ነዉ ሲሉ የአፍሪካ ጋዜጠኞች 
መተቻታቸዉ  ተሰማ።  ፎረሙ  ከዚህ  በተጨማሪ  ኢትዮጵያዊያን  ጋዜጠኞች 
ችግሮቻቸውን  ፊትለፊት  አውጥተው  መናገር  ባለመቻላቸውም  ወቀሳ  አነሱንና 
በጉዳዩ  እጁ  አለበት  ብለዉ  ያመኑበትን  የወያኔን  አገዛዝ  አዉግዘዋል።  ጠ/
ሚኒስትር  ተብዬዉ  ኃ/ማርያም  ደሳለኝ  በጉባዔዉ  መክፈቻ  ላይ  ባደረገዉ 
ንግግር የፕሬስ ነጻነት በኢትዮጽያ መረጋገጡን በማውሳት ፕሬሱ ግን በውስጡ 
የአቅም  ውስንነቶች  እንዳሉበትና  ይህን  ችግር  ለመፍታት  መንግሰት  እየሰራ 
መሆኑን ያለ ምንም እፍረት አፉን ሞልቶ ተናግሯል። ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከነጻ 
ፕሬስ ጋር ፍጹም የማይተዋወቀዉንና በአለም ላይ ጋዜጠኖችን በማሰር አንደኛ 
የሆነዉን  አገዛዝ  የፕሬስ  ነጻነትን  አረጋግጧል  ብሎ  መናገሩ  የራሱን  ደጋፊዎች 
ጭምር ግራ አጋብቷል። 
 
ኃ/ማርያም በዚሁ የመክፈቻ ንግግሩ በደፈናዉ ኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት አክባሪ 
መሆንዋን  ከመናገር ውጪ  በአገዛዙ ውስጥ ያሉ  የፕሬስ ማነቆዎችን  ለመደበቅ 
ሙከራ  ቢያደርግም  በጉባዔው  ላይ  ከደቡብ  አፍሪካ  ተጋብዘው  የመጡ  አንድ 
ተሳታፊ  በኢትዮጵያ  ከ70  በላይ  ፕሬሶች  ባለፉት  ዓመታት  በመንግስት  ጫና 
መዘጋታቸውን፣  ሰባት  ያህል  ጋዜጠኞች  በሸብርተኝነት  ተከስሰው  በእስር  ላይ 
እንደሚገኙ  መረጃ  እንዳላቸው  በመጥቀስ  የኢትዮጵያን  መንግስት  ተችተዋል። 
በተመሳሳይ ሁኔታ ሌላ ተሳታፊ የጉባዔው መሪ ቃል አፍሪካ ትናገር እንደሚል 
በማስታወስ  ኢትዮጵያዊያን  ወንድሞቻችን  ስለችግራቸው  ለምንድነው 
የማይናገሩት በሚል ጠይቀዋል። ይህ ያለመናገራቸው ሁኔታ በእርግጥም ችግር 
መኖሩን  እንደሚጠቁም  ጠቅሰዋል።  በአሁኑ  ወቅት  በኢትዮጵያ  ሃሳባቸውን 
በመግለጻቸው  ብቻ  በሸብርተኛነት  ተከስሰው  በእስር  ላይ  የሚገኙ  ጋዜጠኞች 
መኖራቸውን  በመጥቀስ  ጉባዔው  በዚህ  ጉዳይ  ላይ  በግልጽ  እንዲወያይና 
አቁዋሙን ሊገልጽ እንደሚገባ ተናግረዋል። 
 
አዲሱ የወያኔ የኮምኒኬሽን ሚኒስትር ሬድዋን ሁሴን ኢትዮጵያ የፕሬስ መብት 
ረጋጭ አገር ሆና እንዲህ ዓይነት አህጉራዊ ጉባዔ ልታዘጋጅ አይገባትም በሚል 
ከአንዳንድ  ወገኖች  የቀረበውን  ትችት  በተመለከተ  ተጠይቆ  እነዚህ  ወገኖች 
የኢትዮጽያን ተጨባጭ  ሁኔታ  የማያውቁ  ጸረ ልማት ሃይሎች ናቸው  በማለት 
የተለመደዉን  ወያኔያዊ  የማጣጣል  ምላሽ  ሰጥቷል።  ከዚህ  ተጨማሪ  የአፍሪካ 
ሚዲያ መሪዎች ፎረም ኢትዮጵያ ዉስጥ ከፍተኛ የፕሬስ አፈና መኖሩን በይፋ 
ከመናገሩም  በላይ  ከፍተኛ  ቁጥር  ያለቸዉ  ጋዜጠኞች  መታሰራቸውንና 
በርካታዎች  መሰደዳቸውን  በመጥቀስ  ኢትዮጵያ  በአለማችን  ጋዜጠኞች 
ከሚሰደዱባት አገራት በሶስተኛ ደረጃ የምትገኝ አገር ናት ብሏል።   

Amnesty International: Qatar rife with migrant worker abuse before World Cup “nonsense for Ethiopians“

A new report by Amnesty International finds Qatar’s construction sector rife with abuse, with workers employed on multi-million dollar projects suffering serious exploitation.

As construction is set to begin on the FIFA World Cup 2022 stadiums, the report, The Dark Side of Migration: Spotlight on Qatar’s construction sector ahead of the World Cup, unpicks complex contractual chains and reveals widespread and routine abuse of migrant workers – in some cases amounting to forced labour.

“It is simply inexcusable in one of the richest countries in the world, that so many migrant workers are being ruthlessly exploited, deprived of their pay and left struggling to survive,” said Salil Shetty, Secretary General of Amnesty International.

“Construction companies and the Qatari authorities alike are failing migrant workers. Employers in Qatar have displayed an appalling disregard for the basic human rights of migrant workers. Many are taking advantage of a permissive environment and lax enforcement of labour protections to exploit construction workers.”

In Qatar, migrant construction workers often work for small and medium sized enterprises sub-contracted to major companies who in some cases fail to ensure they are not exploited.

“Companies must ensure that migrant workers employed on construction projects linked to their operations are not being abused. They should be proactive and not just take action when abuses are drawn to their attention. Turning a blind eye to any form of exploitation is unforgivable, particularly when it is destroying people’s lives and livelihoods,” said Salil Shetty.

The report, based on interviews with workers, employers and government officials, documents a range of abuses against migrant workers. These include non-payment of wages, harsh and dangerous working conditions, and shocking standards of accommodation. Researchers also met dozens of construction workers who were prevented from leaving the country for many months by their employers – leaving them trapped in Qatar with no way out.

“The world’s spotlight will continue to shine on Qatar in the run-up to the 2022 World Cup offering the government a unique chance to demonstrate on a global stage that they are serious about their commitment to human rights and can act as a role model to the rest of the region,” said Salil Shetty.

Amnesty International’s findings have highlighted the inadequacy of the government’s existing arrangements to protect migrant workers. Amnesty International urges the government to enforce existing labour protections– which many employers flout routinely. It is also calling for an overhaul of the ‘sponsorship’ system, which leaves migrant workers unable to leave the country or change jobs without their employers’ permission.

The report also sheds light on current practices within the construction industry, in which some managers consider it normal to violate labour standards. Discriminatory attitudes towards migrant workers in Qatar – many of whom come from South or Southeast Asia – are common.  Amnesty International researchers heard a manager of one construction firm referring to the workers as “the animals”.

Such a news was reported by CNN on 19 November 2013. But neither CNN nor Amnesty international gave any coverage about the inhuman activities such us, killings, rapes , tortures against Ethiopian migrants by Saudi Arabian polices since last week.

 Exploitation of migrants in the Arab World is very immense. I did not appreciate Amnesty international at this report . it is not timely. The hot issues regarding the Arab world should be condemning the brutal, , massacre,rapping of Ethiopians that happened last week in Riyadh Saudi Arabia. more than 10 fellows died,Even the killings are just out of humanity.the Saudi boys are raping girls in groups, . It is not expected from a religious Muslims. More than 20,000 are homeless awaiting to be deporting to Ethiopia. In the mean time the are exposed to the flood that wiped Riyadh. I believe Amnesty international and CNN or other media should emphasis for such inhuman activities against migrants in Arab world!!

As it is said iabove Ethiopians were beaten, treated like a cattle in Riyadh  last week not only the case in Qatar. the 170 page report of Amnesty clearly shows http://www.amnesty.org/en/library/asset/MDE22/010/2013/en/ca15040d-290e-4292-8616-d7f845beed7e/mde220102013en.pdf   ….

Qatar has the highest ratio of migrants to citizens in the world, according to U.N. Special Rapporteur Francois Crepeau. About 94% of workers in Qatar are migrants, the United Nations’ International Labour Organization said.

The Amnesty report follows a visit to Doha by Crepeau in November to review worker standards. His preliminary findings called for abolishing the kefala system, which ties workers to a single employer. Under kefala, workers cannot change jobs without permission from employers. Crepeau also called for a minimum wage for all workers. 

 

ዶቸቬሌ -“እንዲያውም ውስጥ ውስጡን ከሳውዲዎች ጋር እየሰራ ያለ ነው የሚመስለው የኢትዮጵያ መንግስት“

እአአ ከ 610 ዓ ም ጀምሮ የእስልምና ኃይማኖት መገኛ እና ማስፋፊያ ማዕከል በመሆን ትታወቃለች። በማዕከላዊው ምስራቅ በፋርስ ባህረ ሰላጤ እና በቀይ ባህር መካከል በተንጣለለው የዓረቢያ በረሃ ላይ ጆርዳን ኢራቅ ኩዌት የመን ኦማን ቀጠር እና የተባበሩት ኣረብ ኢማራት በምድር ያዋስኗታል።

ቀድሞ ኢትዮጵያ ኣሁን ግን ከኤርትራም ጋር የባህር ማዶ ጎረቤት ናቸው። ኣሁን ያለውን ኣገራዊ ቅርጽ ይዛ በኣዲስ መልክ እንደ መንግስት የቆመችው ከ 1818 ዓ ም ጀምሮ ሲሆን ስያሜዋንም ያገኘችው እ ኣ ዘ ኣ በ 1932 ዓ ም በንጉስ አብዱልአዚዝ አል ሳዑዲ ኣማካኝነት በንጉሱ የቤተሰብ ስም ተሰይማ መሆኑ ይተረክላታል። ሳዑዲ ዓረቢያ።

በነዳጅ ዘይት ምርቷ በዓለም ቀዳሚነቱን ይዛ የምትገኘው ሳውዲ ኣረቢያ የቆዳ ስፋቷ 2 ሚሊየን ስ ኪ ሜ ገደማ ሲጠጋ በ2010 በተካሄደ ቆጠራ መሰረት 27,5 ሚሊየን ያህል ህዝብም ኣላት። ከእነዚህ መካከል 19 ሚሊየኑ ብቻ የሳውዲ ዜጎች ሲሆኑ ቀሪው ስምንት ሚሊየን ደግሞ በተለያዩ ጊዜና ሁኔታዎች ወደ ኣገሪቱ የገቡ የውጪ ዜጎች መሆናቸው ነው። ከእነዚህም መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ህጋዊ የኣገር መኖሪያ እንደሌላቸው ሲገመት ለሰሞኑ ኣስደንጋጭ ክስተትም ምክኒያት የሆነው ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት እነዚህኑ ስደተኞች የማስወጣቱ ዘመቻ ነው።

ጤና ይስጥልኝ የተወደዳችሁ የዶቸቬሌ ታዳሚዎች በዕለቱ የማህደረ ዜና ዝግጅታችንም ይህንኑ ዘመቻ ከኢትዮጵያ ኣንጻር ለመዳሰስ እንሞክራለን።

ዘውዳዊው የሳውዲ አረቢያ መንግስት በዚህ ጊዜ የዚህ ዓይነት ግራ የተጋባ ጭፍን እርምጃ ለመውሰድ የተገደደው ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደሚጠቁሙት ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ በዓረቡ ዓለም የተቀጣጠለውን እና ከቱዚያ ጀምሮ ሊቢያን እና ግብጽን ያናወጠውን እንዲሁም በጎረቤት የመን ኣድርጎ እስከ ኣሁንም ሶርያን በማተራመስ ላይ ያለውን ብሶት ወለድ የዓረብ ኣብዮት ተከትሎ ከወዲሁ ለዜጎቿ የስራ ዕድል ለመክፈት ታስቦ ነው ተብሏል።

በዚሁ መሰረት የሪያድ ኣገዛዝ ህጋዊ የመኖሪያ እና የስራ ፈቃድ የሌላቸው የውጪ ዜጎች ኣንድም ሰነዶቻቸውን እንዲያስተካክሉ ኣልያም ኣገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የ ሰባት ወር የእፎይታ ጊዜ መስጠቱ ይታወሳል። በዚህ ጊዜ ውስጥም በሳውዲ ምንጮች መረጃ መሰረት 4 ሚሊየን ያህል የውጪ ዜጎች ሰነዶቻቸውን ኣስተካክሏል። 1 ሚሊየን ገገማ ደግሞ ኣገሪቱን ለቀው መውጣታቸው ታውቐል።

የተጠቀሰው የምህረት ጊዜ ያበቃው እ ኣ ዘ ኣ ባለፈው ህዳር 3 ቀን ሲሆን ወዲያውኑ በሺዎች የሚቆጠሩ የሳውዲ ፖሊሶች በእነሱ ኣጠራር ሹርጣዎች በየአካባቢው ተሰማርተው የውጪ ዜጎችን ማሳደድ ጀመሩ። ምንም እንኩዋን እንደ ወትሮው ወደ ጎዳና የወጣ ስደተኛ ባይኖርም በስራ ቦታው እና ከየመኖሪያ ቤቱም እየገቡ ስደተኞችን ማደኑ ቀጠለ። ኣያያዙም ኃይል የተቀላቀለበት እና ስደተኞቹ እንደሚሉት ፍጹም ጭካኔ የተሞላበት ነው የነበረው።

ከፖሊስ ኃይሉ በተጨማሪ ግርግር ለሌባ ያመቻል እንዲሉ ጋጠ ወጥ የሳውዲ ወጣቶች የፖሊሶቹን ዱካ እየተከተሉ እና ቤት ሰብረው እየገቡ ገንዘብ እና ንብረት መዝረፍ ወንዶችን መደብደብ እና ሴቶችን መድፈሩን ተያያዙት። ምንም እንኩዋን ከየአቅጣጫው የሚወጡት ዘገባዎች እርስ በርሳቸው የሚጣለዙ ቢሆኑም እስከኣሁን በመቶዎች የሚቆጠሩ የአካል ጉዳት ደርሶባቿል። ጥቂት የማይባሉ ደግሞ ህይወታቸውን ኣቷል።

ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ከስደተኞቹ አንደበት መረዳት እንደተቻለው ማሳደዱም ሆነ ጭካኔው የበረታው በተለይ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ነው ተብሏል።

የሴቶቹ እሮሮ ደግሞ በእርግጥም ለየት ያለ እና ዘግናኝም ነው።

የሴት ኢትዮጵያውያን መደፈር በአሰሳው ወቅት በሚደርስባቸው ብቻም ኣልተወሰነም። ተይዘው ወደ ማጎሪያ ካምፕ ከተወሰዱ በኃላም ከካምፑ ተሰርቀው ይወሰዳሉ ተብሏል።

በዚያ ላይ የማጎሪያ ካምፑ እስረኞችም ቢሆኑ ለበረኃ ግመሎች ካልሆነ በስተቀር የሰው ልጅ ማቆያ ኣይመስልም የሚሉት የሪያድ እስረኞች ከዚሁ የተነሳ በርካታ ህጻናት እና እናቶች መታመማቸውንም ይናገራሉ።

በዚህ ጭፍን ዘመቻ ወቅት እጅግ ኣነጋጋሪ ከሆኑት ነገሮች መካከል የሳውዲ ወጣቶች በነቂስ ወተው ፖሊሶችን መከተል እና ስደተኞችን መዝረፍ መደብደብ እና በተለይ ሴቶችን የመድፈሩ ጉዳይ ነው።

የተገደሉትን ስደተኞች ቁጥር ኣስመልክቶም ከኢትዮጵያ እና ሳውዲ መንግስታት የወጡ ዓኃዞች ከሞላ ጎደል ተቀራራቢ ቢሆኑም ዘገባዎች ግን ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል ይጠቁማሉ።

«ነሲም በተባለች ከዚህ ከሪድ ኣንድ 30 እና 50 ኪ ሜ ርቃ በምት ገኘው ከተማ ባለፈው ሐሙስ ምሽት የሳውዲ ፖሊሶች ግርግር ፈጥረው 3 ሰዎችን ገግሏል። ሶስቱም ኢትዮጵያውያን ናቸው። ብዙ ሰው እኮ ነው የተገደለብን። ሰው ሲገደል ወዲያውኑ ኣንስተው ወደማይታወቅበት ቦታ ስለሚወስዱት ለጊዝው ኣይታወቅም እንጂ በጣም ብዙ ሰው ነው የተገደለው። እኔ እራሴ የማውቃቸው ከአስር ሰው በላይ እገሌ እገሊት ብዬ ልቆጥርልህ እችላለሁ።»

እስከ ኣሁን ከ 3000 በላይ ስደተኞች ኣገር ቤት ደርሷል እየተባለ ባለበት በኣሁኑ ወቅትም ከተደበቁበት ገና ያልወጡ እና ባሉበትም በረኃብ እየተቸገሩ ያሉም እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል።

ለዚህ ጭፍን እርምጃ የሳውዲ አረቢያን መንግስት መኮነናቸው ባይቀርም ስደተኞቹም ሆኑ በርካታ ኢትዮጵያውናን ይበልጥ የሚያማርሩት ግን ሪያድ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኢምባሲን እና የኢትዮጵያን መንድስትም ጭምር ነው ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ጉዳይ ከልብ እያየው ኣይመስለንም። እንዲያውም ውስጥ ውስጡን ከሳውዲዎች ጋር እየሰራ ያለ ነው የሚመስለው የኢትዮጵያ መንግስት። ኢምባሲው በተለይ ልክ የዚህ ኣገር ፖሊሶች ገድለው ኣስክሬን እንደሚደብቁት እሱም አብሮ እየደበቀ ነው እንጂ ይህንን ጉዳይ ፈጽሞ በትኩረት እያየው ኣይደለም።

የሳውዲዎች ዘመቻ በተለይ በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ ማተኮሩን ኣስመልክቶ የኢትዮጵያው የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር እርምጃውን ማውገዙ የሚታወስ ሲሆን ቃል ኣቀባዩ ኣምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለዶጨቤሌ እንደገለጹት ስደተኞቹን ወደ ኣገራቸው የመመለሱ ሂደት በተቻለፍጥነት እየሄደ ነው።

የሆነ ሆኖ በሪያድ የኢትዮጵያ ኢምባሲም ሆነ ከአዲስ ኣበባም የኃይለማሪያም ደሳለኝ ኣስተዳደር በኣጠቃላይ ከዘመቻው በፊትም ሆነ ከዚያ ወዲህ ዜጎቹን ለመታደግ የወሰዷቸው እርምጃዎች በቂ ኣይደሉም ሲሉ ብዙዎች ይከሳሉ። በዚሁ ምክኒያት ጭምር ይመስላል በዓለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ከዚያ ወዲህ በቁጣ ገንፍለው ዋሽንግተን ዲ ሲ ን ጨምሮ በተለያዩ የአሜሪካ እና የኣውሮፓ ከተሞች አደባባይ ወቷል። ወደ ሳውዲ ኢምባሲ እየሄዱም ተቃውሞኣቸውን ኣሰምቷል።

በኣገር ቤት የሚንቀሳቀሱ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ኣድራጎቱን በመኮነን መግለጫ ኣውጥቷል። ባለፈው ዓርብ ስማያዊ ፓርቲ የጠራው ሰልፍ ግን አዲስ ኣብባ ላይ ልክ እንደ ሪያድ በሳውዲ ፖሊስ ሳይሆን ግን በኢትዮጲያ ፖሊሶች እርህራሄ በሌለው ድብደባ መበተኑ በኣሳኝነቱ ተዘግቧል።

በተያያዘ ዜና የሰሞኑ የሳውዲ አረቢያ እርምጃ ታሪካዊ ስህተት ነው የሚሉ ወገኖችም ኣሉ። ኣንዱም ሼክ ነጂብ መሐመድ ሲሆኑ በዋሽንግተን ዲ ሲ የሚኖሩት ሼክ ነጂብ በኣሁኑ ጊዜ « ዘ ፈርስት ሂጂራ» የተባለው ዓለም ዓቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ የኢትኆጵያውያን እስላማዊ ተቐም መሪ ናቸው።

በእስልምና ኃይማኖት እንግዳ ይከበራል እንጂ ኣይነካም የሚሉት ሼክ ነጂብ በእስላማዊው የሸሪኣ ህግ እመራለሁ የሚለው የሳውዲ ኣገዛዝ ይህንን በማድረጉ ተጠያቂ ከመሆን ኣያመልጥም ይላሉ።

ጃፈር አሊ